ኢትዮጵያና ቻይና በኢኮኖሚ ጉዳይ ጥብቅ ትሥሥር ለመፍጠር በተነደፈ ሰነድ ላይ በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ እየመከሩ መሆናቸው ተሰምቷል። ምክክሩ አሜሪካ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማዳሸቅ እያሴረች ባለችበት ወቅት መሆኑ ዜናውን አግዝፎታል።
የመነሻው ምክክር በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዢያን እንዲሁም ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ዝርዝር አላስታወቀም እንጂ ከፍተኛ የቻይና የኢኮኖሚ ጉዳይ አማካሪዎች ብምክክሩ ላይ መገኘታቸውን ኢትዮ 12 ሰምታለች።
ሚኒስቴሩ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዢያን በበኩላቸው፥ ሃገራቸው ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ አገራቸው ቁርጠኛ መሆናቸውን እንደገለጸች ከማስታወቁ በፊት የኢኮኖሚ ባለሙያዎቹ ብመን ጉዳይ ላይ እንደመከሩ ይፋ አላደረግም። ከኢትዮጵያ ወገን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ከመገኘታቸው ውጪ የትኞቹ ባለስልጣናት በምክክሩ እንደተገኙ ይፋ አልሆነም።
ምክክሩ ለዋናውና ወቅታዊ ለሆነው የሜሪካ ማዕቀብ ዝግጅት በአገራቱ መሪዎች ደረጃ ለሚደረግ ስምምነት መንገድየሚጠርግ ምክክር መሆኑ ተሰምቷል። ቻይና እድገቱ መፋተን እንዳለበትና ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸው ግብአቶች በአገር ውስጥ እንድታመርት የሚያችል ድጋፍ ለመድረግ ፈቃደኛ መሆኗ ታውቋል።ከኢትዮጵያም በኤክስፖርት እቃዎቿ ላይ ማዕቀብ የሚጣልባት ከሆነ በቻይና ሰፊ ገበያ ልትመሰርት ስለምትችልበት ሁኔታ በምክክሩ እቅድ መነደፉ ተሰምቷል።
ቻይና በጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያን በገሃድ ከወገኑላት አገሮች መካከል አንዷ ናት።
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by the people of… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በበጎ ጎኑንና በስጋት ከፍለው መግለቻቸው… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to local companies, would bring… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism