የቴሌግራፍ ዘጋቢ ዊል ብራውን በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻን ተከትሎ ባወጣው ዘገባ “መንግስት በትግራይ ክልል የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅሟል” ሲል ላወጣው ዘገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባጭሩ “በአሁኑ ወቅት በአገሪቷ ላይ ጫና ለማሳደር ከሚደረገው ጥረት ተለይቶ ሊታይ አይችልም” ሲል ነው መረጃ ያሰራጨው።
ሁሉም ተብሎ ካለቀ በሁዋላ የተፈለገው ባለመሳካቱ አቡነ ማቲያስ በሃይማኖት አባትነት በሚመሩት ህዝብ ላይ ዓለም ክንዱን እንዲያነሳ ሲጠይቁ “ጂኖሳይድ ተፈጽሟል” በሚል ነበር። ጫናውን ለማጥበቅ ያለመ ነው በተባለው የአባ ማቲያስ ጥሪ ተከትሎ በኢትዮጵያ ስም የዓለምን የጤና ድርጅት የሚመሩት የትህነግ አመራር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም አደባባይ ወጥተው እጅግ የተቀነባበረ መግለጫ ሰጡ። “ዘግናኝ” ሲሉ በጠሩት የትግራይ ግጭት የሆነውን ለመግለጽ ቃል እንደሚያጥራቸው አስታውቀው እሳቸውም እንደ አባ ማቲያስ ዓለም ኢትዮጵያ ላይ እጁን እንዲያነሳ ጠይቀዋል።
ይህ ከሆነ በሁዋላ ነው ቴሌግራፍ “የጦር ወንጀል መፈጸሙን የሚያሳይ መረጃ አገኘሁ” ሲል ኢትዮጵያ የተከለከለ መሳሪያ መጠቀሟን የዘገበው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የጦር ወንጀለኛ አድርጎ ለማቅረብ የትህነግ ደጋፊዎች በተደጋጋሚ መዛት የጀመሩት ገና ትግራይን ሳይለቁ እንደነበር የሚያስታውሱ እንዳሉት ውጥኑ ቀደም ሲል ጀምሮ የተቀነባበረ ስለመሆኑ ማስረጃ ነው ይላሉ።
ኢትዮጵያ ተገዳና ሰአራዊቷ ታርዶባት የገባችበትን ጦርነት መልክ ለማስቀየር በየዕለቱ መልካቸውን እየቀያየሩ የሚወጡ መረጃዎች ሄደው ሄደው የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መደረሱ የውጭ ጉዳይ እንዳለው ጫና ማጥበቂያ መሳሪያ፣ የተለመደ የሃሰት ዘገባ ነው። ዘገባው ቅሳነት ገብረሚካኤል የተባለች የ13 ዓመት ታዳጊ አንዷ በኬሚካል መሳሪያ ጉዳት የደረሰባት እንደሆነች አመልክቷል።
መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል።
“ኢትዮጵያ የኬሚካል ጦር መሳሪያ መጠቀም የሚከለክለውን ሕግ በማስፈጸም ድርጊቱንም በግንባር ቀደምነት ከሚያወግዙ አገራት አንዷ ናት”-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርግንቦት 16 ቀን 2013
ኢትዮጵያ የኬሚካል ጦር መሳሪያን መጠቀም የሚከለክለውን ሕግ በማስፈጸምና ድርጊቱንም በግንባር ቀደምነት ከሚያወግዙ አገራት አንዷ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የቴሌግራፍ ዘጋቢ ዊል ብራውን በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻን ተከትሎ ባወጣው ዘገባ “መንግስት በትግራይ ክልል የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅሟል” በሚል ላሰራጨው የተሳሳተ ጽሁፍ የመረጃውን ሐሰተኛነትና ሃላፊነት የጎደለው መሆኑን ገልጿል።
በመግለጫውም “ኢትዮጵያ እንዲህ አይነት ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ የጦር መሳሪያዎችንና በአለም አቀፍ ደረጃ በስምምነት የተቀመጡ ጸረ ኬሚካል መሳሪያ ድንጋጌዎችን በግንባር ቀደምነት ከሚተገብሩ አገራት አንዷ ነች” ብሏል።
የኬሚካል የጦር መሳሪያዎች ሰለባ የሆነችው ኢትዮጵያ የትኛውም አካል በየትኛውም ቦታ የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን ጥቅም ላይ ማዋል በጽኑ እንደምታወግዝ መግለጫው አመላክቷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዚህ አስቀድሞ ለአለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህን የመሰለ ሆን ተብሎ የተሳሳተና ኃላፊነት የጎደላቸው ሪፖርቶችን በተመለከተ ተጨማሪ ውጥረትን ከማባባስ ሌላ ዓላማ እንደሌላቸው ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማስታወቁን ገልጿል።
አሁን የተሰራጨው ሐሰተኛና ሃላፊነት የጎደለው ዘገባም በአሁኑ ወቅት በአገሪቷ ላይ ጫና ለማሳደር ከሚደረገው ጥረት ተለይቶ ሊታይ አይችልም ብሏል።የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን ማምረት፣ ማከማቸትና ጥቅም ላይ ማዋል የሚከለከለው ስምምነት የተዘጋጀው እ.ኤ.አ በ1993 መቀመጫውን በኔዘርላድ ሄግ ባደረገው የኬሚካል የጦር መሳሪያ ክልከላ ድርጅት አማካኝነት ነው። በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች 193 አገራት ስምምነቱን የፈረሙ ሲሆን ስምምነቱ ከእ.አ.አ 1997 ጀምሮ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል።
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran,… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report
- ዓለም ባንክና መንግስት በአሜሪካ እየመከሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ” የብርን የምንዛሬ አቅም ቀንሱ” ጥያቄ አልተቀበለችምዓለም ባንክና የዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም ኢትዮጵያ የጠቀችውን ብድር ለመፍቀድ… Read more: ዓለም ባንክና መንግስት በአሜሪካ እየመከሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ” የብርን የምንዛሬ አቅም ቀንሱ” ጥያቄ አልተቀበለችም