May be an image of standing and outdoors

ግንቦት 23 ቀን 2013 – የዚች ጥቁር አፈር ውበትና ጌጦችዋናው የፍልሚያ ቀናት ተናፈቀ

።ምክንያቱም አካል ብቃት ፣ ተኩስ ፣ ሠልፍ ፣ በተለያዩ ኪሎ ሜትሮች ሩጫዎችና ጉዞዎች ፣ ችግርን መቋቋም ልምምዶች ስለተሰጡ ሁሉም ሰልጣኝ በአካልም በመንፈስም ጠነከረ ። ስለዚህ ብቃቱን በተግባር የሚያሳይበትን ሰኣት ሰልታኝ በጉጉት ናፍቃል ፡፡

ለውጊያ ዝግጅት የሚሰጡ ስልጠናዎች ድጋፍ ሰጪዎችንና በየደረጃው ያሉ አመራሮችንም ያጠቃልላል። ግዳጅን መሬት ላይ ከሚቀበሉ ጓድ መሪዎች ጀምሮ ታክቲካል ፣ ኦኘሬሽናል እያለ እስከ ላይ የዘለቀ ነበረ።ለመደበኛ ውጊያ የሚካሄዱ ስልጠናዎች ከነፍስ ወከፍ ጀምረው የጓድ ፣ የመቶ ፣ የሻምበል ፣ የሻለቃ ፣ የብርጌድ ፣ ክፍለ ጦር እያለ የጥምር ውጊያ ልምምድ ድረስ ዘልቋል።

በየክፍሉ የሚደረጉ ስልጠናዎች በድጋፍ ሰጪ ሙያተኞች፣ የከባድ መሣሪያ ምድብተኞች፣ አስተኳሾች፣ መሐንዲስና መረጃዎች፣ በሁሉም የሎጅስቲክና አስተዳደር ዘርፎች በተለያዩ የተቋሙ አቅም ግንባታ ማዕከላት ተካሂደው ተጠናቋል። ውጤት ተገምግሞ ለክፍሎች በየደረጃው ደረጃ ተሰጥቷል።

ደረጃ ሲባል እንደ ሲቪል ተቋማት ሐላፊነትም ሆነ ደመወዝ ለመጨመር የሚያግዝ ዓይነት አይደለም። ለአብነት በማጥቃት የውጊያ ልምምድ በሁሉም መሥፈርት አንደኛ የሆነ ክፍል ለግዳጅ ቅድሚያ ይሰጠዋል ተብሎ ይታሰባል። በርካታ ጊዜም በገሃድ ታይቷል።የሚሰጠው ግዳጅ ምሽግ ሰበራ ሊሆን ይችላል።

ምሽግ ሰበራ ስሙ እንደሚያመለክተው ተመቻችቶ የተቀመጠ ጠላት ላይ ጥቃት ፈፅሞ፣ ቦታውን ከጠላት አስለቅቆ በወገን ቁጥጥር ሥር ማድረግ ነው። ( የተራኪው መቸት ሰሜን የሀገራችን ክፍል ነው።)እንደዚህ በተፈጥሮ በመሠናክል የተሞላ መሬት ላይ ኮንክሪት ምሽግ ተሠርቶ ዙሪያውን በተዘራ ፈንጂ ታጥሮ አመቺ የሆኑ ቦታዎች ላይ የቡድን መሣሪያዎች ተወድረው ይጠብቃሉ።

የፈንጂ አጠማመዶቹ ከውጊያ በኋላ እንደ ታየው ለእግረኞች መጠጊያ የሆኑ ሸጦች ላይ ፀረ-ሰውና ፀረ- ታንክ ወይም ፀረ_ተሽከሪካሪ በጥምረት ይጠመዱ ነበር። ወታደሩ ፀረ -ሰው የሆነውን ሲረግጥ ፀረ ተሽከርካሪ አብሮ ይነሳል። ያኔ ሊፈጠር የሚችለውን ወታደር ለሆነ ሰው መገመት አስቸጋሪ አይሆንም።

በጋለ የሀገር ፍቅር ስሜት፣ በጠላት ተደፈረች የተባለችውን ሀገራቸውን ነፃ ለማውጣት በየአውደ ውጊያው የተሰለፉ አባላት ስሜት ደግሞ የሚያስገርም ነበር።አብዮታዊ ውድድሩ መቼም ከአእምሮ አይጠፋም። ሁልጊዜ የሚተጉት አንደኛ ለመሆን ነበር። አንደኛ ለመሆን ላባቸውን ከሰውነታቸው ጨርሰው የሚተጉት ለሽልማት አልነበረም። ቅድሚያ ግዳጅ ተቀብሎ የጠላት ምሽግ ለመስበር፤ እነሱ ሞተው የሀገራቸውን ውርደት የጓዶቻቸውን ሞት ለማስቀረት ነበር።አጋጣሚ ሆኖ አንደኛ መውጣት ያልቻሉ ክፍሎች አበላትና አመራር ስሜታቸው ክፉኛ ይጎዳል።

እራት የመብላትም ሆነ የትም የማይገኘውን የወታደር ቤት የጥቂት የእረፍት ጊዜያት ጨዋታ የመጫወት ፍላጎት አይኖራቸውም። ወደ ሠፈራቸው ሲመለሱ እንደ ወትሮው በጭፈራና ሞራል ላይሆን ይችላል። በወታደራዊ የሠልፍ ጉዞ በፀጥታ የሚገሰግሱበትን ወቅት መኮንኑ ደጋግሞ አይቷል።ግንባር ቀደም የሆኑት ደግሞ አይጣል። የተለያዩ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች፤ የዚች ጥቁር አፈር ውበትና ጌጦች ዘመንና ጭፈራ ምድሩ ይደበላለቃል። ይወለድና እንከፍ እንከፉጋን ይሸከማል ከነ ድፍድፉ…. ፈሪ ላይ ይወረዳል። ጀግና ይወደሳል።

በወቅቱ በተደጋጋሚ ይነሱ የነበሩ ጥያቄዎች የመከላከያ ህገ ደንብ ላይ የተቀመጡ የሠራዊቱ መብቶችና ጥቅማ ጥቅሞች አልነበሩም። በጋ በሐሩር – ክረምት በዝናብና ቁር በላስቲክ ተጠልሎ፣ የእረፍት ጊዜ ከተገኘ ደረቅ ላስቲክ አንጥፎ፣ ድንጋይ ተንተርሶ እየደረ በስልጠና ወቅት ችግርን ለመቋቋም ሲባል በቀን አንዴ ውሃና እህል እየቀመሰ የሠራዊቱ ጥያቄ ሌላ ነበር።ለዘመናት በአበው ደምና አጥንት በነፃነት የኖረችው ሀገርህ ተደፍራለች።

ከሠንደቋ ሳትወርድ የኖረችው አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ብሔራዊ አርማ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል ስለተባለ ጥያቄው ሁሉ ለምን አንዋጋም? ዝግጅቱ በዛ ። አባቶቻችን ነፃ ሀገር ያስረከቡን በተራዘመ ወታደራዊ ዝግጁነት ነበር እንዴ? የሚል ይዘት ያለው ነበር።

ሻለቃ ፈይሳ ናኔቻ ከመከላከያ ፌስ ቡክ የተወሰደ


Leave a Reply