ታዋቂው ናይጄሪያው የሃይማኖት ሰባኪ ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሽዋ በትናንትናው ዕለት ህይወታቸው አለፈ።
ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ወይም በተለምዶ ቲቢ ጆሽዋ ማረፋቸውንም ይፋዊ በሆነው ፌስቡክ ገፃቸውም ላይ “አምላክ አገልጋዩን ቲቢ ጆሹዋን ወደቤቱ ወስዷል” በሚልም ሰፍሯል።
ስመ ጥር የሆኑት የኢቫንጀሊካን ሃይማኖት ሰባኪ በትናንትናው ዕለት የቤተክርስቲያን ፕሮግራማቸውን ከጨረሱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምሽት ላይ ማረፋቸው ተገልጿል።
በተከታዮቻቸውም ዘንድ የነብይነትን ማዕረግ ያገኙት ቲቢ ጆሽዋ በአህጉሪቷ ውስጥ ተፅእኖ መፍጠር ከቻሉ የኢቫንጀሊካል ሰባኪዎች አንዱ ናቸው ። በአፍሪካ ውስጥም ያሉ ታዋቂ ፖለቲከኞችንም በተከታይነት ማፍራት ችለዋል።
ዘ ሲናጎግ፣ ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽንስ (የሁሉም ህዝቦች ቤተ ከርስቲያን) የሚባል የእምነት ተቋምን የመሰረቱ ሲሆን እንዲሁም በቴሌቪዥንም በሚያደርጓቸው ስብከቶችም በርካታ የእምነቱ ተከታይ ምዕመናንን ማፍራት ችለዋል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም በናይጄሪያ መዲና ሌጎስ የሚያደርጓቸውን ሳምንታዊ የአገልግሎት ስርዓት ይከታተላሉ።
በቅርቡ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተመልካች ያለው የዩቲዩብ ገፃቸው ከጥላቻ ንግግር ጋር በተያያዘ በሚያዝያ ወር ታግዶ ነበር።
ቅሬታውን ያቀረበው አንድ ገለልተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የኢቫንጀሊካን ሐይማኖት ሰባኪውን ሰባት የሚሆኑ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች ከተመለከተ በኋላ በሁሉም ላይ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያንን ለመፈወስ ጸሎት ሲያደርጉ ነበር ብሏል።
ፌስቡክም ቢሆን የሐይማኖት ሰባኪውን የቲቢ ጆሽዋ አንድ ቪዲዮ አጥፍቶታል። በቪዲዮው ላይ ቲቢ ጆሽዋ “እርኩስ መንፈስ” ለማስወጣት በማለት አንዲት ሴትን በጥፊ ሲመቱ ይታያል።ሐይማኖት ሰባኪው በበኩላቸው የዩቲዩብን ውሳኔ በመቃወም ቅሬታቸውን አሰምተው ነበር።
በ57 አመታቸው ያረፉት ቲቢ ጆሽዋ በአውሮፓውያኑ 2011 ፎርብስ ላይ በወጣው መረጃ መሰረት የሃብት መጠናቸው ከ10-15 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ይገመታል። BBC Amharic
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰምና ወርቅና የትህነግ ማስተባበያለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው” የሚለው የዋዜማ ዜና… Read more: “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰምና ወርቅና የትህነግ ማስተባበያ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In its statement,… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council
- ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉየፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ የ3 ግለሰቦችን ጊዜ ቀጠሮ መዝገብን… Read more: ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉ