በቅርቡ ከዳርፉር ግዳጃቸውን አጠናቀው የተመለሱትን የሰላም እስከባሪ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የትህነግ ቡድን በተለያየ ዓለም አቀፍ ተቋም ውስጥ በሚሠሩ የራሱ ሰዎች አማካይነት የተለያዩ ጫናዎችን በማሳደር ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ ጥረት ማድረጉን የገለጹት የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ተፈራ መላክ ናቸው፡፡
ኮሎኔል ተፈራ መላክ ጁንታው በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሀሰት ወሬን እየነዛና ሠራዊቱ ውስጥ ባደራጃቸው ቅጥረኞቹ አማካይነት ቅስቀሳዎችን ሲያደርግ ነበር ብለዋል፤ ለዚህ አንሸነፍም በማለት የሀገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ አንግበው የዘመቱት የሰላም አምባሳደሮች የጁንታውን ሴራ በማከሸፍ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡
የጁንታው ኃይል ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም አቀፍ ሰላም የማስከበር ተልዕኮ ያላትን ስምና ዝና ለማጉደፍና ዝቅ ለማድረግ ቢጥርም በሠራዊቱ ጥንካሬ ይህ ሴራው ከሸፏል ያሉት ደግሞ የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ዋና አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ ናቸው፡፡
አሸባሪው ሕወሃት ለትግራይ ሕዝብ አንዳችም የጠቀመው ነገር እንደሌለና አሁንም በሴራ የተተበተበ ስለመሆኑ ተግባሩ ይመሰክራል ያሉት የሠራዊቱ አባላት ይህን ኃይል የትግራይ ወጣቶች ሊታገሉት ይገባል ብለዋል፡፡ ምንጭ የመከላከያ ሚዲያ ዳይሬክቶሬት ነው
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ