በኢትዮጵያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብና የቪዛ እገዳ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንደሌለው ያስታወቁት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አዲስ አበባ መግባታቸው ታወቀ። ሴናተሩ አዲስ አበባ መግባታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ናቸው በማህበራዊ ገጻቸው ያስታወቁት። በዲፕሎማሲው በአሜሪካ ኢትዮጵያን የሚደግፉ ሴናተሮች ድምጽ የሚሰማበትና የሚሰባሰብበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው።
‘‘የኢትዮጵያውያን ወዳጅ የሆኑትን፣ የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር፣ ጂም ኢንሆፍን ወደ ሁለተኛው ቤትዎ ኢትዮጵያ እንኳን ደኅና መጡ’’ ሲሉ በፊስ ቡክ ገጻቸው አክብሮት ሰጥተዋቸዋል።
“በቁርጥ ቀን ከእውነት ጋር አብረው ስለሆኑ እናመሰግናለን” በሚል የኢትዮጵያ አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል የአድናቆትና የምስጋና ደብዳቤ የላከላቸው ጂም ኢንሆፍ፣ በተለየ የመጡበት ምክንያት ባይገለጽም፣ በወቅታዊ ጉዳዮች እንደሚመክሩ ታውቋል።
የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግን በተደጋጋሚ በተሰጠው ስም ” አሸባሪ ቡድን” እያሉ የጠሩት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አስራ አራት ደቂቃ የፈጀ ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል። መዕቀቡ ይፋ በሆነ ማግስት ንግግር ያሰሙት ሴናተሩ ዲስኩራቸውን ሲጨርሱ፣ “የኢትዮጵያን ታሪክ በመረዳትና በማክበር” በማለት ያላቸውን ክብር ገለጹ። አስከተሉና ” ኢትዮጵያዊያን ወዳጆቼ ” ሲሉ ወንድማዊ ልሳን ተሞልተው ዳግም ክብር ሰጡ። ኢትዮጵያን ለማንበርከክ ባደሙትና ባሴሩት ፊት ሆነው ” ወንድሜ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ” አሉና “አብረንዎት ነን” የሚል ማረጋገጫ ሰጡ።
ይህን ባሉ ቀናት ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ሲንሆፍ “አሸባሪው ህወሓት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ደስተኛ አልነበረም፤ ከመንግስትም ጋር አብሮ ለመስራት እንቢተኛ ሆነ፤ ተቃውሞውንም አገሪቷን በማወክ መግለጽ ጀምሮ ነበር፤ በዚህ የህወሓት ሽብር የተሞላበት አካሄድ የተነሳ የኢትዮጵያ ፓርላማ አሸባሪ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፤ ይህንን አሸባሪ ድርጅት የአሜሪካ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት እኩል ማየት መጀመሩ ስህተት ነው፣ ተቀባይነት የለውም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ጥረት እያደረጉ ነው” ብለው ነበር።
እሳቸው ይህን ከማለታቸው በፊት ኢትዮ 12 ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ የአውሮፓ ዲፕሎማት ለጊዜው መዘርዘር የማይፈልጉት ነገር ግን እየተሰራ ያለ ስራ መኖሩን መግለጻቸው ይታወሳል። ከዛም በቀጣይ ኢትዮጵያዊያን ሲንሆፍን ባለቸው መድረጅና አውድ ሁሉ እንዲያመሰግኑ አሳስበው ነበር።
ሲንሆፍ ወደ አገራቸው ሲመለሱ እሳቸውን መስል ሴናተሮችን በማሳመንና በማሰባብሰብ ትርጉም ያለው ስራ ይሰራል ብለው እንደሚያምኑ ዲፕሎማቱ በግርድፍ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። አንዳንድ አላማቸውን የሳቱ የተቃውሞ አግባቦች አገር ስለሚጎዳ ህዝቡ እንዲጠነቀቅ፣ ሲያጋጥማቸውም በማውገዝ ኢትዮጵያን እንደማይወክል በመግለጽ መታገል እንደሚገባም አመልክተዋል።
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው” የሚለው የዋዜማ… Read more: “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In its… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council