የአሜሪካ መንግስት ውሳኔ ኢትዮጵያ ከአሜሪካን ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት መልሳ እንድትገመግም ያስገድዳታል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
በአሜሪካ መንግስት የተላለፉ የቪዛ ገደቦችና መሰል ውሳኔዎች የአገራቱን የተጠናከረ ወዳጅንት ከመሸርሸሩ ባለፈ ኢትዮጵያ ከአሜሪካን ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት መልሳ እንድትገመግም እንደሚያስገድዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
ሚኒስቴሩ በአሜሪካ መንግስት የተላለፈውን ውሳኔ በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ ጋር ያለውን ግኝኙነትና ትሥሥር በአዎንታዊ ደረጃ አጠናክሮ እያራመደ ባለበት፣ የሀሉትዮሽ ግንኙነቱንና ትስስሩን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ባለበት ወቅት፣ እንደዚህ አይነት ውሳኔዎች መሰወሰኑ አገባብነት የጎደለው መሆኑንን ተገቢነት የውጭ ጉዳይ መግለጫ ያትታል።
መግለጫው ውሳኔው አግባብ አለመሆኑንን አምለክቶ እንዳለው “ አሜሪካ የውሰነሽው የቪዛ ማዕቀብ የሁለቱን አገሮች የረጅም ጊዜ የተጠናከረ ወዳጅነት የሚሸረሽር ተግባር ነው” ብሏል።
የሁለቱን አገሮች ጠንካራ ግንኙነት በሚያሳይ መልኩ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በቅርቡ የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክትኛ ተደርገው ከመጡት ጄፍሪ ፌልትማን ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ምክክር ማካሄዳቸውን መግለጫው በበጎ ጎኑ አንስቷል።
በተጨማሪም በአገሪቱ አዲስ የፖለቲካ ሽግግር ያመጣል ተብሎ የሚጠበቀውን ብሔራዊ ምርጫ ለማካሄድ ኢትዮጵያ እየተዘጋጀች ባለበት፣ የአሜሪካን ድጋፍ በምትጠብቅበት በዚህ ወቅት በምርጫው ላይ መጥፎ ጥላ ሊያጠላ የሚችል ውሳኔ ከጅምሩ መታሰብ አልነበረበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል።
አሜሪካ ያደረገችው የቪዛ ክልከላም የአገሮቹን የረጅም ጊዜ የተጠናከረ ወዳጅንት የሚሸረሽር ተግባር መሆኑን ያስታወሰው መግለጫው፣ መንግስት የኢትዮጵያን ብልጽግናን ለማሳካት ከመላው የህብረተሰብ ክፍል ጋር ብሔራዊ ምክክርን እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፤ ይህም እየሆነ ያለው ያለማንም የውጭ አማካሪ አመልካችነትና ትዕዛዝ እንዳልሆን ጠቅሷል።
ከላይ ያነሳቸውን ነጥቦች ካስረዳ በሁዋላ መግለጫው ቀደም ሲል የመንግስትን አቋም ግልጽ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ዛሬም በድጋሚ “መንግስት በአሸባሪነት ከተፈረጀው ህወሃት ጋር በምንም አይነት ሁኔታ አይደራደርም” ብሏል። አያይዞም “ የሽብር ቡድኑን እንደገና ለማነቃቃት የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ሙከራ ውጤታማ የማይሆንና መንግስት የማይታገሰው ጉዳይም ነው” ሲል አቋሙን ይፋ አድርጓል።
ከዚህ ቀደም መንግስት በግልጽ እንዳስታወቀው፣ አሁንም አሜሪካ በውስጥ ጉዳይ ላይ የምታደርገው ጣልቃ ገብነት ተገቢነት የሌለውና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጾ፣ “ ኢትዮጵያን ማንም የውስጥ ጉዳይዋን እንዴት እንደምታስኬድ የሚያሳያት አካል ሊኖር አይችልም” ሲል አስታውቋል።
መንግስት በትግራይ የሰብአዊ ድጋፍ ለመስጠት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት እና ቁርጠኝነቱን በማሳወቅ ያልተቋረጠና የሙሉ ጊዜ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም መግለጫው አመልክቷል። በአሜሪካ መንግስት የተላለፉ የቪዛ ገደቦችን እና ሌሎች ጉዳዮች የሁለቱን አገራት ለዘመናት የቆየ ገንቢ ትስስርን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳ ውሳኔ ነውም ሲል አስገንዝቧል።
ይህን መሰል ጫናዎች ከቀጠሉ ለዘመናት የቆየውን የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነቶች የሚጎዳ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካን ጋር ያለውን ሁለትዮሽ ግንኙነት መልሶ እንዲገመግም የሚገደድ ይሆናል ብሏል።
በመጨረሻም መግለጫው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያጋጠሟትን ችግሮች በሕዝቦቿ አንድነትና ድጋፍ በመሻገር ሰላሟን አስጠብቃ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ ትቀጥላለች ብሏል።
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by the… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በበጎ ጎኑንና በስጋት… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to local companies,… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism