ይህ ታሪክ ያስታወሰኝ “ዶላር እናዘንባለን” ሲሉ የነበሩ መታሰራቸውን ስሰማ ነው። ሮጠው ካከማቹት መካከል ለነዚሁ መንታፊዎች አስረክቦ ብቻውን ሲያወራ የነበር ሰው ታወሰኝ። እሱ ብቻ አይደለም አንድ የሩጫ ታዋቂ አሰልጣኝ እዚሁ ዶላር አውራጅ ቤት እንዴት እንዳጠቧቸው አስምለው ነግረውኝ ነበር።
እኙሁ አባት አሰልጣኝ በሚቀርቧቸው ሰዎች ተጀንጀነው፣ ዶላር እንዲዘንብላቸው ሜርኩሪ ግዙ እየተባሉ ነበር የተሸለሙትን ያራገፉት።
አንድ ካሜሩናዊና ኢትዮጵያዊ ዶላር እናባዛለን በሚል መያዛቸውን ፖሊስ ይፋ ቢያደርግም ገና በምርመራ ላይ በመሆናቸው እንዴትና በምን ዘዴ እንደሚያጭበረብሩ አላስታወቀም።
የዚህ ዓምድ አዘጋጅ ቀደም ሲል ከተዘረፉ እንደሰማው ከሆነ ዶላር እንዲወርድላቸው የሚፈልጉ “ሜርኩሪ ግዙ” ይባላሉ። ይህን ለግለሰብ የተከለከለ ውድ ንጥረነገር የሚሸጠው ሰው ደግሞ የዚሁ የሌብነት ኔትዎርክ አባል ነው። ነገሩን እውነት ለማስመሰል በሰው ሰው ነው የሚገኙት።
አቅራቢዎቹ አረቦች ወይም ሌላ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው እንዲሆኑ የሚደረገው እምነት ለመጨመር ነው። በዚህ ሂደት ዶላር እንዲዘንብላቸው የሚቋምጡ ይህ ኔት ዎርክ የመለመላቸው ሃብታሞች ” እኔ ይህን ያህል አገኘሁ” በማለት ልክ እኚህን አሰልጣኝ እንዳደረጉት ይቀሰቅሳሉ።
ምንም ያልጎደለባቸው ሰዎች ያላቸውን እንዳይበሉ ንብረት ጭምር እያስያዙ ዶላር እንዲዘንብላቸው ምንነቱን የማያውቁትን ሜርኩሪ መሳይ ነገር እየሸመቱ እንደ ቃሊቻ ዶላር አወርዳለሁ እሚለው ሰው ዘንዳ ይሄዳሉ። “ሜርኩሪ ነው” ተብል የተሰጣቸውን ቅመም አቅርበው የሚሆነውን ይጠብቃሉ። አውራጁ ሜርኩሪ የሚባለውን ይሁን ሌላ የማይታወቅ ነገር እያጨሰ ትንሽ ዶላር ያሳይና / የተቀረው ፎርጂድ ነው/ የሚጨሰው ሜርኩሪ እንዳለቀ በመናገር ሌላ እንዲያቀርቡ ያዛል።
ድራማው የሚሰራበት ክፍል፣ የሚሰራበት የቅንብር ደረጃውና፣ ከመንፈሳዊ ዛር ጋር የሚመሳሰልበት ጥበብ የሚያማልል በመሆኑ ባለጉዳይ ሜርኩሪ የተባለውን ባዕድ ነገር ለመግዛት ይሮጣል ወይም ትሮጣለች። በዚህ ስልት ሃብታቸውን ጨርሰው ያጨበጨቡ በርካታ ናቸው። ደላሎቹ ሃብታሞች አውቀው እነሱም አብረው እንደከሰሩ ሆነው ሃዘን ይቀመጣሉ። ፖሊስ ምርመራውን በደንብ ከያዘው ብዙ ጉድ ይወጣዋል። ኢዜአ የዘገበው እንደሚከተለው ነው።
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ዶላር እናባዛለን በማለት የማጭበርበር ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦች በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ‘ሲኤምሲ’ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ዶላር እናባዛለን በማለት የአካባቢውን ህብረተሰብ ሲያጭበረብሩ የነበሩ ካሜሮናዊና ኢትዮጵያዊት በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ኢንተለጀንስ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ሰዓት ዶላር እናባዛለን በማለት ለማጭበርበሪያ የሚጠቀሙባቸው ሁለት ካርቶን ዶላር የሚመስል ወረቀትና ሁለት ጠርሙስ ኬሚካል ይዘው መገኘታቸው ታውቋል፡፡ ከማህበረሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ኢንተለጀንስ ሁለቱንም ግለሰቦች በቁጥጥር ስር በማዋል በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡
እንደነዚህ አይነት ህገ-ወጥ ተግባር በሚፈጽሙ ግለሰቦች ዙሪያ ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ፖሊስ ጥሪ ማቅረቡን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በማህበራዊ ገፁ ይፋ አድርጓል፡፡
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ በሀገራችንም የሽግግር ፍትህ አስፈላጊነት… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና ፊርማ የተሰራጨው… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሮማናት አደባባይ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- የዜናው ሰም፣ ወርቅና “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የትህነግ ዜናውን አጣጣለለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው” የሚለው የዋዜማ ዜና ፖለቲካውን ለሚረዱ የዜናው… Read more: የዜናው ሰም፣ ወርቅና “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የትህነግ ዜናውን አጣጣለ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In its statement, the Council underscored… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council