ቀደም ሲል መንግስት እያለ የአሜሪካ መንግስት ከሽብረተኞች መዝገብ ውስጥ ያልፋቀውና በቅርቡ ፓርላማ ከኦነግ ሸኔ ጋር አሸባሪ ብሎ የሰየመው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ፣ ሃያ ሁለት ዓላማውን የማይቀበሉ የአመራር አባላትን መግደሉና ሃያ ያሚሆኑትን ማገርቱ ተገለጸ።
“የተበተኑ የአሸባሪው የሕወሓት ርዝራዦች እስከ አሁን 22 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን ገድለዋል፤ 20 የሚሆኑትን አግተዋል” ሲል ያስታወቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ነው።
የተበተኑ የአሸባሪው የሕወሓት ርዝራዦች በተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች እስከ አሁን ድረስ ብቻ 22 የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር አባላት መግደላቸውን ፣ ከዚህ በተጨማሪ 20 የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላት መታገታቸውን እና 4 የአስተዳደሩ አባላት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው ለሕክምና ሆስፒታል መግባታቸውን ስፍራና የስራ ሃላፊነት ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።
“እየታገልኩ ያለሁት ለትግራይ ህዝብ ነው የሚለው አሸባሪው ሕወሓት ይልቁንም የክልሉን ሃብት እያወደመ እንዲሁም በክልሉ መረጋጋትን ለማምጣት የሚሰሩ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላትን እየገደለና እያገተ” ነው ሲል መረጃው አስታውቋል።
በትግራይ የሰብአዊ ዕርዳታ በወጉ እንዳይዳረስና በነጻነት እንዳይሰራጭ ህወሃት በየስርቻው እየተሹለከለከ እክል መፍጠሩን፣ ሰላማዊ ዓላማውን የማይደግፉትን አካላት መግደሉን በመጥቀስ የክልሉ ምክትል አስተዳዳሪ መናገራቸው ይታወሳል። ህወሃት ይህን ቢያደርግም የውጭ ሚዲያዎችና የመብት ተቆርቋሪዎች መረጃውን አይጠቀመኡበትም።
- ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡMore stories የአውሮፓ ህብረት፤ በኢትዮጵያ አዲስ ከሚመሰረተው መንግስት ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ ነውOctober 1, 2021 ኢትዮጵያ የ “50… Read more: ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
- “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደትሰሞኑንን ለይቶለት ይፋ ሆነ እንጂ ውስጥ ውስጡን የጦርነት እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር መረጃዎች ከበቂ በላይ ነበሩ። ለዚህም ይመስላል ጠቅላይ… Read more: “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደት
- የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይየ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እግሮቹ ቆስለው መራመድም ሆነ መቆም አቅተውታል። ብርክ ይዞት ይንገዳገዳል፡፡ ይህ ሰው የተሻለ ህይወት… Read more: የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይ
- ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል“ህወሓትና የግብረ አበሮቹ ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀቡ ይገባል” ሲል አማራ ክልል አሳሰበ። ስም… Read more: ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል
- የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ… Read more: የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?