ከአማራ ክልል ከተለያዩ ዞኖች በደላሎች ተታለው በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር ለመውጣት የሞከሩ 60 ወጣቶች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የባቲ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሃመድ አሊ ለኢዜአ እንደገለጹት ወጣቶቹ ጨለማን ተገን አድርገው ከሃገር ለመውጣት ሲሞክሩ ትላንት ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባቲ ከተማ ተይዘዋል ።
ወጣቶቹ በህገ ወጥ መንገድ ወደ አረብ ሀገር ለመውጣት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 43619 አአ በሆነ የጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪ ተሳፍረው ከደጋን መስመር ወደ አፋር በመጓዝ ላይ እንዳሉ በከተማው ቀበሌ 03 ቀርሳ ፍተሻ ጣቢያ ላይ መያዛቸውን ተናግረዋል ።
ወጣቶቹ ከ17 እስከ 28 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ መሆናቸውን ጠቁመው ከወጣቶቹ መካከል ሶስቱ ሴቶች እንደሆኑ ገልጸዋል።
እንደ ዋና ኢኒስፔክተሩ ገለጻ ወጣቶቹ ከሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሽዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች በህገ ወጥ ደላሎች ተታለው የተሰባሰቡ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ወጣቶቹን በህገወጥ መንገድ ከሀገር ለማሶጣት በታሰበ ወንጀል ተሳትፎ እንዳላቸው የተጠረጠሩ አሽከርካሪውን ጨምሮ ሁለት ግለሰቦች ተሸከርካሪውን አቁመው መሰወራቸውን ተናግረዋል ።
ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል መጀመሩን አመልክተዋል ።
ወጣቶቹን በሂደት ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ ከወዲሁ ስራዎች መጀመራቸውንም ጠቁመዋል።
ዜጎች ጫካ ለጫካ ጭምር በእግራቸው በመጓዝ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገራት ለመውጣት በሚያደርጉት ሙከራ ለሞት፣ ለአካል ጉዳትና ለመደፈር እየተጋለጡ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ድርጊቱ በተደራጀ አግባብ የሚፈፀም በመሆኑ ለመከላከል አስቸጋሪ እንዳደረገው ያመለከቱት ዋና ኢኒስፔክተሩ የባለድርሻ አካላት ጠንካራ ትብብር በመፍጠር ድርጊቱን ለመከላከል ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ። via (ኢዜአ)
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች ለዓመታት… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ