‹‹የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የኢትዮጵያን እውነታ የተረዳ አይመስልም… የተሳሳተ መረጃዎችም የሚሰጧቸው አሉ››

‹‹የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የኢትዮጵያን እውነታ የተረዳ አይመስልም። የመረጃ እጥረቶች አሉባቸው። የተሳሳተ መረጃዎችም የሚሰጧቸው አሉ››፣ በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመው አይነት ጥቃት በአሜሪካ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ አሜሪካኖች ኢትዮጵያ ያደረገችውን ነበር የሚያደርጉት ሲሉ በሰሜን ካሮላይና በኤ ኤንድ ቲ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና የጋዜጠኝነት መምህሩ ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ተናገሩ።

የአሜሪካ ዴሞክራት ፓርቲ አመራሮች በብቃታቸውና በአፈጻጸማቸው የተነሳ ጸረ-ኢትዮጵያ ከሆኑ እንደምነቀጣቸው፤ ድምጻችንንም ለሪፐብሊካን እንደምንሰጥ በግልጽ ነግረናቸዋል፤ በተጨባጭም ልዩነት እንደምንፈጥር አሳይተናቸዋል ብለዋል።

ፕሮፌሰር ብሩክ ‹‹ሃሽታግ ስለኢትዮጵያ ያገባኛል›› በሚል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሚያቀርበው የኦንላይ ውይይት መድረክ ላይ በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ አሸባሪው ህወሓት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ አባላት ላይ የፈጸመው አይነት ክህደትና ጥቃት በአሜሪካ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ አሜሪከኖች ያለምንም ማመንታት ኢትዮጵያ የወሰደችውን አይነት እርምጃ ነበር የሚወስዱት።

ኢትዮጵያውያን የአገራቸውን ሉዓላዊነት ለማስከበር በህብረት የሚያደርጉትን ጥረት በማጠናከር በህብረትና በቅንጅት የውጭ ጫናን ሊቋቋሙ ይገባል ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ በአሜሪካ በኢትዮጵያውያን የሚደረጉ ሰልፎች አገራችንን ለቀቅ አድርጉ መልዕክት የሚያስተላልፉ መሆኑን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በአገሩ ሉዓላዊነት የማይደራደርና አንድነት ያለው በመሆኑ አሜሪካ በራሷ አገር ወታደር ላይ ጥቃት ቢደርስ የማታልፈውን ኢትዮጵያ እንድታልፍ ግፊት እያደረገች ትገኛለች ብለዋል። ኢትዮጵያውያን በሰልፎች ላይ የሚይዟቸው መፈክሮችና ፖስተሮች የሚያሳዩት ይህንን ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ በዓለም አቀፍ ቋንቋዎች መልዕክቱ እንደሚተላለፍም ጠቁመዋል።

ለአሜሪካ ፖለቲከኞችም ‹‹በምርጫ ድምፃችንን በመንፈግ እንቀጣችኋለን›› የሚል መልዕክት መተላለፉን ጠቁመዋል። ይህ ደግሞ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር ፕሮፌሰር ብሩክ አመልክተዋል። ‹‹የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የኢትዮጵያን እውነታ የተረዳ አይመስልም። የመረጃ እጥረቶች አሉባቸው። የተሳሳተ መረጃዎችም የሚሰጧቸው አሉ›› ሲሉ ተናግረዋል። መረጃውን የሚያገኙት ላለፉት 30 ዓመታት ካለፈው መሪ ፓርቲ ጋር በፈጠሩት ሰንሰለት መሆኑንም ተናግረዋል። ጦርነቱን ራሱ ህወሓት እንደጀመረው ፕሮፌሰር ብሩክ አስታውሰው፤ ጥቃቱን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንግሥት ያደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ የአገር ሉዓላዊነትን የማስጠበቅ ሥራ መሆኑንም አመልክተዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።


 • ትህነግ ቅድመ ሁኔታ አንስቶ ድርድር ጠየቀ፤ “ክተቱ ለትህነግና ለኢትዮጵያ ጠላቶች እንጂ ለትግራይ ሕዝብ አይደለም”
  አዲስ አበባ በሁለት ሳምንት ለመግባት የሚያግደው አንዳችም ሃይል እንደሌለ በይፋ ያስታወቀውና በቃል አቀባዩ ጌታቸው አማካይነት ትናንት ጎንደርና ወልቃይት በአሸባሪው ትህነግ እጅ መውደቁን ያወጀው ቡድን ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ትቶ ድርድር እንደሚፈልግ ማስታወቁ ተሰማ። ለዚሁ ተግባር አዲስ አበባ የገቡ አሜሪካዊ አማላጆች መኖራቸውን ታውቋል። ቀደም ሲል ስምንት ቅደመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ የነበረው የትግራይ ሕዝብContinue Reading
 • ትህነግ ሲዘጋ፤ ኢትዮጵያ ትወቀሳለች- እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል?
  ኢትዮጵያዊያን ላለፉት 50 ዓመታት ስለምን በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ይሰቃያሉ? በረሃ ሆኖ ስቃይ፣ መንግስት ሆኖ መከራ፣ ሲባረር ደግሞ ” እኔ የማልመራት አገር ትፍረስ” ብሎ ዘመቻ። የኢትዮጵያ ሕዝብ የድሮው ሳይቆጠር ስለምን ግማሽ መዕተ ዓመት በትህነግ ሲጠበስ ይኖራል? መቼ ነው ይህን ሕዝብ ትህነግ የሚተወው? የሰሞኑ ክተት የሳምንቱ ኩርፊያ ውጤት አይደለም። የተጠራቀመContinue Reading
 • የተመድ የሚል ጽሁፍ ያለበት ኣወሮፕላነ ምስራቅ ሃረርጌ ወደቀ
  ዛሬ አመሻሽ ላይ በምስራቅ ሀረርጌ ስለወደቀው አውሮፕላን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ለኢትዮጵያ ቼክ የሰጠው ምላሽ! ዛሬ አመሻሽ 11 ሰዓት ተኩል አካባቢ አንድ አነስተኛ አዉሮፕላን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ መዉደቁን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል። የኮምቦልቻ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዲ ቡሽራ አራት ሰዎችን የጫነዉContinue Reading
 • በትግራይ ያለው የእርዳታ ምግብ ክምችት የፊታችን አርብ ያልቃል፤ ትህነግ 170 መክኖችን እህል ጭነው እንድይገቡ ከልክሏል
  አሸባሪው ህወሓት ከ170 በላይ እርዳታ የጫኑ ከባድ መኪናዎችን አግቶ ማቆሙን የትራንስፖርት ሚኒስትሯ አስታወቁ በትግራይ ያለው የእርዳታ ምግብ ክምችት የፊታችን አርብ ያልቃል አሸባሪው ህወሓት ከ170 በላይ እርዳታ የጫኑ ከባድ መኪናዎችን አግቶ ማቆሙን የትራንስፖርት ሚኒስትሯ አስታወቁ። የዓለም የምግብ ድርጅት በትግራይ ያለው የርዳታ ምግብ ክምችት አርብ ያልቃል ሲል ገልጿል። የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊትContinue Reading

1 Comment

 1. አሁን ማን ይሙት የምዕራብ ኤምባሲ ከ ኣንድ ሚኒስተር ወይ የደሕንነት በተሻለ መረጃ የለውም እና ነው..? ። ይህን ለማወቅ የሃይ ስኩል እውቀት ኣይበቃም.? በሰሚ ሰሚ በተባራሪ ወሬ ኣቛም ይይዛል..? ኣይደለም በወሬ በሐቅም መስረት ተደርጎ ኣቛም ኣይወሰደም…!!! በጥቅም እንጂ ..!!! ለመሆኑ ማናቸው የሚያሳስቱት ??
  ኣብይ የእዚህ ዓይነት ልወደድ ባይ ሰብስቦ ነው ጉድ የሆነው

Leave a Reply