ጋሽ አሜሪካ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ኢትዮጵያን እንደ ሸክላ በእጇ የሰራቻት እስኪመስል የሃገርን ሉዓላዊነት በሰብአዊ መብት ጥሰት ሰበብ እና በእርዳታ ስም ድብቅ የተንኮል እጇን በማርዘም ስትገፋ፤
ስለ ሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የዓለም-ዓቀፉ ማህበረሰብ በውገና ድርሰት እና በተሳሳተ ሱዛናውያን መረጃ እና የውሸት ትርክት የተዛባ ግንዛቤ መያዝ (ከዚህ ረገድ የፐብሊሲቲ ስራውን ከመስራት አንፃር የሃገሪቱ ሚድያዎች እና በየሃገሩ ያሉ አምባሳደሮች ብልጫ እንደተወሰደባቸውና ክፍተታቸው ሰፊ መሆኑ ልብ ይለዋል)
የፓለቲካ ርዕዮትንና የሃገርን ጥቅም በደንብ ያልለዩት ዱዝ “አዋቂዎቻችን” ደግሞ በደስታ ፌሽታ ሲፍከነከኑና ከበሮ ሲደልቁ፤
የግብፅ ድንፋታን እና የጎረቤት ሱዳንን ጭራ መቁላት እንዲሁም የጦርነት ትንኮሳ ስትመለከት፤
ለያዥ ለገናዥ አስቸግራ የነበረችው ትህነግ ቅሪት አካሏ ዛሬም አፈር-ልሶ ለመነሳት ሲውተረተር፣ ሲደነፍና የግጭት መርዝ ርጭት ሲያደርግ ስታይ፤
ሃገራችን በብዙ ፈተናዎች ውስጥ 6ኛውን ምርጫ ለማድረግ ደፋ ቀና ስትል፤
የህዳሴውን ግድብ ለመሙላት ብሎም ለመጨረስ የመጨረሻው ምዕራፍ መቃረቡን ስታይ፤
ሃገሪቱ በግሽበትና በኑሮ ውድነት ተወጥራ የዜጎች ህይወት ሲፈተን፤
ሃገርን በመምራት ሃገሪቱን በሁለንተናዊ የእድገት ጎዳና ወደፊት ለመውሰድ በሚደረገው የፓለቲካ አማራጭ ውድድር የተወዳዳሪ ፓርቲዎች ከአቅም በታች ወርደው ጉንጭ አልፋ እና አንዳንዴም እንቶ-ፈንቶ የሆነ ውሃ የማያነሳ የወፈፌ እና የንቅል ሙሾ አውራጅ ዥልጥ የዕድርተኞች ፓርቲ ስብስብ (በጣት የሚቆጠሩ ጠንካራ የመከራከርያ ነጥብ እና በሃሳብ ልእልና የሚሟገቱትን አይመለከትም) ዲስኩር ስትሰማ፤
በተለያዩ ቦታዎች በዜጎች ላይ በተለይም በትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ፈተና መሆንና የዜጎች ደህንነት አጣብቂኝ ውስጥ መውደቅ
አለማቀፍ የዲኘሎማስ ስራው እጅጉን ፈተና የበዛበት ትንቅንቅ ሲሆን፤
አለማቀፍ ሚድያዎች ሲኤንኤ, ቢቢሲ እና አልጀዚራ በተናበበ መልኩ የፈጣሪዎቻቸውን ህልም ለማሳካት የውገና ዘገባዎችን እና የጦርነት ድግስና የሰቆቃ ድምፅ ኦኬስትሬት ሲያደርጉ ስታይ፤
የምዕራባውያኑን ጥቅም እስካልነካ ድረስ በየትኛውም የሃገራችን ክፍል ተፈፅሞ የነበረና የሚፈፀም በደል አዓለም-ዓቀፍ ሚድያዎች በተለይም ሲኤንኤ, ቢቢሲ እና አልጀዚራ … ሌሎችም ብዙም እንደማያስጨንቃቸው በተደጋጋሚ ስታይ፤
ከጊዜ ወደጊዜ የሃገሪቱ የፓለቲካ አካሄድ ውስብስብነት እየጨመረ መሄዱን፤
የማህበራዊ ሚድያው በአብዛኛው በሚባል ደረጃ መረን የለቀቀ የጦርነት ነጋሪት መጎሰሚያ እና የውሸት አውድማ መሆኑ … ወዘተ ስታይኢትዮጵያችን ምን አይነት ከባድ ሁለንተናዊ ፈተናዎች ምዕራፍ ላይ መሆኗን ታጤናለህ። ስለዚህ ዜጎች የፓለቲካ ጭምብላቸውን አውልቀው ነገሮችን ሁሉ በሃገራዊ ጥቅም መነፅር መመልከት ግድ የሚልበት ምዕራፍ ላይ መድረሳችንን መረዳት ተገቢ ይሆናል።ሊነጋ ሲል ይጨልማል የሚባለው ብሂል ይሁን? ይነጋል!
በላይ ባይሳ
ግንቦት 20/2013 ዓ.ም
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by the people… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ ከዚህ… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በበጎ ጎኑንና በስጋት ከፍለው… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to local companies, would… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism