በቅርቡ ከዳርፉር ግዳጃቸውን አጠናቀው የተመለሱትን የሰላም እስከባሪ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የትህነግ ቡድን በተለያየ ዓለም አቀፍ ተቋም ውስጥ በሚሠሩ የራሱ ሰዎች አማካይነት የተለያዩ ጫናዎችን በማሳደር ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ ጥረት ማድረጉን የገለጹት የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ተፈራ መላክ ናቸው፡፡
ኮሎኔል ተፈራ መላክ ጁንታው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሀሰት ወሬን እየነዛና ሠራዊቱ ውስጥ ባደራጃቸው ቅጥረኞቹ አማካይነት ቅስቀሳዎችን ሲያደርግ ነበር ብለዋል፤ ለዚህ አንሸነፍም በማለት የሀገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ አንግበው የዘመቱት የሰላም አምባሳደሮች የጁንታውን ሴራ በማከሸፍ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡
የጁንታው ኃይል ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም አቀፍ ሰላም የማስከበር ተልዕኮ ያላትን ስምና ዝና ለማጉደፍና ዝቅ ለማድረግ ቢጥርም በሠራዊቱ ጥንካሬ ይህ ሴራው ከሸፏል ያሉት ደግሞ የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ዋና አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ ናቸው፡፡
አሸባሪው ሕወሃት ለትግራይ ሕዝብ አንዳችም የጠቀመው ነገር እንደሌለና አሁንም በሴራ የተተበተበ ስለመሆኑ ተግባሩ ይመሰክራል ያሉት የሠራዊቱ አባላት ይህን ኃይል የትግራይ ወጣቶች ሊታገሉት ይገባል ብለዋል፡፡ ምንጭ የመከላከያ ሚዲያ ዳይሬክቶሬት ነው
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ።… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በበጎ ጎኑንና… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to local… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism
- መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀMore stories «ዛሬ ዓባይ ተረት ሳይሆን የሚጨበጥ እውነት ነው» ዐቢይ አሕመድAugust 11, 2022 ትህነግ በምርጫ ቀን… Read more: መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀ