ታዋቂው ናይጄሪያው የሃይማኖት ሰባኪ ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሽዋ በትናንትናው ዕለት ህይወታቸው አለፈ።
ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ወይም በተለምዶ ቲቢ ጆሽዋ ማረፋቸውንም ይፋዊ በሆነው ፌስቡክ ገፃቸውም ላይ “አምላክ አገልጋዩን ቲቢ ጆሹዋን ወደቤቱ ወስዷል” በሚልም ሰፍሯል።
ስመ ጥር የሆኑት የኢቫንጀሊካን ሃይማኖት ሰባኪ በትናንትናው ዕለት የቤተክርስቲያን ፕሮግራማቸውን ከጨረሱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምሽት ላይ ማረፋቸው ተገልጿል።
በተከታዮቻቸውም ዘንድ የነብይነትን ማዕረግ ያገኙት ቲቢ ጆሽዋ በአህጉሪቷ ውስጥ ተፅእኖ መፍጠር ከቻሉ የኢቫንጀሊካል ሰባኪዎች አንዱ ናቸው ። በአፍሪካ ውስጥም ያሉ ታዋቂ ፖለቲከኞችንም በተከታይነት ማፍራት ችለዋል።
ዘ ሲናጎግ፣ ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽንስ (የሁሉም ህዝቦች ቤተ ከርስቲያን) የሚባል የእምነት ተቋምን የመሰረቱ ሲሆን እንዲሁም በቴሌቪዥንም በሚያደርጓቸው ስብከቶችም በርካታ የእምነቱ ተከታይ ምዕመናንን ማፍራት ችለዋል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም በናይጄሪያ መዲና ሌጎስ የሚያደርጓቸውን ሳምንታዊ የአገልግሎት ስርዓት ይከታተላሉ።
በቅርቡ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተመልካች ያለው የዩቲዩብ ገፃቸው ከጥላቻ ንግግር ጋር በተያያዘ በሚያዝያ ወር ታግዶ ነበር።
ቅሬታውን ያቀረበው አንድ ገለልተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የኢቫንጀሊካን ሐይማኖት ሰባኪውን ሰባት የሚሆኑ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች ከተመለከተ በኋላ በሁሉም ላይ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያንን ለመፈወስ ጸሎት ሲያደርጉ ነበር ብሏል።
ፌስቡክም ቢሆን የሐይማኖት ሰባኪውን የቲቢ ጆሽዋ አንድ ቪዲዮ አጥፍቶታል። በቪዲዮው ላይ ቲቢ ጆሽዋ “እርኩስ መንፈስ” ለማስወጣት በማለት አንዲት ሴትን በጥፊ ሲመቱ ይታያል።ሐይማኖት ሰባኪው በበኩላቸው የዩቲዩብን ውሳኔ በመቃወም ቅሬታቸውን አሰምተው ነበር።
በ57 አመታቸው ያረፉት ቲቢ ጆሽዋ በአውሮፓውያኑ 2011 ፎርብስ ላይ በወጣው መረጃ መሰረት የሃብት መጠናቸው ከ10-15 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ይገመታል። BBC Amharic
- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”“የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም!” በሚል ርዕስ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ባሰራጨው መግለጫ ትህነግን… Read more: የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”
- በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!More stories ካለፈ በሁዋላ … እንዳይቆጨን ቁ 2April 10, 2024 አብይ አህመድና ተቀናቃኝ ድርጅቶችApril 3, 2024 በዝቋላ ገዳም… Read more: በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William Ruto… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting a… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership