የአሜሪካ ኤምባሲ የሰላማዊ የተቃውሞ ጥሪውን ጠምዝዞ የማስጠንቀቂያ መልዕክት አሰራጨ

“ብሔራዊ ክብር በህብር” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን ዘመቻ በተቀናጀ መልኩ በአገር ቤትና በውጭ አገር ለመቃወም የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የአዲስ አበባ አሜሪካ ኤምባሲ የማስጠንቀቂያ መግለጫ አሰራጨ።

አሜሪካ በተለያዩ ወሳኝና አስቸጋሪ ጊዜያት ኢትዮጵያን በመክዳትና ለጠላት አሳልፋ በመስጠት የምትታወቅ አገር ናት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መታረዱን፣ ትጥቅ የፈታው በትራክ መጨፍለቁን፣ ትህነግ ይህ ሳያነሰው በማይካድራ ንጹሃንን ቀደሞ በመዘጋጀት አርዶ መሰወሩን እያወቀች ድርጊቱን ከማመን በዘለለ የወሰደችው አንዳችም አቋም አለመኖሩ ዜጎችን አሳዝኗል። የተባበሩት መንግስታትን ሃላፊነት ወስዶ ለሰላም አስከባሪነት በአፍሪካ የተሰማራውን የአገር መከላከያ ሰራዊት በጅምላ ሲታረድ ምንም ያላለችው አሜሪካ በተገላቢጦሽ እየወሰደች ያለው አቋም አግባብ አለመሆኑንን ለመቃወምና ደብዳቤ ለማሰራጨት የተደረገውን ጥሪ መልኩን ማስቀየር ለምን እንደተፈለገ አብዛኞችን ግር አሰኝቷል።

Related stories   መካከለኛዉ ምሥራቅ ሌላ ዘመን ሌላ ጥፋት

ኤምባሲው ጉዳዩን አጋኖና ለተጀመረው ኢትዮጵያን የማጥፋት ሃሳብ እንደ ግብአት ተጠቀሙበት እንጂ የተላለፈው ጥሪ ” ህዝቡ ህግና ስርዓትን በተከተለ መልኩ በየኤምባሲዎች አቅራቢያ በመገኘት ድምጹን ማሰማት ይችላል” የሚል ሲሆን ጥሪውን ያሰሙት ከአስተባባሪ ኮሚቴው ውስጥ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ዑስታዝ አቡበክር አህመድ፣ አርቲስት ዘለቀ ገሰሰን ጨምሮ ሌሎችም ታዋቂ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበት ተጠቅሶ ነበር።

በዚህ ግልጽና ሰላማዊ የተቃውሞ ጥሪ መነሻነት ነው ኤምባሲው አገልግሎት እንደማይሰጥ ቀኑንን ጠቅሶ ያስታወቀው። ሰዎችም ከኤንባሲው አካባቢ ራሳቸውን እንዲያረቁ ያሳሰበው። በአንድ ከተማ ውስጥ አገር ከልሎ የያዘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሰላማዊው ተቃውሞ ለምን እንዳስጨነቀው ግን ይፋ አላደረገም።

“ድንገት ሊከሰት የሚችል ጉዳይ ካለ ሚዲያ ተከታተሉ፣ ሰው የበዛበት አካባቢን ተጠነቀቁ፣ አካባቢያችሁን ነቅታችሁ ተከታተሉ፣ ህግን አክብሩ” ሲል ዜጊቹ ለሆኑት ጥሪ ያሰራጨው ኤንባሲው፣ ይህን ያሰራጨው ነገ የተቃውሞ ስለፍ በተለያዩ ኤምባሲዎች ዘንድ እንደሚደረገ በማህበራዊ ሚድያዎች እየተሰራጨ መሆኑንን ጠቅሶ ነው። ኤምባሲው በምን መነሻ ይህን እንዳለ ባይታወቅም ጥሪው በኦፊሳል በሚታወቁ ተጸኖ ፈጣሪ ወገኖች፣ በአገሪቱ ብሄራዊ ሚዲያዎችና ይህንን ለማስተባበር “ብሔራዊ ክብር በህብር” በሚል መሪ ቃል የሚመራዉን የተቃውሞ ዘመቻ በሚመሩ አካላት ነው።

የዘመቻው የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ አቶ አብይ ታደለ ” እስከ መጪው አርብ ባሉት ጊዜያት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆችን በማስተባበር በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚሞክሩ የውጭ ሀይሎች እጃቸውን እንዲያነሱ የሚጠይቅ ፊርማ ይሰበሰባል። እንዲሁም፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች የወከሏቸውን ሀገራት በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ የሚጠይቅና የኢትዮጵያውያንን አቋም የሚገልጹ ደብዳቤዎች እንዲደርሳቸው ይደረጋል” ሲሉ ነበር ጥሪያቸውን በይፋ ያሰሙት።

አቶ አብይ አክለውም፣ ከቀኑ 10 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት ባለው ጊዜ “ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ” የሚል መፈክር በመላው ሀገሪቱ እንዲሁም በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች እንዲስተጋባ ይደረጋል። በመጨረሻም ከምሽቱ 12 ሰዓት የዕለቱ መርሃ ግብር ማጠቃለያ እና የአጠቃላይ ዘመቻው መክፈቻ የሆነውን የኪነ-ጥበብ ዝግጅት ይካሄዳል ብለዋል። ህብረተሰቡ የኮሮና ቫይረስ መመሪያዎችን በጥንቃቄ በመተግበር የዘመቻው ተሳታፊ እንዲሆኑም አስተባባሪዎቹ ጥሪያቸውን አስተላለፈው ነበር።

ህዝቡ ህግና ስርዓትን በተከተለ መልኩ በየኤምባሲዎች አቅራቢያ በመገኘት ድምጹን ማሰማት ይችላልም ተብሏል።በአስተባባሪ ኮሚቴው ውስጥ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ዑስታዝ አቡበክር አህመድ፣ አርቲስት ዘለቀ ገሰሰን ጨምሮ ሌሎችም ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል።

ኤምባሲው አዲስ አበባ ተቀምጡ ሰላማዊውን ተቃውሞ ቢጠመዝዘውም አዘጋጆቹ ፕሮግራሙ ቀደም ሲል በተባለው መሰረት እንደሚካሄድ በድጋሚ በመንግስት መገናኛዎች ይፋ አድርገዋ።

የኤምባሲውን ማስጠንቀቂያ መንግስትንና ጥሪውን ያቀረቡትን ወገኖች ለማሸማቀቅ፣ እንዲሁም የተቃውሞውን መጠን ለማቀዛቀዝ ዒላማ ያደርገ እንደሆነ በማህበራዊ ገጾቻቸው የጻፉ አሉ። በሌላም በኩል ሰላማዊውን አንገራዊ ጥሪ ዓላማውን በማሳት ወደ ሃይልና ባንዲራ ማቃጠል ጥሪ አዙረው ሲያበቁ አስተባባሪዎቹ ባንዲራ እንዲቃጠልና በኤምባሲዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ጥሪ እንዳሰራጩ ተደርጎ በማህበራዊ ገጾች የሚያሰራጩ ታይተዋል። ስምና አድራሻ እየጠቀሱም በሌለ ጉዳይ ኢትዮጵያ ላይ ላሴሩ አገራት ተቆርቋሪ ሆነው መርጃ ሲሰጡ የነበሩም ተስተውለዋል።


 • World Bank suspends aid to Sudan after military takeover
  World Bank suspends aid to Sudan after military takeover AFP, Washington The World Bank said Wednesday it has suspended aid to Sudan following the military takeover that deposed the prime minister. “I am greatly concerned by recent events in Sudan, and I fear the dramatic impact this can have onContinue Reading
 • Sudan PM Released As Protesters Face Tear Gas
  Sudanese Prime Minister Abdalla Hamdok was brought home late Tuesday, his office said, after a day of intense international pressure following his removal in a military coup. Hamdok was “under close surveillance” while other ministers and civilian leaders remained under arrest, his office added, after the army dissolved Sudan’s institutionsContinue Reading
 • Sudan State Oil Workers to Join Civil Disobedience Movement
  Workers at Sudan’s state petroleum company Sudapet said on Wednesday they would join a nationwide civil disobedience movement called by trade unions in response to the military’s overthrow of the government, and doctors also announced a strike. A group of neighborhood committees in Khartoum have announced a schedule of furtherContinue Reading
 • African Union Suspends Sudan’s Participation in Organisation’s Activities
  MOSCOW (Sputnik) – The African Union (AU) has suspended Sudan’s participation in the activities until the country’s civilian transitional government is restored.In a statement, the AU said that its Peace and Security Council decided to suspend Sudan’s participation in all activities of the organization. Sudanese military detained Prime Minister AbdallaContinue Reading
 • ጌታቸው ረዳ የማያውቃቸው የጄ. ይልማ መርዳሳ ንሥሮች
  …. SU-27 ሆዬ 100KM ላይ ኢላማውን አረጋግጦ ሚሳይልና ቦምቦቹን አራግፎለት ተመልሷል። በዚህ ቅፅበት የጌቾ ሰዎች ፍንዳታ እና እሳትን እንጂ SU-27 መምጣቱንም ማወቅ አይችሉም። ጌቾ ፍንዳታውን በተመለከተ መረጃ ሳይደርሰው/ በማይሰማበት ቅፅበት ጄቱ ሚሳይሉን ካስወነጨፈበት የ 100KM ርቀት አፍንጫውን ወደ ደብረ ዘይት መልሶ ከድምፅ ሁለት እጥፍ በላይ ተወንጭፎ ወደ ጦር ሰፈሩ ለማረፍContinue Reading

2 Comments

 1. ኣሁን በቃኝም አዘንኩም ። የእዚህ መነሻ ኣንዳርጋቸው እና ንግ ግሩ መሆኑን ለመጥቀስ ኣለመድፈርህ ያሳዝናል ምን ያህል ቢከፍሉህ ነው ። ለእዚህ ለእዚህ ከእነ ኣላሙዲን ኣይሻልህም ነበር በእርግጠኝነት ነገም ክብር ኣቶ ኣብነት ገብረመስቀል ብለህ እንድምትጽፍ እርግጠኛ ነኝ ። ለእመቤት ታምሜ ለገረድ ሞታለው ማለት ይሄ ነው ።
  በአንድ ወቅት የሚዲያ ቁንጮ ነበርክ ዛሬ ግን ያሳዝናል

  1. ስለ አስተያየትህ አመሰግናለሁ። ሃሳብህንም አከብራለሁ። በምታውቀኝ መተን ስለግምገማህም አመሰግናለሁ። የአንዳርጋቸውን ንግግር ዘነግቼው ሳይሆን ባራግበው አይጠቅምም የሚል ሃላፊነት ለመውሰድ ነው። አብነት ላልከው አይመስለኝም። አይመስለኝም ግን መልካም ከስራ ባደንቅ ምንም ክፋት እንዳለው አላስብም። በድጋሚ አመሰግናለሁ።

Leave a Reply