የሕዝብና የአገርን ሚዛን ማንጋደድ- ሚዲያዎች ተቃውሞውን አዛብተው እየዘገቡ ነው

Ethiopians protest interference from US
ሊደበቅ የማይችለው ሕዝብ ለቻይና፣ ለሩሲያ፣ ለቱርክ መሪዎች ድጋፉን አሳይቷል። በግልጽ ምስላቸውም ታይቷል። ኢትዮጵያን ደግፈው ፍትህ እንዲበየን፣ ጣልቃ ገብነት እንዲወገድና ያጠፉ ብቻ እንዲጠየቁ በመጠየቃቸው ሕዝብ ድጋፍ አበርክቷል።

በመላው ኢትዮጵያ በሚባል ደረጃ ወይም በአብዛኛ ከተሞች በዛሬው እለት ” ድምጻችን ለነጻነታችን” በሚል መሪ ቃል የተካሂደውን ሰለፍ የውጭ ሚዲያዎች እያጣመሙ እየዘገቡት ነው። ቢቢሲ አማርኛ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሲል እንደዘገበው ሁሉም የውጭ ሚዲያዎች አንሸዋረው ዘግበውታል። ሰልፉ በአዲስ አበባ ስታዲየም ውስን ሰዎች ብቻ እንዲገኙ ታስቦ መካሄዱ ቢታወቅም በሚዲያዎቹ ግን አልተገለጸም። በሰለፉ ላይ ያልነበሩ መፈክሮችና የአሜሪካ ባንዲራ ሲቃጠል የሚያሳዩ አስነዋሪ ምስሎችም በማህበራዊ ሚዲያ በወገን ተብየዎች ሲሰራጭ ታይቷል።

” በአስር ሺዎች” ሲሉ ቢቢሲ አማርኛውን ጨምሮ በጠቅላላ በሚባል ደረጃ የውጭ ሚዲያዎች የዘገቡት ዘገባ በምን መነሻ አዲስ አበባ ስታዲየም ውስጥ ምን ያህል ሰው ሊይዝ እንደሚችል አለመጠቆማቸው ግልጽ አይደለም። የአዲስ አበባ ስታዲየም ከሞላ እስከ ሃያ ሺህ ብር ብቻ እንደሚይዝ በይፋ የሚታወቅ ሆኖ፣ በአዲስ አበባ ስታዲየም ውስን ሰዎች ብቻ እንዲገኙ የተደረገበት ምክንያት ይፋ ሆኖ ሳለ አነስተኛ ሕዝብ እንደወጣ አድርገው የዘገቡም አሉ።

እነዚሁ በውጭ አገር ቋንቋ የዘገቡት ዜናዎች በአጻጻፍ ስልት የተቃውሞውን ሰልፍ በማንሳት አሜሪካ የያዘችውን አቋም በማጉላት፣ የባይደንን ጥሪ በመደጋገም፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከኢትዮጵያው አቻው ጋር በህብረት ምርመራ እያደረጉ ባለበትና በገለልተኛ ወገኖች ባልተረጋገጠ መልኩ መንግስትን ጥፋተኛና ለፍርድ የሚቀርብ አድረገው ጽፈዋል። እንደተለመደው የችግሩ መስዒ የሆነውን ጉዳይ ዘለውታል። መከላከያ ሰራዊት በወገኖቹ ክህደት ተፈጽሞበትና ታርዶ ህግ ማስከበር ስለመጀመሩ አልተነፈሱም። በንግግር ላይ ቢገለጽም በዘገባቸው አልተነገረም።

ኢየሩሳሌም ፖስት የተሻለ ቢዘግብም ለምስሉ የተጠቀመው በሱዳን የተፈናቀሉ እናትን አሳዛኝ ምስል ነው። ምስሉ የሚያሳዝን ቢሆንም ሰላማዊ ሰልፉን ከቶውንም የማይወክል ነው። አሜሪካንን ላወገዘው ሰልፍ ዜና የተመረጠው ፎቶ ሪፖርቱን የሚያራክስ ሆኗል። ሚዲያዎቹ ትህነግ በተደጋጋሚ “አሸባሪ” ተብል ቢፈረጅም በተፈረጀበት ስም ሲጠሩት አልታየም። ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የተቀሱት ሚዲያዎች ” ይህን አሸባሪ እጁን መቁረጥ በምንም መስፈርት አያስወግዝም” ሲሉ የአሜሪካንን ፍርደ ገምድልነት የገለጹበትን ቁልፍ ጉዳይም አላነሱም። ውሳኔው ተቀባይነት እንደሌለው መናገራቸውን ነው የጠቆሙት። ሁሉም ሚዲያዎች እጅግ ተመሳሳይ ሪፖርት ማቅረባቸው ” ይናበባሉ” ለተባለው ማመሳከሪያ እንደሆነ ጠቋሚ ሆኗል።

aa የሚባለው ሚዲያ Hundreds of thousands of Ethiopians of all walks of life took to the streets to protest what they described as interference by the US administration. በብቸኛነት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሲል ዘግቧል። ለጉዳዩ አግባብ የሆነ ምስልም ተጠቅሟል። ምዕራባዊያን እጃችሁን አንሱ በሚል የተነሳው ተቃውሞ በመላው አገሪቱ አብዛኛ ከተሞች ቤኒሻንጉልና ጋምቤላን ጨምሮ ቢደረግም ለሚዲያዎቹ አልታያቸውም። ለወትሮው የመንግስት ሚዲያን የሚጠቅሱት ሚዲያዎች ይህን አላደረጉም። እንደውም ” የመንግስት ደጋፊዎች” ሲሉ አገራቸውን አስቀድመው ሰለፍ የወጡትን ፈርጀዋቸዋል።

May be an image of one or more people and text that says 'Browani Pro-government protesters burnt US flag today @AddisAtaba. These are literarily pro Genocide protesters @TigrayGenocide U.S. Embassy Addis Ababa U.s. Department tment of State U.S. Army U.S. Senator Elizabeth Warren U.S. Senator Kamala Harris (Archive) Haitians burn flags in anti-government demo ® Saturday 16 February 2019 10:25, UK'

ሰልፉ ዓላማውን እንደሳተ ለማስመሰልና በሰልፉ ቦታ አዘጋጆቹ ያላሰራጩትን መፈክርና ምስል ቆርጦ በመቀጠል በማህበራዊ ሚድያ ታይቷል። ከሁሉም በላይ ግን አሳፋሪ የሆነውና የመንግስት መረጃ አንታሪ ገጽ የሚከተለውን ያፋ አድርጓል። በኢትዮጵያዊ ስም የሃይቲን ተቃውሞ በመተቀም የቀረበውን አስነዋሪ ደርጊት ሁሉም ሊያጋልተው እንደሚገባ ተተቁሟል።


 • World Bank suspends aid to Sudan after military takeover
  World Bank suspends aid to Sudan after military takeover AFP, Washington The World Bank said Wednesday it has suspended aid to Sudan following the military takeover that deposed the prime minister. “I am greatly concerned by recent events in Sudan, and I fear the dramatic impact this can have onContinue Reading
 • Sudan PM Released As Protesters Face Tear Gas
  Sudanese Prime Minister Abdalla Hamdok was brought home late Tuesday, his office said, after a day of intense international pressure following his removal in a military coup. Hamdok was “under close surveillance” while other ministers and civilian leaders remained under arrest, his office added, after the army dissolved Sudan’s institutionsContinue Reading
 • Sudan State Oil Workers to Join Civil Disobedience Movement
  Workers at Sudan’s state petroleum company Sudapet said on Wednesday they would join a nationwide civil disobedience movement called by trade unions in response to the military’s overthrow of the government, and doctors also announced a strike. A group of neighborhood committees in Khartoum have announced a schedule of furtherContinue Reading
 • African Union Suspends Sudan’s Participation in Organisation’s Activities
  MOSCOW (Sputnik) – The African Union (AU) has suspended Sudan’s participation in the activities until the country’s civilian transitional government is restored.In a statement, the AU said that its Peace and Security Council decided to suspend Sudan’s participation in all activities of the organization. Sudanese military detained Prime Minister AbdallaContinue Reading

Leave a Reply