የጎንደር ከተማን በተለያዩ አቅጣጫዎች ለማጥቃት ተኩስ ከፍተው የነበሩ ታጣቂዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መመለሳቸውን የጎንደር ከተማ ወጣቶችና የከተማ አስተዳደሩ ዐስታወቁ።
ታጣቂዎቹ ከትናንት በስትያና ትናንት የጎንደር ከተማን የሽብር ማዕከል ለማድረግ በሦስት አቅጣጫዎች ተኩስ ከፍተው ጉዳት ማድረሳቸውን በጎንደር የአማራ ወጣቶች ማኅበር ፕሬዚደንት ተስፋ ታምራት ለዶይቼ ቬለ ተናግሯል። «ጎንደርን የሽብር ቀጠና ለማድረግ ሥራ ተሠርቶ ነበር። ድንበር አካባቢ ሰው በማገት እየተደራደሩ ገንዘብ ሲቀበሉ ቆዩ።
አሁን ደግሞ በሕዝብ ላይ ግልጽ የኾነ ጦርነት ከፍተው በአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ እንዲሁም የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ሕልማቸው አልተሳካላቸውም። አሁን ዛሬ ነው፤ ጥሩ ሠላም ነው።»የጎንደር ከተማ የሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ናትናኤል ጎሹ በበኩላቸው በስም ያልጠቀሷቸውና «የተደራጁ ቡድኖች» ያሏቸው ኃይሎች በሦስት የጎንደር ከተማ አቅጣጫዎች ጥቃት ከፍተው በመንግሥት ታጣቂዎች መመለሳቸውን አብራርተዋል።
«አንደኛው ቁስቋም ይባላል፣ አንዱ ብላጅግ ዳብርቃ ነው፣ ሌላኛው ደግሞ አዘዞ ሳይድ (አቅጣጫ)፣ በእነዚህ ሦስቱ ቦታዎች፣ ያው ቁስቋም ትንሽ ጠንከር ያለ ነበር። በርከት ያለ የጥፋት ኃይል ገብቶ ከተማውን የማጥቃት ፍላጎት ነበረው። ይህን ያህል ሕይወት ጠፋና ይህን ያህል ቆሰለ ምናምን እንደዚህ የምጠቅሰው ነገር አይኖረኝም፣ ግን የተቃጠሉ ቤቶች አሉ ዳር ወጣ ወጣ ብለው ያሉ።
ድርጊቱን የፈፀመውን ሰው በክትትል አንዳንዶቹን በቁጥጥር ስር አውለናል፤ ክትትል እያደረግን ነው።»በነበረው የተኩስ ልውውጥ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰና የታጣቂዎችን ማንነት በተመለከተ ዶይቼ ቬለ የጠየቃቸው አቶ ናትናኤል «በጥናት ይመለሳል» የሚል ጥቅል ምላሽ ሰጥተዋል። አሁን የጎንደር ከተማና አካባቢው ሰላም እንደሆነ መምሪያ ኃላፊው ማመልከታቸውን የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን የላከልን ዜና ይጠቁማል።
DW Amharic
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ”… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ