በቻይና በተካሄደ አገር አቋራጭ የተራራ (አልትራማራቶን) ውድድር ላይ በተከሰተ ከባድ የአየር ሁኔታ የ21 ሯጮች ሕይወት አልፏል። በ100 ኪ.ሜ (60 ማይልስ) የአልትራማራ ውድድሩ በጋንሱ አውራጃ የቱሪስት ስፍራ በሆነው በቢጫ ወንዝ የድንጋይ ደን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መካሄዱ ተገልጿል።
በወቅቱም በተከሰተው ከፍተኛ ንፋስ እና በረዶ የቀላቀለበት ዝናብ አትሌቶቹ በመመታታቸው በውድድሩ ከተሳፉ 172 ሯጮች መካከል አንዳንዶቹ ሲጠፉ ÷21 ሯጮች ለህልፈት መዳረጋቸው ተገልጿል። ውድድሩ ተቋርጦም የነፍስ አድን ሥራ መጀመሩ ተመላክቷል።
በዚህም ከተሳታፊ አትሌቶች መካከል 151 የሚሆኑት ደህንነታቸው የተረጋገጠ ሲሆን÷ ከነዚህ ውስጥ ስምንቱ መቁሰላቸውም ነው ባለሥልጣናቱ የገለጹት ፡፡ ውድድሩ ሲጀመርም የተወሰኑ ተወዳዳሪዎችን ቁምጣ እና ቲሸርት ብቻ ለብሰው እንደነበር ነው የተገለጸው ፡፡
በሕይወት የተረፉት ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትም ÷የአየር ሁኔታው በእይታቸው ላይ ተጽዕኞ በማሳረፉ መንገዳቸውን መሳታቸውን ገልጸዋል። የአየር ንብረት ትንበያው የተወሰነ ንፋስ እና ዝናብ እንደሚጠበቅ ቢተነብይም እነሱ የገጠማቸውን ያህል የከፋ የአየር ጸባይ ሊኖር እንደሚችል አለመግለጹን ተናግረዋል።
ሩጫው ከተጀመረ ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላ በተራራማው ክፍል በበረዶ ፣ በከባድ ዝናብ በመምታቱ የአካባቢው ሙቀት መጠኑን እንዲያሽቆለቁል ምክንያት መሆኑን በአቅራቢያው የሚገኘው የቤይን ከተማ ባለሥልጣናት ገልጸዋል ፡፡
የነፍስ አድን ስራው ሌሊቱን ሙሉ እስከ እሁድ ጠዋት የቀጠለ ሲሆን÷ ተጨማሪ የሙቀት መጠን መቀነሱ ፍለጋውን ይበልጥ ከባድ እንዳደረገው የቻይናው የዜና አውታር ዘግቧል ፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”“የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም!” በሚል ርዕስ የወልቃይት ጠገዴ… Read more: የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”
- በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!More stories አብይ አህመድና ተቀናቃኝ ድርጅቶችApril 3, 2024 አዲሱ ሚኒስትር… Read more: በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran,… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report