በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ዶላር ዩሮና ፓውንድ ተያዘ – 44 ሚሊየን ብር


መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ወደ ሞያሌ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ዶላር ዩሮና ፓውንድ ተያዘ።

በህብረትሰቡ ጥቆማና በሻሸመኔ ፖሊስ መምሪያ ክትትል የተያዘው የውጭ ምንዛሬ ወደ 44 ሚሊየን ብር ነው።

በዚህም 473 ሺ 770 ዶላር፣ 393 ሺ 660 ዩሮ እና 39 ሺ 675 ፓውንድ ኮድ 2 አአ B 67186 በሆነ ፒካፕ መኪና ውስጥ የተያዘው።

በሻሸመኔ ከተማ 05 በተለምዶ ሞቢል በሚባለው አካባቢ ተሽከርካሪ በረቀቅ መንገድ የውስጠኛው የፋብሪካ ብሎን ተከፍቶ የተደበቀው ገንዘብ በፖሊስ ክትትል በተደረገ ፍተሻ ነው ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር ነው የተያዘው።

የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮምኒኬሽን ዲቪዥን ሀላፊ ኢንስፔክተር ታምራት አበበ ለፋና እንደገለጹት÷በተሽከርካሪው ላይ ተጨማሪ ፍተሻ ተደርጎ የተገኘው ገንዘብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸምኔ ሪጅን እየተቆጠረ ነው።

ፖሊስ የተያዘው ገንዘብ ምንጭና አላማውን በተደራጀ የምርመራ ቡድን እያጣራ ነውም ብለዋል ።

ህብረተሰቡ ህገወጦችን በማጋለጥ ሀገርን ለመጉዳት የተሰማሩ ሀይላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ከጸጥታ አካላት ጋር እያደረገ ያለው ትብብርብ የሚበረታታና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው መሆኑን የኤፍቢሲ ዘገባ ያሳያል።

Leave a Reply

%d bloggers like this: