አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ አማካይነት ይፋ እንዳደረገችው የቪዛ እቀባ ያደረገችው በመልዕክተኛዋ በኩል መፍትሄ ያለችውን ሃሳብ ተግባራዊ ባለመደረጉ ወይም ” ሃሳቤን ስላታታሉብኝ ነው” ብላለች። እቀባው የአማራ ልዩ ሃይልን ሲካትት። በዋናነት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር/ ትህነግ/ የኤርትራና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ ያነጣጠረ ነው። እቀባው እንደ አሜሪካ እየታ ይመለከታቸዋል የተባሉትን አካላት የቅርብ ቤተሰቦች እንደሚመለከት ተመልክቷል

አሜሪካ ከጉዞ እገዳው በተጨማሪ ሰፊ ሊባል በሚችል ደረጃ የገንዘብ ድጋፍ ማዕቀብ ማድረጓን ያወሳው መግለጫ፣ ማዕቀቡ በተጨማሪም በደህንነት ዘርፍ የሚደረገው ድጋፍ የሚያካትት እንደሆነ አትቷል። በሌላ በኩል ግን ቁልፍ የተባሉ ድጋፎችና የሰብአዊ እርድታዎች እንደወትሮ ቀጣይ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያን “ ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ተደራደሪ” የሚለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፣ ይህንኑ ሃሳብ “እንዳይተገበር እንቅፋት ሆነዋል” ያላቸውን አካላት በሙሉ እቀባው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዝቶባቸዋል። አያይዞም “ሌሎች” ሲል የተራቸው ወዳጅ መንግስታት ከአሜሪካ ጎን እንዲቆሙ “የዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ እርምጃ መውሰድ ያለበት ጊዜ አሁን ነው” ሲል በተዛዋሪ የትዕዛዝ ጥሪ አቅርቧል።  

አሜሪካ በቀድሞው የትራምፕ አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በኢትዮጵያ ምድብተኛ የነበሩት አምባሳደር፣ እንዲሁም የተለያዩ ባለስልጣናት በይፋ ትህነግ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ባልተገመተና ባልተጠበቀ ሁኔታ የፈጸመውን ግፍና ወንጀል ማውገዛቸው፣ “ የአገር ክህደት ነው” ሲሉ በትክክለኛው ስም ጠርተው መቃወማቸው፣ ኢትዮጵያም ይህንኑ ግፍ ፈጻሚ አካል ላይ እርምጃ መውሰዷ አግባብ ነው በሚል ድጋፍ መስጠጣቸው የሚታወስ ነው።

የጆን ባይደን አስተዳደር ወደ ሃላፊነት ከመጣ በሁዋላ ስለግጭቱ ዋና መንስዔና በግፍ ታሪክ ትልቅ የተባለውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጭፍጨፋ በስህተት እንኳን ማንሳት አይፈለግም። ዛሬም አሜሪካ የጉዞ ማዕቀብ ውሳኔዋን ይፋ ስታደርግ መነሻዋ “የትግራይ ግጭት” መሆኑንና በትግራይ ግጭት ተሳታፊ የሆኑ በሚል ነው።

በትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ግጭት እንዲቆም፣ ትግራይ አሉ የተባሉ የኤርትራ ወታደሮች እንዲለቁና እንዲወጡ፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲሻሻልና በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑት ወደ ድርድር እንዲመጡ ግፊት ብታደርግም ሊሆን ባለመቻሉ የጉዞ ማዕቀቡ መታወጁን የባይደን መንግስት አስታውቋል። በዚሁ “ለማሸማገል ሞክሬ አልሆነለኝም” ሰበብ አሁን በስልጣን ላይ ያሉም ሆነ የቀድሞ የኢትዮጵያና ኤርትራ ባለስልጣናት የአሜሪካ መግቢያ ቪዛ እንዳያገኙ ታቅበዋል።

ሚዛናዊነት የተላበሰ እንዲመስል ከህግ ማስከበሩ ዘመቻ የተረፉትንና መንግስት “በረሃ ቦታ እየቀያየሩ የሚሹለከለኩ” የሚላቸው እጅግ ጥቂት የትህነግ ሰዎችንም የቪዛ ማዕቀብ እንደጣለባቸው ያወሳው መግለጫ፣ ትህነግና መንግስት እንዲደራደሩ መጠየቁ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት እንደሌለው መንግስት መልስ መስጠቱ ይታወቃል። መንግስት አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀ ደርጅት ጋር እንዲደራደር ማስገደድ ሉዓላዊነትን እንደመጣስ ተደርጎ እንደሚወሰድም አመልክቶ ነበር።

“በትግራይ ክልል የደረሰውን ቀውስ እንዲፈጠር ያደረጉና የመፍትሄ ጥሪው እንዳይሳካ ያደናቀፉ” ሲል ስም አበጅቶላቸው እቀባው እንደሚጸናባቸው ከተዘረዘሩት መካከል የአማራ ክልል ልዩ ሃይል፣ ኢመደበኛ ሃይሎችና ግለሰቦች የቪዛ እገዳ እንደተጣለባቸው መግለጫው ያመለክታል። መግለጫው ከአማራ ክልል ጋር አያይዞ ኢመደበኛ ስላላቸው ክፍሎችና “ ግለሰቦች” ያላቸውን አላብራራም። ነገር ግን ውሳኔው የትህነግን አባላትን የሚያካትን እንደሆነ ተመልክቷል።

ከተወሰደው የአሁን የጉዞ ማዕቀብ በተጨማሪ የኤርትራ ላይ ከዚህ ቀደም ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

አሜሪካ በቅርቡ ለምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ የሾመቻቸው ጄፍሪ ፊልትማን ሁሉንም አገራት ካካለሉና ባለስልጣናትን ካነጋገሩ በሁዋላ የመፍትሄ ሃሳብ ብለው ካቀረቡት መካከል ከትህነግ ሰዎች ጋር መደራደር እንደሆን ይታወሳል። ገና ሹመቱ እንደተሰታቸው ከፋይናንሺያል ታይም ጋር ዲስኩር ያደረጉት ግብረገብ የጎደላቸው ዲፕሎማት ሚዛን የጎደላቸው እንደሆኑ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአሜሪካ ወቅሷቸው ነበር።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመግለጫው ማጠቃለያ በትግራይ የተከሰተው ቀውስ እልባት እንዲያገኝ አስፈላጊውን ሁሉ ደጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ይህን ሲያስታውቅ ግን ያቀረበውን የመፍትሄ ሃሳብ ስለመቀየሩ ወይም ሊያሻሽል ስለመቻሉ ያለው ነገር የላም።

የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ ለማናቸውን እርዳታ ድርጅቶች በሩን መክፈቱን፣የፈር ማዳበሪያና የርሻ ዘር አስቀድሞ ማቅረቡን የክልሉ አማእራሮች በይፋ መናገራቸው ይታወሳል።

አንዳንዶቹ እርዳት አቅራቢዎች ከሱዳን በቀጥታ ሳይፈተሹ መግባት እንደሚፈልጉ፣ ይህ ሲሆን እርዳታውን የማስቆምና አስገድዶ የመፈተሽ ስራ እንደሚሰራ፣ በዚህ መካከል መስተጓጎል እንደሚፈጠር፣ የትህነግ ሃይል የሲቪል አስተዳደሮችን እያደፈጠ እንደሚገል፣ እርዳታ እየውሰደ ወደዋሻ እንደሚያጓጉዝ በአካባቢው ያሉ ታዛቢዎች መናገራቸው ይታወሳል።


Leave a Reply