በማስገደድ በመውሰድ ከባድ የውንብድና ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

የዋጋ ግምታቸው ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ጌጣ ጌጦችንና ንበረቶችን በሀይልና በማስገደድ በመውሰድ ከባድ የውንብድና ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

ተስፋ ጌታቸው የተባለው ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀፅ 671 ( 1 ) (ለ) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ህዳር 20/ 2011 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ሲሆን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ”ቀራኒዮ ቢራ ማህበር“ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከግል ተበዳይ መኖርያ ቤት 2ኛ ፎቅ መኝታ ክፍል በመግባትና ሽጉጥ ግንባራቸው ላይ ይደግናል፡፡

ቀጥሎም ያለሽን የወርቅና የብር ጌጣጌጦች እንዲሁም ሌሎች ውድ ንብረቶችሽን ካላመጣሽ ልጆችሽን እገላቸዋለሁ በማለት አስገድዶና አስፈራርቶ የተለያዩ የወርቅና የብር ጌጣጌጦች ፣ ዲጂታል ፎቶ ካሜራ፣ሞባይሎችንና በጥሬ ገንዘብ 25 ሺህ ብር በአጠቃላይ ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ንበረቶችን በመውሰድ ለግል ጥቅሙ ያዋለ በመሆኑ በፈፀመው ከባድ የውንብድና ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል።

የፌደራሉ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በዐቃቤ ህግ የቀረበለትን ከባድ የውንብድና ወንጀል ክስ፣ የቀረቡትን የሰው ምስክሮችንና የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ እንደክስ አመሰራረቱ ያስረዱ በመሆኑ ተከሳሽ አሉኝ የሚላቸዉን ማስረጃዎች በማቅረብ ወንጀሉን አለመፈጸሙን እዲከላከል ዕድል ቢሰጠዉም ተከሳሽ የተመሰረተበትን ክስም ሆነ የቀረቡበትን ማስረጃዎች ማስተባበል ባለመቻሉ ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ግንቦት 02/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወንጀለኛው በ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

Leave a Reply

%d bloggers like this: