ታዋቂው ናይጄሪያው የሃይማኖት ሰባኪ ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሽዋ በትናንትናው ዕለት ህይወታቸው አለፈ።
ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ወይም በተለምዶ ቲቢ ጆሽዋ ማረፋቸውንም ይፋዊ በሆነው ፌስቡክ ገፃቸውም ላይ “አምላክ አገልጋዩን ቲቢ ጆሹዋን ወደቤቱ ወስዷል” በሚልም ሰፍሯል።
ስመ ጥር የሆኑት የኢቫንጀሊካን ሃይማኖት ሰባኪ በትናንትናው ዕለት የቤተክርስቲያን ፕሮግራማቸውን ከጨረሱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምሽት ላይ ማረፋቸው ተገልጿል።
በተከታዮቻቸውም ዘንድ የነብይነትን ማዕረግ ያገኙት ቲቢ ጆሽዋ በአህጉሪቷ ውስጥ ተፅእኖ መፍጠር ከቻሉ የኢቫንጀሊካል ሰባኪዎች አንዱ ናቸው ። በአፍሪካ ውስጥም ያሉ ታዋቂ ፖለቲከኞችንም በተከታይነት ማፍራት ችለዋል።
ዘ ሲናጎግ፣ ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽንስ (የሁሉም ህዝቦች ቤተ ከርስቲያን) የሚባል የእምነት ተቋምን የመሰረቱ ሲሆን እንዲሁም በቴሌቪዥንም በሚያደርጓቸው ስብከቶችም በርካታ የእምነቱ ተከታይ ምዕመናንን ማፍራት ችለዋል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም በናይጄሪያ መዲና ሌጎስ የሚያደርጓቸውን ሳምንታዊ የአገልግሎት ስርዓት ይከታተላሉ።
በቅርቡ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተመልካች ያለው የዩቲዩብ ገፃቸው ከጥላቻ ንግግር ጋር በተያያዘ በሚያዝያ ወር ታግዶ ነበር።
ቅሬታውን ያቀረበው አንድ ገለልተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የኢቫንጀሊካን ሐይማኖት ሰባኪውን ሰባት የሚሆኑ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች ከተመለከተ በኋላ በሁሉም ላይ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያንን ለመፈወስ ጸሎት ሲያደርጉ ነበር ብሏል።
ፌስቡክም ቢሆን የሐይማኖት ሰባኪውን የቲቢ ጆሽዋ አንድ ቪዲዮ አጥፍቶታል። በቪዲዮው ላይ ቲቢ ጆሽዋ “እርኩስ መንፈስ” ለማስወጣት በማለት አንዲት ሴትን በጥፊ ሲመቱ ይታያል።ሐይማኖት ሰባኪው በበኩላቸው የዩቲዩብን ውሳኔ በመቃወም ቅሬታቸውን አሰምተው ነበር።
በ57 አመታቸው ያረፉት ቲቢ ጆሽዋ በአውሮፓውያኑ 2011 ፎርብስ ላይ በወጣው መረጃ መሰረት የሃብት መጠናቸው ከ10-15 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ይገመታል። BBC Amharic
- ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡMore stories «የትህነግ የሽብር ቡድን ለማጥፋት ሁሉም በየአካባቢው እንዲዘጋጅ»October 30, 2021 BRICS አዳዲስ አባል ሀገራትን በይፋ መቀበሉን አስታወቀ፤… Read more: ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
- “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደትሰሞኑንን ለይቶለት ይፋ ሆነ እንጂ ውስጥ ውስጡን የጦርነት እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር መረጃዎች ከበቂ በላይ ነበሩ። ለዚህም ይመስላል ጠቅላይ… Read more: “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደት
- የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይየ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እግሮቹ ቆስለው መራመድም ሆነ መቆም አቅተውታል። ብርክ ይዞት ይንገዳገዳል፡፡ ይህ ሰው የተሻለ ህይወት… Read more: የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይ
- ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል“ህወሓትና የግብረ አበሮቹ ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀቡ ይገባል” ሲል አማራ ክልል አሳሰበ። ስም… Read more: ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል