ኢትዮጵያ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እና ለፕሬስ ነፃነት መከበር የማይናወጥ አቋም ያላት መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እና የፕሬስ ነፃነት መብቶች በሕገ-መንግሥቱ የተረጋገጡ እሴቶች ናቸው ያለው ባለሥልጣኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እነዚህን እሴቶች ለመጠበቅ ቁርጠኛ መሆኑን በድርጊት ያረጋገጠ መሆኑን ጠቁሟል። አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ወደ ሥልጣን እንደመጣ በቀዳሚነት የወሰደው እርምጃ ጋዜጠኞችን እና የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት እንደነበርም በምሳሌነት አንስቷል።
የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች የመረጃ ተደራሽነትን እንዲያገኙ ለማስቻልም ለበርካታ ዓመታት ተጥለው የቆዩት ክልከላዎች እና እንቅፋቶች ሙሉ በሙሉ መነሳታቸውንም ጠቅሷል። በአሁኑ ሰዓትም በ129 ቋሚ ዘጋቢዎች የተወከሉ 35 የውጭ የዜና ድርጅቶች ሀገሪቱ ውስጥ እንዳሉም ባለሥልጣኑ ጠቁሟል። ከዚህ ባለፈም በትግራይ ክልል ሲካሄድ በነበረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅትም ከተለያዩ ሀገራት ለተወጣጡ 82 የውጭ ጋዜጠኞች ጊዜያዊ ፈቃድ ተሰጥቶ ያለውን ሁኔታ መዘገብ የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸቱን አመላክቷል።
ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እና የፕሬስ ነፃነት መብቶች በሁሉም ወገኖች መከበር ይኖርባቸዋል ያለው የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣ ጋዜጠኞቹ የግጭት ዘገባዎችን በተመለከተ ሁኔታውን በሚገልጽ መልኩ ሙያዊ የሆኑ የአዘጋገብ ደንቦችን አክብረው ይዘግባሉ የሚል እምነት እንደነበረው አውስቷል። በየትኛውም ዓለም እንደሚደረገው ሁሉ ወታደራዊ ዘመቻ በሚካሄድበት አካባቢ ገደብ እንደሚጣል በመግለጽም፣ ፈቃድ የተሰጣቸው የውጭ ዘጋቢዎችም ይህንኑ እውነታ አክብረው እና ጠብቀው ይሠራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ የሕግ ጥሰት ሲያጋጥም በየትኛውም የዓለም ክፍል እንደሚደረገው ሁሉ ባለሥልጣኑ ሕግን የማስከበር ኃላፊነቱን የመወጣት ግዴታ እንዳለበት አስገንዝቧል። በዚሁ አግባብ ዓለም አቀፍ ተሞክሮን በመከተል በትብብር ለመሥራት እና ለዘጋቢዎች በተቻለ መጠን ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ዝግጁ መሆኑን ባለሥልጣኑ አመልክቷል። አሁንም ቢሆን መንግሥት ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እና የፕሬስ ነፃነትን መከበር በተመለከተ የያዘው አቋም የማይናወጥ መሆኑን ገልጾ፣ “ሀገሪቱም ሆነች ባለሥልጣኑ በቅንነት ሥራቸውን የሚሠሩ ጋዜጠኞችን ለማስተናገድ ዝግጁ ናቸው” ሲል ገልጿል። ( ኢዜአ)
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው”… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው” የሚለው… Read more: “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council