የጎንደር ከተማን በተለያዩ አቅጣጫዎች ለማጥቃት ተኩስ ከፍተው የነበሩ ታጣቂዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መመለሳቸውን የጎንደር ከተማ ወጣቶችና የከተማ አስተዳደሩ ዐስታወቁ።
ታጣቂዎቹ ከትናንት በስትያና ትናንት የጎንደር ከተማን የሽብር ማዕከል ለማድረግ በሦስት አቅጣጫዎች ተኩስ ከፍተው ጉዳት ማድረሳቸውን በጎንደር የአማራ ወጣቶች ማኅበር ፕሬዚደንት ተስፋ ታምራት ለዶይቼ ቬለ ተናግሯል። «ጎንደርን የሽብር ቀጠና ለማድረግ ሥራ ተሠርቶ ነበር። ድንበር አካባቢ ሰው በማገት እየተደራደሩ ገንዘብ ሲቀበሉ ቆዩ።
አሁን ደግሞ በሕዝብ ላይ ግልጽ የኾነ ጦርነት ከፍተው በአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ እንዲሁም የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ሕልማቸው አልተሳካላቸውም። አሁን ዛሬ ነው፤ ጥሩ ሠላም ነው።»የጎንደር ከተማ የሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ናትናኤል ጎሹ በበኩላቸው በስም ያልጠቀሷቸውና «የተደራጁ ቡድኖች» ያሏቸው ኃይሎች በሦስት የጎንደር ከተማ አቅጣጫዎች ጥቃት ከፍተው በመንግሥት ታጣቂዎች መመለሳቸውን አብራርተዋል።
«አንደኛው ቁስቋም ይባላል፣ አንዱ ብላጅግ ዳብርቃ ነው፣ ሌላኛው ደግሞ አዘዞ ሳይድ (አቅጣጫ)፣ በእነዚህ ሦስቱ ቦታዎች፣ ያው ቁስቋም ትንሽ ጠንከር ያለ ነበር። በርከት ያለ የጥፋት ኃይል ገብቶ ከተማውን የማጥቃት ፍላጎት ነበረው። ይህን ያህል ሕይወት ጠፋና ይህን ያህል ቆሰለ ምናምን እንደዚህ የምጠቅሰው ነገር አይኖረኝም፣ ግን የተቃጠሉ ቤቶች አሉ ዳር ወጣ ወጣ ብለው ያሉ።
ድርጊቱን የፈፀመውን ሰው በክትትል አንዳንዶቹን በቁጥጥር ስር አውለናል፤ ክትትል እያደረግን ነው።»በነበረው የተኩስ ልውውጥ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰና የታጣቂዎችን ማንነት በተመለከተ ዶይቼ ቬለ የጠየቃቸው አቶ ናትናኤል «በጥናት ይመለሳል» የሚል ጥቅል ምላሽ ሰጥተዋል። አሁን የጎንደር ከተማና አካባቢው ሰላም እንደሆነ መምሪያ ኃላፊው ማመልከታቸውን የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን የላከልን ዜና ይጠቁማል።
DW Amharic
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report
- ዓለም ባንክና መንግስት በአሜሪካ እየመከሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ” የብርን የምንዛሬ አቅም ቀንሱ” ጥያቄ አልተቀበለችምዓለም ባንክና የዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም ኢትዮጵያ የጠቀችውን ብድር ለመፍቀድ ያቀረቡት ዋና ቅድመ ሁኔታ… Read more: ዓለም ባንክና መንግስት በአሜሪካ እየመከሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ” የብርን የምንዛሬ አቅም ቀንሱ” ጥያቄ አልተቀበለችም
- ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡMore stories “የመንግስትና ኦነግ ድርድር በሰላም የድል ዜና ለሕዝብ ይፋ ይሆናል”April 28, 2023 “በትግራይ… Read more: ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
- “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደትሰሞኑንን ለይቶለት ይፋ ሆነ እንጂ ውስጥ ውስጡን የጦርነት እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር መረጃዎች ከበቂ በላይ… Read more: “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደት