በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ጨረታ ያሸነፈው “ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ” የስራ ፈቃድ አገኘ።በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ያገኘው ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ የተባለው ኩባንያ ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።
የስምምነት ፊርማው የተከናወነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የኬኒያው ፕሬዝዳነት ኡሁሩ ኬኒያታ በተገኙበት ነው።የኢትዮጵያ ኮሙንኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ፤ ከቮዳኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ሻሚል ጆሱ፣ ከሳሪ ኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ኢድግዋ እንዲሁም ከሲሚቶሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ስምምነቱን ተፈራርመዋል።ኩባንያው ጫረታውን ያሸነፈበትን 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን የኢትዮጵያ ከሚዩኒኬሽን ባለስልጣን መግለፁ ይታወቃል።
በዛሬው እለት ደግሞ ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችለውን ፈቃድ ያገኘበት መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ በተገኙበት በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል።ግሎባል ፓርትነር ፎር ኢትዮጵያ የኬኒያው ሳፋሪ ኮም፣ የዩናይትድ ኪንግደም ቮዳፎንና ሲዲሲ ግሩፕ፣ የደቡብ አፍሪካውን ቮዳኮም የጃፓኑን ሲሚቶምና ዲኤፍሲን በጥምረት የያዘ ኩባንያ ነው።ኩባንያው በቀጣይ አስር ዓመታት ከ8 ቢሊዮን
ዶላር በላይ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።በዚህም ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላ ዜና የጃፓኑ ሱምቶም ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ በቴሌኮም ዘርፍ ኢንቨስት እንደሚያደርግ ገለጸ በቴሌኮም ዘርፍ የውጭ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ መንግስት በወሰደው ውሳኔ መሠረት ጨረታውን ያሸነፈው ‘የግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ ‘ ድርጅት አንዱ የሆነው የጃፓኑ ሱምቶም፤ በቀጣይ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ከሁለት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡
የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ቶሽካዙ ናምቡ የኢንቨስትመንት ዕቅዳቸውን ያስታወቁት፤ በጃፓን የኢ.ፌ.ዲ.ረ አምባሳደር ካሣ ተክለብርሃን ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው። ምክትል ሥራ አስፈጻሚው ኮርፖሬሽናቸው ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የኢትዮጵያ መንግስት በግልጸኝነት ባካሄደው የጨረታ ሂደት በማሸነፋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡አምባሳደር ካሣ ተክለብረሃን በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ በጃፓን፣በኤሽያ እና በአፍሪካ ያለው የካበተ ልምድ በኢትዮጵያ ኢንቬስት በማድረግ እንዲደግመው ጥሪ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል።
- ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡMore stories የቡና ግብይትና ጥራት ቁጥጥር ሕግ (ክፍል አንድ)August 29, 2023 ትህነግ የቡድን መሳሪያ ባስረከበ ማግስት ጦሩ ለተሃድሶ ካምፕ ገባMay 29, 2023 የትግራይ ክልልን መልሶ የመገንባትና የሰብዓዊ ድጋፍ ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል- አቶ ደመቀ መኮንንJanuary 22, 2021 ከፍተኛ ውድመት በደረሰባት የሰሜን ሸዋዋ አጣዬ ከተማ የመንግስት አገልግሎት ነገ ይጀመራልJune 6, 2021 ቀሲስ በላይ ከስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ… Read more: ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
- “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደትሰሞኑንን ለይቶለት ይፋ ሆነ እንጂ ውስጥ ውስጡን የጦርነት እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር መረጃዎች ከበቂ በላይ ነበሩ። ለዚህም ይመስላል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ንገሩዋቸው፣ ምክሩዋቸው” ሲሉ ከትግራይ ህዝብ ተወክለው ከመጡ ጋር ሲወያዩ ደጋግመው ያስታወቁት። በወይይቱ ላይ የተገኙ እናቶችም ” ካሁን በሁዋላ” ሲሉ ጦርነቱ ያስከተለው መዘዝና ጠባሳ እያንዘፈዘፋቸው ” ልጆቻችንን አንሰጥም” ሲሉ የተሰሙት። የድንበርና የማንነት ውዝግብ ያልተለየው የአማራና… Read more: “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደት
- የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይየ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እግሮቹ ቆስለው መራመድም ሆነ መቆም አቅተውታል። ብርክ ይዞት ይንገዳገዳል፡፡ ይህ ሰው የተሻለ ህይወት ይኖረናል ብለው በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሳኡዲ ዓረቢያ በባህር ላይ ተጉዘው ለእንግልት ከተዳረጉ ዜጎች መካከል አንዱ ነው፡፡ አብዱረሃማን ከማል ይባላል፡፡ ምስራቅ ሀረርጌ ባበሌ የትውልድ ሥፍራው ናት፡፡ በሱማሊያና በየመን አድርገን ወደ ሳኡዲ ዓረቢያ ለመግባት ሲሞክር አሲር በሚባል የሳኡዲ… Read more: የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይ
- ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል“ህወሓትና የግብረ አበሮቹ ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀቡ ይገባል” ሲል አማራ ክልል አሳሰበ። ስም ጠቅሶ ለአራተኛ ጊዜ ወረር የተፈጸመባቸውን ስፍራዎች አስታወቀ። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የፌደራል መንግስትና ዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ የህወሃትን የዳግም የጦርነት አዋጅ እንዲያወግዙና እንዲያስታግሱ ጠይቋል። ትህነግ ወረራ የፈፀመባቸው የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም እና ዛታ እንደሆኑ ያስታወቀው መግለጫው የክልሉ… Read more: ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል