የውጭ ሀገር መንግስታት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ የሚገልፅ ደብዳቤ ለማስገባት አለመቻሉ ተጠቆመ። ደብዳቤውን ማድረስ ያልተቻለው ኤምባሲዎቹ ሆን ብለው ስራ የለም በሚል በሮቻቸውን በመዝጋታቸው ነው።

በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ለማሰማትና በሉዓላዊቷ ኢትዮጵያ ጉዳይ ጣላቃ በመግባት ዓላማው ግልጽ ያልሆነና ፍትህ ያዘነበለበት ውሳኔ እያስተላለፉ ካሉት አገሮች መካከል አሜሪካ ጉዳዩን በመገልበጥ የጸጥታ ችግር እንዳለ አድርጋ በትናንትናው ዕለት መግለጫ አውጥታ ነበር። ሰፊ ቦታ ከልላ የይዛቸው አሜሪካ በምትከተለው የተሳሳተ አካሄድ ኢትዮጵያ ግንኙነቷ ምን ሊመስል እንደሚችል ለማጤን እንደምትገደድ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።

የውጭ ሀገር መንግስታት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ የሚገልፅ ደብዳቤ ዛሬ ማለዳ መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ላደረጉ ኤምባሲዎች ለማስገባት ታቅዶ የነበረው መርሐግብር ኤምባሲዎቹ በእለቱ ዝግጁ ባለመሆናቸው መከናወን አለመቻሉ ያስታወቁት አዘጋጆቹ ናቸው።

ለዛሬ ባይቻልም በሚቀጥለው ሳምንት ከኤምባሲዎቹ ጋር ይፋዊ ቀጠሮ በመያዝ ደብዳቤዎቹን ለማድረስ መታቀዱ አስተባባሪዎቹ አመልክተዋል። ሆኖም የውጭ ሀገር መንግስታት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት የሌለው መሆኑንና እጃቸውን እንዲያነሱ የሚጠይቀው መርሐግብር ግን በተያዘለት ጊዜ ይከናወናል ተብሏል።በዚህም ዜጎች በያሉበት ቦታ ሆነው ይህ መልዕክት በተለያዩ መንገዶች እንዲያስተላልፉ የመርሐግብሩ አስተባባሪዎች ጠይቀዋል።

ከሀገራት ጋር የሚኖረውን ወዳጅነት ላይ ጥላ በማያጠለሽ መልኩና የሀገርን ገፅታ እንዳያበላሽ ጥንቃቄ በማድረግ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ህዝቡ ድምፁን እንዲያሰማም ጥሪ አቅርበዋል።

“ብሔራዊ ክብር በሕብር” በሚል የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ዜጎች ባሉበት ሆነው ጽምጻቸውን የሚያሰሙበት መርሃ-ግብር ተካሂዷል፤ በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት በይፋ በተጀመረው መርሃ ግብር ላይ ታዋቂ ግለሰቦችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል፣

“ግድቡ የእኔ ነው”

“ግድቡ ገንዘቤ፣ አባይ ደግሞ ወንዜ ነው”

“አባይ ሀብታችን ስለሆነ እንገድበዋለን”

“መምረጥ መብታችን ስለሆነ እንመርጣለን”

“ሰላማችን ጌጣችን ስለሆነ ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን” የሚሉ ግልፅ መልዕክቶች ተላልፈዋል‼

Leave a Reply