በአዲሱ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ መሠረት ሕጋዊ ሆነው እንዲመዘገቡና ፈቃድ እንዲያወጡ የተወሰነባቸው የበይነመረብ ሚዲያዎች የሕጋዊነት ምዝገባ፣ እስከ ግንቦት 15 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲያካሂዱ ጥሪ ቢቀርብም ጥሪውን አክብረው የተመዘገቡት ጥቂት መሆናቸው ተጠቆመ። ቀነ ገደቡ ካለፈ ያልተመዘገቡት የበይነ መረብ ሚዲያዎች በሙሉ ሕገወጥ እንደሚሆኑ ይፋ ሆነ።
የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሕጉን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስን ጠቅሶ ሪፖርተር እንዳስታወቀው ባለስልጣኑ ህግን አክብረው በማይሰሩ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። ” ይታወቅልን” ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት እስካሁን የነበረው መለሳለስ አይቀጥልም። ህግን በማያከብሩት ላይ ህጋዊና አግባብነት ያለው እርምጃ ይወሰዳል።
ሕግ ለማስከበር ባለሥልጣኑ ከመቼውም በላይ ቆፍጣና ሆኖ እንደሚሰራ አቶ መሀመድ የገለጹት ለፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርት ባቀረቡበት እንደሆነ የሪፖርተር ዜና ያስረዳል። ከዚህ በፊት የነበረው እንቅስቃሴ መለሳለስ የበዛበት፣ ጥሰቶችና ግድፈቶች ሲያጋጥሙ ባለሥልጣኑ የሚሰጣቸውን የዕርምት ማስጠንቀቂያዎች ወይም ግብረ መልስ እንደ ግብዓት ከመውሰድ ይልቅ፣ ውድቅ በማድረግባለሥልጣኑ መሳለቂያ የመሆን ደረጃ የደረሰቡት ሁኔታ እንደነበረ በመግለጽ፣ የሚዲያ ተቋማት ይህን ያህል ሲወርዱ ዝም ብሎ ማየት የባለሥልጣኑ ችግር እንደነበር ጠቁመዋል።
የሚዲያዎችን፣ በተለይም በዩቲዩብ የሚሰራጩት ላይ መንግስት እጅግ የተለሳለሰ አቋም የያዘበት ምክንያት አብዛኞችን እይነጋገረ የቆየ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል። አንዳንዶቹ ” አገራቸው የት ነው” በሚባል ደረጃ ህዝብን ከህዝብ፣ ክልልን ከክልል፣ ቤተሰብን ከቤተሰ ለማጋጨት ሆን ብለው የሚሰሩ፣ ለሚያቀርቡት ዝግጅት ጥንቃቄ የማይወስዱ፣ እጅግ በወረደ ደረጃ ሙያዊ ሽታ የሌላቸው፣ ለልዩ ዓላማና ለማተራመስ የተፈጠሩ የሚመስሉ …” በሚል ጠንካራ ትችት የሚሰነዘርባቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ አስተያየት ሲሰጥ ስለነበር የባልስልጣኑንን ሪፖርት የሰማው ቋሚ ኮሚቴ ይህን አንስቶ ስለመሞገቱ በሪፖርተር ዜና አልተካክተተም። ይሁን እንጂ ይህንን ሃሳብ የሚያጸና ሃሳብ ግን ሃላፊውን ጠቅሶ አካቷል።
የተሳሳተ መረጃን ማቆም የሚቻለው የመንግሥት አካላት ስለፈጸሙትና እየፈጸሙት ስላለው ሥራ፣ ሚዲያ ሲጠይቃቸው መልስ መስጠት ሲችሉ እንደሆነም አቶ መሐመድ አመልክተው “ይሁን እንጂ ሚዲያው በዘገባው በአገራዊ ጉዳዮች የማይደራደር መሆን አለበት። ሰላም ብሔራዊ ጥቅማችን ነው” ሲሉ ሁሉም በአገሩ ጉዳይ ሃላፊነት ሊወስድ እንደሚገባ መናገራቸው በዜናው ተመልክቷል። በተመሳሳይ የመንግሥት ተቋማትና አመራሮቻቸው በሮቻቸውን ለሚዲያ ተቋማት ክፍት በማድረግ ለሕዝብ መድረስ ያለበት መረጃ እንዲደርስ፣ ጋዜጠኞች ሊታገዙ እንደሚገባ አቶ መሐመድ ጥሪ አቅርበዋል። ሃላፊዎች በሮቻቸውን በመክፈት የሚፈልጉትን ብቻ ሳይሆን የማይፈልጉትንም የመጠየቅና የመመለስ ልምድ ሊያካብቱ እንደሚገባ በማሳሰቢያ መልክ መክረዋል።
ፎቶ – ሪፖርተር
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by the people of Somaliland… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በበጎ ጎኑንና በስጋት ከፍለው መግለቻቸው ላይ… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to local companies, would bring a… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism