ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ ከ20 ዓመታት በፊት ከአንድ ሴት ሰራተኛ ጋር ጾታዊ ግንኙነት ነበራቸው የሚል ምርምራ እየተደረገባቸው ሳለ ከማይክሮሶፍት ቦርድ አባልነት እራሳቸውን አገለሉ።

ማይክሮሶፍት በቢሊየነበሩ ጠባይ ዙሪያ ሪፖርቶች ከደረሱት በኋላ ምርመራ እያደረገባቸው ባለባት ጊዜ ነበር ቢል ጌትስ እራሳቸውን ከማይክሮሶፍትን ማግለላቸው የተሰማው።

ማይክሮሶፍት ከሕግ ተቋም ጋር በመሆነው ምርመራ መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን፤ ቅሬታውን ላቀረበችው ሠራተኛ ድጋፍ እየሰጠሁ ነው ብሏል።

ሆኖም የባለሀብቱ ቃል አቀባይ የቢል ጌትስ ከማይክሮሶፍት መልቀቅ ከምርመራው ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ብለዋል።

ከኩባንያው ጋር በተያያዘ በሰውዬው ላይ ምርመራው የመጀመሩ ዜና እየተሰማ የመጣው ቢል ጌትስ ከባለቤታቸው ጋር መለያታቸው ከተገለጸ በኃላ ነው።

ከቀናት በፊት ቢል ጌትስ 27 ዓመታት የቆየ ትዳራቸውን ለማፍረስ ከባለቤታቸው ጋር ከስምምነት መድረሳቸውን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

የማይክሮሶፍት ቃል አቀባይ ደግሞ በፈረንጆቹ 2019 መገባዳጃ ላይ ጌትስ በአውሮፓውያኑ 2000 “ከሴት ተቀጣሪ ጋር ግንኙነት ለመመስረት ፈልገው ነበር” የሚል ቅሬታ ኩባንያው መቀበሉን አስታውሰዋል።

“ለዚሁ አላማ በኩባንያው ቦርድ የተዋቀረ ኮሚቴ የቀረበውን ጉዳይ ከሕግ ተቋም ጋር በመሆን ገምግሞታል” በለዋል።

ቢል ጌትስ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ ከማይክሮሶፍት የለቀቁት በቢልና ሜሊንዳ ፍውንዴሽን የበጎ አድራጎት ስራ ላይ የበለጠ ትኩረት ለማድረግ እንደነበረ ገልጸዋል።

“ማይክሮሶፍትን በተመለከተ ከቦርድ መልቀቅ ከኩባንያው መራቅ ማለት አይደልም። ማይክሮሶፍት የህይወቴ ጠቃሚ ክፍል ሆኖ ይቀጥላል። … ኩባንያው እያከናወነ ያለው ስራና ዓለምን ለመጥቅም ባለው ተግባር የበለጠ ተስፋ አለኝ” የሚል ጽሁፍ አስፍረዋል። via bbc AmharicLeave a Reply