አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ድርጅቶች የመረጃ መረብ ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዳልሆነና የፖሊሲ አውጭዎች በትኩረትና በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡የበይነ መረብ ግንኙነት እየጨመረ መምጣት፣ በመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በቂ ግንዛቤ አለመኖር፣ ዝቅተኛ የዲጂታል እውቀት፣ የመረጃ መረብ ጥበቃ ባለሙያ እጥረት፣ ፍቃድ የሌላቸው ሶፍትዌሮችን መጠቀም የአፍሪካን የመረጃ መረብ ለመንታፊዎች እንዲጋለጥ አድርጎታል፡፡ ስለሆነም አፍሪካ ምነታፋውን እልባት ለማስያዘ ይቻል ዘነድ በህብረት መስራት እንዳለባት ኢትዮጵያ ጠይቃለች።
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የመረጃ መረብ ደህንነት ስብሰባ ላይ አፍሪካዊያን ፖሊሲ አውጭዎች የመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በትብብር እንዲሰሩ ጠይቃለች፡፡10ኛው አለም አቀፍ የመረጃ መረብ ደህንነት ስብሰባ-አፍሪካ 2021 በበይነ መረብ እየተካሄደ ነው፡፡
ስብሰባው በመረጃ መረብ ደህንነትና የዲጂታል ጠላፊዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየመከረ ነው፡፡የአፍሪካን የመረጃ መረብ ደህንነት ሁኔታ ያብራሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሃመድ (ፒ ኤች ዲ) አፍሪካ በበይነ መረብ ግንኙነት ተደራሽነት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ብትሆንም በመረጃ መረብ መንታፊዎች በአመት እስከ 3.5 ቢሊየን ዶላር እንደምታጣ ተናግረዋል፡፡
ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት በ469 ሚሊዮን ገደማ የሞባይል መጠቀሚያዎች 456.3 ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ዝውውር እንደሚፈፀም ያብራሩት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይህ እያደገ የመጣው የሞባይል የገንዘብ ዝውውር የመረጃ መረብ መንታፊዎች አይን ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል ብለዋል፡፡
አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ድርጅቶች የመረጃ መረብ ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዳልሆነና የፖሊሲ አውጭዎች በትኩረትና በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡የበይነ መረብ ግንኙነት እየጨመረ መምጣት፣ በመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በቂ ግንዛቤ አለመኖር፣ ዝቅተኛ የዲጂታል እውቀት፣ የመረጃ መረብ ጥበቃ ባለሙያ እጥረት፣ ፍቃድ የሌላቸው ሶፍትዌሮችን መጠቀም የአፍሪካን የመረጃ መረብ ለመንታፊዎች እንዲጋለጥ አድርጎታል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካን የበይነ መረብ ደህንነት ለማስጠበቅ ከአፍሪካ 2063 አጀንዳ ጋር በተጣጣመ መልኩ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንም አብራርተዋል፡፡ በሂደት ላይ ያለው የአፍሪካ የአይ ሲ ቲ አድገት ህግና ፖሊሲ፣ የኢንተርኔት መንግስት ሰነድ መዘጋጀቱ፣ የመረጃ መረብ ደህንነትና የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ (ማላቦ ኮንቬንሽን)፣ የመረጃ ደህንነት ዳሰሳ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን መጥቀሳቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ዓለም አቀፉ የመረጃ መረብ ደህንነት ስብሰባ ትኩረቱን የመረጃ መረብ ደህንነት ላይ አድርጎ በየአመቱ የሚካሄድ ስበሰባ ነው፡፡
- ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡMore stories አሸባሪው ትሕነግ በአፆኪያ ገመዛ የጅምላ ግድያ መፈፀሙ ተገለፀDecember 5, 2021 “የናይል ንስር” የግብጽ ባታሊዮን ጦር ሱዳን ገባ-ኢትዮጵያዊያን በአርበኝነት ስሜት ውስጥ ናቸውMay 23, 2021 አሸባሪው ህወሓት ለመዝመት ፍቃደኛ ያልሆኑ ልጆች ወላጆችን እያሰረ መሆኑ ተነገረMay 4, 2022 “አሸባሪው ሃይል ህጻናትና አዛውንቶችን በጅምላ ጨፍጭፏል”አፋርAugust 10, 2021 ቀሲስ በላይ ከስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ… Read more: ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
- “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደትሰሞኑንን ለይቶለት ይፋ ሆነ እንጂ ውስጥ ውስጡን የጦርነት እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር መረጃዎች ከበቂ በላይ ነበሩ። ለዚህም ይመስላል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ንገሩዋቸው፣ ምክሩዋቸው” ሲሉ ከትግራይ ህዝብ ተወክለው ከመጡ ጋር ሲወያዩ ደጋግመው ያስታወቁት። በወይይቱ ላይ የተገኙ እናቶችም ” ካሁን በሁዋላ” ሲሉ ጦርነቱ ያስከተለው መዘዝና ጠባሳ እያንዘፈዘፋቸው ” ልጆቻችንን አንሰጥም” ሲሉ የተሰሙት። የድንበርና የማንነት ውዝግብ ያልተለየው የአማራና… Read more: “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደት
- የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይየ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እግሮቹ ቆስለው መራመድም ሆነ መቆም አቅተውታል። ብርክ ይዞት ይንገዳገዳል፡፡ ይህ ሰው የተሻለ ህይወት ይኖረናል ብለው በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሳኡዲ ዓረቢያ በባህር ላይ ተጉዘው ለእንግልት ከተዳረጉ ዜጎች መካከል አንዱ ነው፡፡ አብዱረሃማን ከማል ይባላል፡፡ ምስራቅ ሀረርጌ ባበሌ የትውልድ ሥፍራው ናት፡፡ በሱማሊያና በየመን አድርገን ወደ ሳኡዲ ዓረቢያ ለመግባት ሲሞክር አሲር በሚባል የሳኡዲ… Read more: የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይ
- ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል“ህወሓትና የግብረ አበሮቹ ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀቡ ይገባል” ሲል አማራ ክልል አሳሰበ። ስም ጠቅሶ ለአራተኛ ጊዜ ወረር የተፈጸመባቸውን ስፍራዎች አስታወቀ። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የፌደራል መንግስትና ዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ የህወሃትን የዳግም የጦርነት አዋጅ እንዲያወግዙና እንዲያስታግሱ ጠይቋል። ትህነግ ወረራ የፈፀመባቸው የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም እና ዛታ እንደሆኑ ያስታወቀው መግለጫው የክልሉ… Read more: ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል
- የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ ሌሎች የራያ ወረዳዎች መሸሻቸው ተሰማ። ገዳያቸውን ለመግለጽ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ዜናውን ይፋ ያደረጉት ሃላፊ ገልፀዋል። የትግራይ ሃይሎች ከአላማጣ ከተማ በሶስት ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኙ ቢገለጽም ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ “ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ… Read more: የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?