በቻይና በተካሄደ አገር አቋራጭ የተራራ (አልትራማራቶን) ውድድር ላይ በተከሰተ ከባድ የአየር ሁኔታ የ21 ሯጮች ሕይወት አልፏል። በ100 ኪ.ሜ (60 ማይልስ) የአልትራማራ ውድድሩ በጋንሱ አውራጃ የቱሪስት ስፍራ በሆነው በቢጫ ወንዝ የድንጋይ ደን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መካሄዱ ተገልጿል።
በወቅቱም በተከሰተው ከፍተኛ ንፋስ እና በረዶ የቀላቀለበት ዝናብ አትሌቶቹ በመመታታቸው በውድድሩ ከተሳፉ 172 ሯጮች መካከል አንዳንዶቹ ሲጠፉ ÷21 ሯጮች ለህልፈት መዳረጋቸው ተገልጿል። ውድድሩ ተቋርጦም የነፍስ አድን ሥራ መጀመሩ ተመላክቷል።
በዚህም ከተሳታፊ አትሌቶች መካከል 151 የሚሆኑት ደህንነታቸው የተረጋገጠ ሲሆን÷ ከነዚህ ውስጥ ስምንቱ መቁሰላቸውም ነው ባለሥልጣናቱ የገለጹት ፡፡ ውድድሩ ሲጀመርም የተወሰኑ ተወዳዳሪዎችን ቁምጣ እና ቲሸርት ብቻ ለብሰው እንደነበር ነው የተገለጸው ፡፡
በሕይወት የተረፉት ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትም ÷የአየር ሁኔታው በእይታቸው ላይ ተጽዕኞ በማሳረፉ መንገዳቸውን መሳታቸውን ገልጸዋል። የአየር ንብረት ትንበያው የተወሰነ ንፋስ እና ዝናብ እንደሚጠበቅ ቢተነብይም እነሱ የገጠማቸውን ያህል የከፋ የአየር ጸባይ ሊኖር እንደሚችል አለመግለጹን ተናግረዋል።
ሩጫው ከተጀመረ ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላ በተራራማው ክፍል በበረዶ ፣ በከባድ ዝናብ በመምታቱ የአካባቢው ሙቀት መጠኑን እንዲያሽቆለቁል ምክንያት መሆኑን በአቅራቢያው የሚገኘው የቤይን ከተማ ባለሥልጣናት ገልጸዋል ፡፡
የነፍስ አድን ስራው ሌሊቱን ሙሉ እስከ እሁድ ጠዋት የቀጠለ ሲሆን÷ ተጨማሪ የሙቀት መጠን መቀነሱ ፍለጋውን ይበልጥ ከባድ እንዳደረገው የቻይናው የዜና አውታር ዘግቧል ፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት… Read more: “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council