አፍሪካ በዓመት እስከ 3.5 ቢሊየን ዶላር በመረጃ መረብ መንታፊዎች ትዘረፋለች- ኢትዮጵያ መቋጫ እናበጅ አለች

አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ድርጅቶች የመረጃ መረብ ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዳልሆነና የፖሊሲ አውጭዎች በትኩረትና በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡የበይነ መረብ ግንኙነት እየጨመረ መምጣት፣ በመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በቂ ግንዛቤ አለመኖር፣ ዝቅተኛ የዲጂታል እውቀት፣ የመረጃ መረብ ጥበቃ ባለሙያ እጥረት፣ ፍቃድ የሌላቸው ሶፍትዌሮችን መጠቀም የአፍሪካን የመረጃ መረብ ለመንታፊዎች እንዲጋለጥ አድርጎታል፡፡ ስለሆነም አፍሪካ ምነታፋውን እልባት ለማስያዘ ይቻል ዘነድ በህብረት መስራት እንዳለባት ኢትዮጵያ ጠይቃለች።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የመረጃ መረብ ደህንነት ስብሰባ ላይ አፍሪካዊያን ፖሊሲ አውጭዎች የመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በትብብር እንዲሰሩ ጠይቃለች፡፡10ኛው አለም አቀፍ የመረጃ መረብ ደህንነት ስብሰባ-አፍሪካ 2021 በበይነ መረብ እየተካሄደ ነው፡፡

ስብሰባው በመረጃ መረብ ደህንነትና የዲጂታል ጠላፊዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየመከረ ነው፡፡የአፍሪካን የመረጃ መረብ ደህንነት ሁኔታ ያብራሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሃመድ (ፒ ኤች ዲ) አፍሪካ በበይነ መረብ ግንኙነት ተደራሽነት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ብትሆንም በመረጃ መረብ መንታፊዎች በአመት እስከ 3.5 ቢሊየን ዶላር እንደምታጣ ተናግረዋል፡፡

ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት በ469 ሚሊዮን ገደማ የሞባይል መጠቀሚያዎች 456.3 ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ዝውውር እንደሚፈፀም ያብራሩት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይህ እያደገ የመጣው የሞባይል የገንዘብ ዝውውር የመረጃ መረብ መንታፊዎች አይን ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል ብለዋል፡፡

አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ድርጅቶች የመረጃ መረብ ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዳልሆነና የፖሊሲ አውጭዎች በትኩረትና በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡የበይነ መረብ ግንኙነት እየጨመረ መምጣት፣ በመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በቂ ግንዛቤ አለመኖር፣ ዝቅተኛ የዲጂታል እውቀት፣ የመረጃ መረብ ጥበቃ ባለሙያ እጥረት፣ ፍቃድ የሌላቸው ሶፍትዌሮችን መጠቀም የአፍሪካን የመረጃ መረብ ለመንታፊዎች እንዲጋለጥ አድርጎታል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካን የበይነ መረብ ደህንነት ለማስጠበቅ ከአፍሪካ 2063 አጀንዳ ጋር በተጣጣመ መልኩ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንም አብራርተዋል፡፡ በሂደት ላይ ያለው የአፍሪካ የአይ ሲ ቲ አድገት ህግና ፖሊሲ፣ የኢንተርኔት መንግስት ሰነድ መዘጋጀቱ፣ የመረጃ መረብ ደህንነትና የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ (ማላቦ ኮንቬንሽን)፣ የመረጃ ደህንነት ዳሰሳ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን መጥቀሳቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ዓለም አቀፉ የመረጃ መረብ ደህንነት ስብሰባ ትኩረቱን የመረጃ መረብ ደህንነት ላይ አድርጎ በየአመቱ የሚካሄድ ስበሰባ ነው፡፡


 • ለትግራይ ጄኔራሎች- “አይ” ካላችሁ ግን ውርድ ከራሴ ብያለሁ
  የምትከተሉት የውጊያ ስልት ያረጀና ያፈጀ ነው። የመጨረሻ ውጤቱም ትግራይን ትውልድ አልባ የሚያደርግ ነው። ለዚህ ማስረጃው ደግሞ አፋር ላይ “ክተት” ብላችሁ ልካችሁት እንደ ቅጠል ረግፎ የቀረው ወጣት ነው። የሰው ማዕበል ስትራቴጂ በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን የሚያስገኘው ውጤት ኢምንት ነው። የሰው ማዕበል በአንድ ድሮን፣ በአንድ የአውሮፕላን ቦንብ ወይም በዘመናዊ አውቶማቲክ መሳሪያ ይበተናል። አፋርContinue Reading
 • “አሸባሪው ትህነግ”በማይጠብሪ፣ በዋግ በአበርገሌ አከባቢ፣ በራያና በአላማጣ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባታል
  የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት በአውደ ዉጊያ ዉሎው ጠላትን እያንበረከከ ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን አስታወቁ። በማይጠብሪ፣ በዋግ በአበርገሌ አከባቢ፣ በራያና በአላማጣ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባታል ዋና ዳይሬክተሩ በቅጥረኛ የትህነግ ተቀጣሪ አክቲቪስቶች በሀሰት እንደሚነዛው መረጃ ሳይሆን በማይጠብሪ፣Continue Reading
 • አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቅጥፈት መግለጫ አወጣ፤ ቡድኑንን እየበጠበጠ ነው
  “ሕዝባችንና መንግስታችን” የሚል ተደጋጋሚ ሃረግ በመጠቀም መገልጫ ያሰራጨው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3000 መሰናክል እንዲወዳድር መደረጉ አግባብ እንዳልሆነ አስታወቀ። በመግለጫው የሰጠው ምክንያትና ቀደም ሲል ያቀረበው ሪፖርት አይሰማማም። ፌዴሬሽኑ በቶኪዮ ኦሊምፒክ አጠቃላይ ሂደት ላይ ያሰራጨው መግለጫ ” ከውዲሁ የለሁበትን” ዓይነት ሲሆን ውጤቱን አብዝቶ ሊጎዳ የሚችልና ኢትዮ 12 ባደረገው ማጣራትContinue Reading
 • (no title)
  Continue Reading
 • በትግራይ ያሉ የዪኒቨርሲ ተማሪዎች ወደ ሰመራ እየገቡ ነው
  በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች አፋር ክልል ሰመራ ከተማ መግባት መጀመራቸው አል ዐይን አማርኛ ያነጋገራቸው የሰመራ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡የተማሪዎች ወላጆች ከሰሞኑ ልጆቻቸው ትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመለሱ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ክልል መውጣት ከጀመረ እና የተናጠል ተኩስ አቁም ከታወጀ በኋላ ትግራይ ክልል ባሉ ዮኒቨርሲቲዎች ልጆች ያሏቸውንContinue Reading

Leave a Reply