የአገር መከላከያ ሰራዊት ለምርጫና ለሁለለተኛው የህዳሴ ግድብ ሙሌት እንከን እንዳይፈጠር በጥብቅ ዝግጅት ማድረጉ ተገለጸ። የምድርና የአየር ሃይል አዛዦች በተደጋጋሚ ይህንን ቢሉም ዛሬ በድጋሚ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ይህንኑ አጠንከረው አስታውቀዋል። በምርጫ ዙሪያ ወንጀል የሰሩም ተያዘዋል።
የመከላከያ ሚኒስቴርም ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት የተናገሩት ለአሐዱ ሬዲዮ ነው። 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የመከላከያ ሰራዊት ዝግጅት አድርጓል ነው ያሉት።
” በመላው ሀገሪቱ ወንጀለኛን አድኖ ለመያዝ የመከላከያ ሰራዊቱ ዝግጁ ነው” ሲሉ ያስታወቁት ኮሎኔሉ በተለይ ስለተደረገው ዝግጅት ማብራሪያ አልሰጡም።
ኢትዮጵያ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ለማካሄድ ቀን መቁረጧ ይታወቃል፡፡ ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ዝግጅት እያደረጉ ስለመሆኑ በየፊናቸው ከሚሰጡት መረጃ ለመረዳት ተችሏል። ብልጽግናም ስብሰባውን ሲያጠቃልል ምርጫው መሰላማዊ እንዲጠናቀቅ፣ ሁለተኛው የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ አቋም መያዛቸው ይታውሳል። ላለፉት አራት ወራት ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ የፖሊስ አባላት፣ በልዩ ልዩ ስልታዊ ተግባር የሰለጠኑ፣ ከፖሊስ ኮሌጅ የወጡ መኮንኖች በተከታታይ ሲመረቁ በክልል ደረጃም ሰፊ ቁጥር ያለው ሃይል ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።
በለኢላ የምርጫ ዜና የምርጫ ቅስቀሳ ባነር ወይም የምርጫ ምልክት በመቅደድ የተጠረጠሩ 22 ግለሰቦችን በመያዝ እያጣራሁ ነዉ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን አስታወቋል።
ስድስተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ እየሰራሁ ነዉ ያለዉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን የፖለቲካ ፓርቲዎች የቅስቀሳ ባነሮችን ቀደዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ 22 ግለሰቦችን መያዙን ገልፃል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ እንደተናገሩት በከተማዋ ስድስተኛዉን ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የተሰቀሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባነርን በመቅደድ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን መያዙን ገልፀዉ ከነዚህ ዉስጥ በኮልፌ ቀራንዮ አንድ ግለሰብ የ5 ወር እስራት ተፈርዶበታል ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ኮማንደሩ አክለዉም የዘንድሮዉ ስድስተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ከዚህ በፊት ከተካሄዱ አምስት ሀገራዊ ምርጫዎች የተሻለ እና የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ከዚህ ቀደም ከነበሩ ምርጫዎች በተሻለ የምርጫ ምልክታቸዉን በነፃነት እያስተዋወቁ ነዉ ሲሉ ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by the people… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ ከዚህ… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በበጎ ጎኑንና በስጋት ከፍለው… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to local companies, would… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism
- መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀMore stories “…በሌብነት የሚጠረጠሩ አመራሮች ከእንግዲህ ቦታ የላቸውም”March 25, 2022 አየር መንገድ ለመንገደኞች ጥንቃቄ ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ… Read more: መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀ