በአዲስ አበባ ከተማ የጎዳና ተዳዳሪ በመምስል የሽብር ተግባር ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ጨምሮ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ከ900 በላይ ግለሰቦች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ። የተሰወኑት ግለሰቦች የጎዳና ተዳዳሪ በመምስል የሽብር ተግባር ለማስፈፀም ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም ተመክቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ የጎዳና ተዳዳሪ በመምስል የሽብር ተግባር ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ከ900 በላይ ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅሶ ኢዜአ ነው የዘገበው።
ኮሚሽኑ ከህዝብ የደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በጥናት ላይ በመመስረት በሰባት ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 20 ቦታዎች ላይ ግንቦት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ባከናወነው ኦፕሬሽን ቋሚ አድራሻ የሌላቸውና በዋና ዋና አደባባዮች እና በምሽት በሰዋራ ቦታዎች የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ 999 ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል አብዛኞቹ ማስቲሽና ቤንዚን በመጠቀም እራሳቸውን በማደንዘዝ የትራፊክ እንቅስቃሴዎችን ሲያውኩ እንደነበር በተለይ ደግሞ የትራፊክ መብራት ካስቆመው ተሽከርካሪ ላይ ስፖኪዮ ገንጥለው እንደሚወስዱ፣ ከአሽከርካሪ ወይም ከተሳፋሪ ላይ ሞባይል ስልክ፣ የአንገት ሃብል፣ ቦርሳ እና ልዩ ልዩ ንብረቶችን ቀምተው እንደሚሰወሩ ማረጋገጡን ገልጿል።
በተለይም ሴት አሽከርካሪዎች አደጋ ሳያደረሱባቸው አደጋ እንዳደረሱባቸው በማስመሰልና በማዋከብ ገንዘብ እንደሚቀበሉ፣ የትራፊክ አደጋ ሲያጋጥም ልዩ ልዩ ስልቶችን በመጠቀም ንብረቶችን እንደሚሰርቁ በጥቅሉ ትኩረታቸውን በዋና ዋና አደባባይ የትራፊክ መብራት በያዘው ተሽከርካሪ ላይ አድርገው ወንጀል ሲፈፅሙ እንደነበር ኮሚሽኑ ከህዝብ ከደረሰው ጥቆማና ባደረገው ጥናት ማረጋገጡን አመልክቷል።
ግለሰቦቹ በምሽት የቅሚያ ወንጀል ሲፈፅሙ እንደነበር መረጋጋጡ በተለይ ደግሞ የውጪ ሀገር ዜጎችንና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡን በማዋከብና በማስጨነቅ በከተማዋ መልካም ገፅታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሲፈጥሩ እንደነበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የተሰወኑት ግለሰቦች የጎዳና ተዳዳሪ በመምስል የሽብር ተግባር ለማስፈፀም ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ መገኘታቸውንም ኮሚሽኑ ገልጿል።
በከተማዋ የሚስታወሉ መሰል ስጋቶችን ለመቀነስ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረገው ህግን የማስከበር ተግባርና በተጠርጣሪዎቹ ላይ እየተደረገ ያለው ምርመራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል፣ በወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት ግለሰቦች መካከል እንደ ድርጊታቸው መጠንና ስፋት በህግ የሚጠየቁት እንተጠበቀ ሆኖ እድሜያቸው አነስተኛና በወንጀል ድርጊት ተሳትፏቸው እጅግ ቀላል የሆኑት ደግሞ ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ጋር በመቀናጀት የተሃድሶ ስልጠና እንደሚሰጣቸው ፖሊስ ገልጿል፡፡
ኮሚሽኑ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ተግባሩን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ነዋሪው ለሰላም ስጋት የሆኑ ግለሰቦችን በመጠቆምና ማስረጃ በመሆን ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡
- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”“የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም!” በሚል ርዕስ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ… Read more: የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”
- በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!More stories በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!April 19, 2024 ካለፈ በሁዋላ … እንዳይቆጨን ቁ 2April… Read more: በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country,… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership