በቀጣይ አምስት ዓመታት 500 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት አቅዶ እየሰራ ያለው የአዲስ አበባ አስተዳደር የአንድ መቶ ሺህ ቤቶች ግንባታ ለማከናወን ከስምምነት የደረሰ መሆኑንን ይፋ አደረግ።
በዚሁ መረሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ አመት ውስጥ 100 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት መፈረሙን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።ስምምነቱን የፈረሙት በየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤና ፕሮፐርቲ 2000 ደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ተወካይ ናቸው።
ለግንባታው 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ወጪ የሚደረግ ሲሆን፥ ሙሉ ወጪው በኩባንያው እንደሚሸፈን ተመልክቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለግንባታ የሚያስፈልገውን መሬት ያቀርባል፡፡
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በ30 አመታት ክፍያ ለተጠቃሚዎች የሚተለለፉ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ የተቀናጀ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ትብብር አካል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በአንድ በመቶ አነስተኛ ወለድ ለህብረተሰቡ የሚተላለፉ ሲሆን፥ በቀጣዮቹ አምስት አመታት ውስጥም 500 ሺህ ቤቶች እንደሚገነቡም አስተዳደሩ እግረመነገዱን አስታውቋል።
ለመኖሪያ ቤቶቹ በመሃል ከተማ የመልሶ ማልማት በሚከናወንባቸው እና በአይሲቲ ፓርክ አካባቢ ቦታ መለየቱም በስምምነቱ ወቅት ተነስቷል፡፡
- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”“የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም!” በሚል ርዕስ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ባሰራጨው… Read more: የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”
- በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!More stories የባህር በር ህልውናችን!! አብይ አህመድ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል” ሲሉ አወጁDecember 30, 2023 አዲሱ ሚኒስትር… Read more: በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership