አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ድርጅቶች የመረጃ መረብ ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዳልሆነና የፖሊሲ አውጭዎች በትኩረትና በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡የበይነ መረብ ግንኙነት እየጨመረ መምጣት፣ በመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በቂ ግንዛቤ አለመኖር፣ ዝቅተኛ የዲጂታል እውቀት፣ የመረጃ መረብ ጥበቃ ባለሙያ እጥረት፣ ፍቃድ የሌላቸው ሶፍትዌሮችን መጠቀም የአፍሪካን የመረጃ መረብ ለመንታፊዎች እንዲጋለጥ አድርጎታል፡፡ ስለሆነም አፍሪካ ምነታፋውን እልባት ለማስያዘ ይቻል ዘነድ በህብረት መስራት እንዳለባት ኢትዮጵያ ጠይቃለች።
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የመረጃ መረብ ደህንነት ስብሰባ ላይ አፍሪካዊያን ፖሊሲ አውጭዎች የመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በትብብር እንዲሰሩ ጠይቃለች፡፡10ኛው አለም አቀፍ የመረጃ መረብ ደህንነት ስብሰባ-አፍሪካ 2021 በበይነ መረብ እየተካሄደ ነው፡፡
ስብሰባው በመረጃ መረብ ደህንነትና የዲጂታል ጠላፊዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየመከረ ነው፡፡የአፍሪካን የመረጃ መረብ ደህንነት ሁኔታ ያብራሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሃመድ (ፒ ኤች ዲ) አፍሪካ በበይነ መረብ ግንኙነት ተደራሽነት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ብትሆንም በመረጃ መረብ መንታፊዎች በአመት እስከ 3.5 ቢሊየን ዶላር እንደምታጣ ተናግረዋል፡፡
ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት በ469 ሚሊዮን ገደማ የሞባይል መጠቀሚያዎች 456.3 ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ዝውውር እንደሚፈፀም ያብራሩት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ይህ እያደገ የመጣው የሞባይል የገንዘብ ዝውውር የመረጃ መረብ መንታፊዎች አይን ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል ብለዋል፡፡
አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ድርጅቶች የመረጃ መረብ ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዳልሆነና የፖሊሲ አውጭዎች በትኩረትና በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡የበይነ መረብ ግንኙነት እየጨመረ መምጣት፣ በመረጃ መረብ ደህንነት ላይ በቂ ግንዛቤ አለመኖር፣ ዝቅተኛ የዲጂታል እውቀት፣ የመረጃ መረብ ጥበቃ ባለሙያ እጥረት፣ ፍቃድ የሌላቸው ሶፍትዌሮችን መጠቀም የአፍሪካን የመረጃ መረብ ለመንታፊዎች እንዲጋለጥ አድርጎታል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካን የበይነ መረብ ደህንነት ለማስጠበቅ ከአፍሪካ 2063 አጀንዳ ጋር በተጣጣመ መልኩ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንም አብራርተዋል፡፡ በሂደት ላይ ያለው የአፍሪካ የአይ ሲ ቲ አድገት ህግና ፖሊሲ፣ የኢንተርኔት መንግስት ሰነድ መዘጋጀቱ፣ የመረጃ መረብ ደህንነትና የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ (ማላቦ ኮንቬንሽን)፣ የመረጃ ደህንነት ዳሰሳ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን መጥቀሳቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ዓለም አቀፉ የመረጃ መረብ ደህንነት ስብሰባ ትኩረቱን የመረጃ መረብ ደህንነት ላይ አድርጎ በየአመቱ የሚካሄድ ስበሰባ ነው፡፡
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር መተብተቧ እየተጠቆመ ነው። በተጀመረው የአብይ ጾም ማቅ ለብሰውና አመድ ነስንሰው ችግራቸውን ሊፈቱ እንደሚገባ ምክር እየተሰጠ ነው። መንግስት በዋናነት ብቻ ባለው አስራ አንድ ጊዜ ስብሰባ የተቀመጠው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቅዱስ ሲኖዶስ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳለ የተጠቆመው አሁን ከቀናት… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡ More stories አዲስ አበባና ዙሪያዋን በሽብር ለማናወጥ ተዳራጅቶ ሲንቀሳቅስ የነበረ ሃይል ከነትጥቁ ተያዘJanuary 15, 2023 በአፋር የተደበቁ 15 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉJune 29, 2022 Ethiopia: Tigrayan forces murder, rape and pillage in attacks on civilians in… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ እውቀቶች ፈሰውበታል፤ አዳዲስ ነገሮች ተዋውቀውበታል፡፡ ዓለምን እጅ በአፍ አስጭኗል…. “ኒዮም ሲቲ” (Neom City) በሳውዲው ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ይፋ የሆነው ይህ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ በ2017 የተጀመረ ሲሆን በውስጡ አራት ሥራዎች ይገኙበታል፡፡ እነሱም ዘ ላየን፣ ኦክሳገን፣ ትሮጄና እና ሲንዳላህ… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions about the stability of the Horn of Africa and resulted in a similar deal struck between Somalia and Türkiye recently. However, arguments that the region might fall into turmoil due to Ethiopia’s move are overstated. Addis Ababa, with the deal,… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች ለዓመታት የቆየ ውዝግብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት ህገመንግስቱ በሚያዘው መሰረት በህዝበ ውሳኔ እንዲቋጭ በይፋ ስምምነት ላይ መደረሱ ተረጋገጠ። ተፈናቃዮች ወደቀያቸው መመለስ ይጀምራሉ። በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ወልቃይት ጠገዴን ጨምሮ ” ነጻ ወጡ” የተባሉት አካባቢዎች ለትግራይ እንዲመለሱ ካልተደረገ ጦርነት እንደሚቀሰቅሱ ሲገልጹ… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ