የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም የነበሩትን ጀነራል ሰዓረ መኮንን እና ጓደኛቸውን ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራን በመግደል ወንጀል ተከሶ የነበረው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ጥፋተኛ መባሉን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ገልጸ።
ውሳኔውን አርብ ግንቦት 27/2013 ዓ.ም የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ሦስትኛ የጸረ ሽብርና የሕገመንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ከሁለት ዓመት በፊት በአዲስ አበባ በጀነራል ሰዓረ መኮንን መኖሪያ ቤት ውስጥ ግድያውን በመፈጸም የተከሰሰው አስር አለቃ መሳፍንት ጉዳይን የተመለከተው ችሎት ተከሳሹ የሰፊ የወንጀል ድርጊት አካል ሆኖ ወንጀሉን መፈጸሙን አመልክቷል።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባወጣው መረጃ መሰረት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈበት ተከሳሹ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በአማራ ክልል የቀድሞ የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ በነበሩት በብርጋዲየር ጀነራል አሳምነው ጽጌ በተመራ ሰፊ ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ሴራ ውስጥ ተሳታፊ እንደነበር አመልክቷል።
በዚህም ተከሳሹ በዚሁ ሴራ ውስጥ የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ኤታማዦር ሹም የነበሩትን ጀነራል ሰዓረ መኮንን እንዲገድል እንዲሁም ሌላ ግለሰብ ደግሞ ምክትል ኤታማዦር ሹም የነበሩትን ጀነራል ብርሃኑ ጁላን እንዲገድል ተልዕኮ ሰጥቷቸው እንደነበር ተገልጿል።
ዐቃቤ ሕግ እንዳለውም ግንቦት 15/2011 ዓ.ም ምሽት ሦስት ሰዓት ላይ አስር አለቃ መሳፍንት ባሕር ዳር ከተማ የተፈፀመውን ጥቃት ሲሰማ “ተኩሶ ጀነራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራን በመግደል ለማምለጥ ሲሞክር ተከቦ በቁጥጥር ስር ውሎ” ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱን ገልጿል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ሦስትኛ የጸረ ሽብርና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በክሱ ላይ የቀረበውን የግራ ቀኝ ክርክርና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ ነበር ተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ በመስጠት የቅጣት አስተያየት ለመስማት ለሰኔ 11/2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
ሰኔ 15/2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የተገደሉት ኤታማዦር ሹሙ፤ ለረጅም ዓመታት በኃላፊነቱ ላይ የቆዩትን ጄነራል ሳሞራ የኑስን ተክተው የአገሪቱ ሠራዊት አዛዥ ከሆኑ ብዙም አልቆዩም ነበር።
በጥቃቱ ወቅት በአጋጣሚ በጄነራሉ ቤት የተገኙት ጓደኛቸውና የቀድሞ የሠራዊቱ አባል ጀነራል ገዛኢ አበራም በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።
ዐቃቤ ሕግ የዚሁ ሴራ አካል ነው ባለው ድርጊት በዚያው ዕለት ምሽት ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ በባሕር ዳር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩትን ዶ/ር አምባቸው መኮንንና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮቻቸው ላይ ግድያ መፈጸሙ ይታወሳል። BBC amaharic
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by the people of Somaliland in a… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረቡ… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በበጎ ጎኑንና በስጋት ከፍለው መግለቻቸው ላይ አክለዋል። በኢትዮጵያ… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to local companies, would bring a new dynamism… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism
- መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀMore stories ብልጽግና “ተላላኪ” ያላቸውን ሊመነጥር ነው፤ መረጃው ተጠናቋልAugust 14, 2022 ህጋዊ መስፈርት ሳያሟሉ አክሲዮን ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ሊከሰሱ ነውJune 22,… Read more: መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀ