የሚያሳስበኝ ከህዝብ የተቀበልኩትን ከፍተኛ አደራ እንዴት ነው የምወጣው የሚለው ነው፤ በአንድ በኩል ሰዎች በእኔ ላይ ይህ ዓይነት እምነት ስላላቸው ኩራት ይሰማኛል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ትልቅ ኃላፊነት መሆኑንም አውቀዋለሁ፣
ፍርድ ቤቶች አሁን ነጻ ሆነው ይሰራሉ፣ ቀደም ሲል ቢሆን መንግሥት የሚከታተለውና ፍላጎት ያሳደረበት ጉዳይ ላይ በፍርድ ቤቶች ልዩ ውሳኔ ሲሰጡ አይታይም፣
በህዝብ እይታ ውስጥ ያሉ ትልልቅ ጉዳዮች ላይ ፍርድ ቤቶች ወጥ የሆነ ውሳኔ የሚሰጡ አይደሉም። አንዱ ፍርድ ቤት የሚሰጠውን ሌላው ፍርድ ቤት እያሻሻለ፣ ሌላው ፍርድ ቤት የሚሰጠውን ሌላው እያጸና ነው፤
አሁን ከአስፈጻሚው አካል በእኔም ሆነ በሌሎች የፍርድ ቤት አስተዳዳሪዎች ላይ ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት የለም፣
በፍትህ ዘርፉ በአጭር ጊዜ ሊታዩ የሚችሉ ለውጦች ቢኖሩም ብዙዎቹ ግን ሂደቶች በመሆናቸው ጊዜ ይፈልጋሉ፣
ለሪፎርም ስራዎቻችን ዋና መሰረት የሆኑት ሁለት አዋጆች ናቸው፤ አንዱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን አወቃቀርና የስልጣን ደረጃን የሚመለከት፤ ሁለተኛው የዳኞች አስተዳደርን የሚመለከት ሲሆን በተለይ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔን አሁን ላይ በአብዛኛው የዳኞች ተወካይ የሚሆኑት ዳኞች ናቸው፣
ባለፈው ዓመት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከመጡት ጉዳዮች 90 በመቶ ያህሉ የተወሰኑት ከአንድ ዓመት በታች በሆነ ጊዜ ነው፤ አንድ ጠበቃ ስትነግረኝ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአምስት ቀን ጉዳይ ተፈጽሟል፣
የምርጫ አዋጁ 1112/11 ለምርጫ ፍርድ ቤቶች በልዩ ሁኔታ መደራጀት እንዳለባቸው ይደነግጋል፤ ምክንያቱም ከመደበኛ ስራዎች ለየት ባለ ሁኔታና ፍጥነት የምርጫ ጉዳዮች መታየት ስለሚኖርባቸው፣
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ዳኛ ያላቸው 11 ችሎት፤ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስት ሦስት ዳኞች ያሉባቸው አስር ችሎቶች እንዲሁም እዚህ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለጊዜው ሂደቱ ገና ስለሆነ ይፋ አላደረግንም ግን ሰባት ችሎቶች ተደልድለዋል፣
አሁን ያለን የስነሥርዓት ሕግ በመደበኛ ሂደት ማስረጃ ተሰምቶ ውሳኔ መስጠት የሚያስችል ነው፤ የምርጫን ሁኔታ የሚያካትት ስርዓት ባለመሆኑ ልዩ የምርጫ ስነስርዓት ሕግ ያስፈልጋል፤ይህ በእኛ አገር የተጀመረ አይደለም፤ ሌላ አገርም ያለ ነው፣
መወሰን ያለበት በስንት ጊዜ ነው? የይግባኝ ሂደቱ ምን መምሰል አለበት? የሚሉትንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች የሚመለከት አዲስ የስነሥርዓት ሕግ አርቅቀን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየታየ ነው፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይጸድቃል፣
ዳኛው በወሰደው መንገድ ሕጉን መተርጎም መብቱ ነው። ነገር ግን ከሕግ ውጪ እንደተሰራ የሚያሳይ ማስረጃ ካለ ተጠያቂነትን ያስከትላል፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በፍርድ ቤቶች የተከናወኑ የለውጥ ስረዎችንና 6ኛው ሀገራዊ ምርጫን አስመልክተው የሰጡትን ዝርዝር ማብራሪያ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር በምትታተመው ዘመን መጽሔት የሚያዚያ ወር እትም ላይ ያገኙታል!!ዘመን መጽሔት በገበያ ላይ ናት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa