በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ጨረታ ያሸነፈው “ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ” የስራ ፈቃድ አገኘ።በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ያገኘው ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ የተባለው ኩባንያ ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።
የስምምነት ፊርማው የተከናወነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የኬኒያው ፕሬዝዳነት ኡሁሩ ኬኒያታ በተገኙበት ነው።የኢትዮጵያ ኮሙንኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ፤ ከቮዳኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ሻሚል ጆሱ፣ ከሳሪ ኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ኢድግዋ እንዲሁም ከሲሚቶሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ስምምነቱን ተፈራርመዋል።ኩባንያው ጫረታውን ያሸነፈበትን 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን የኢትዮጵያ ከሚዩኒኬሽን ባለስልጣን መግለፁ ይታወቃል።
በዛሬው እለት ደግሞ ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችለውን ፈቃድ ያገኘበት መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ በተገኙበት በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል።ግሎባል ፓርትነር ፎር ኢትዮጵያ የኬኒያው ሳፋሪ ኮም፣ የዩናይትድ ኪንግደም ቮዳፎንና ሲዲሲ ግሩፕ፣ የደቡብ አፍሪካውን ቮዳኮም የጃፓኑን ሲሚቶምና ዲኤፍሲን በጥምረት የያዘ ኩባንያ ነው።ኩባንያው በቀጣይ አስር ዓመታት ከ8 ቢሊዮን
ዶላር በላይ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።በዚህም ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላ ዜና የጃፓኑ ሱምቶም ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ በቴሌኮም ዘርፍ ኢንቨስት እንደሚያደርግ ገለጸ በቴሌኮም ዘርፍ የውጭ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ መንግስት በወሰደው ውሳኔ መሠረት ጨረታውን ያሸነፈው ‘የግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ ‘ ድርጅት አንዱ የሆነው የጃፓኑ ሱምቶም፤ በቀጣይ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ከሁለት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡
የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ቶሽካዙ ናምቡ የኢንቨስትመንት ዕቅዳቸውን ያስታወቁት፤ በጃፓን የኢ.ፌ.ዲ.ረ አምባሳደር ካሣ ተክለብርሃን ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው። ምክትል ሥራ አስፈጻሚው ኮርፖሬሽናቸው ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የኢትዮጵያ መንግስት በግልጸኝነት ባካሄደው የጨረታ ሂደት በማሸነፋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡አምባሳደር ካሣ ተክለብረሃን በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ በጃፓን፣በኤሽያ እና በአፍሪካ ያለው የካበተ ልምድ በኢትዮጵያ ኢንቬስት በማድረግ እንዲደግመው ጥሪ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል።
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር መተብተቧ እየተጠቆመ ነው። በተጀመረው የአብይ ጾም ማቅ ለብሰውና አመድ ነስንሰው ችግራቸውን ሊፈቱ እንደሚገባ ምክር እየተሰጠ ነው። መንግስት በዋናነት ብቻ ባለው አስራ አንድ ጊዜ ስብሰባ የተቀመጠው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቅዱስ ሲኖዶስ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳለ የተጠቆመው አሁን ከቀናት… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡ More stories አጭበርባሪው ኮሎኔል – በሐሰተኛ ማንነትና ሰነዶች ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙJanuary 27, 2024 «የትግራይ ሕዝብ ያተረፈው መከራና ስቃይ ነው»May 5, 2022 አረንጓዴው ጎርፍ ሲታወስ፤ “የኢትዮጵያ ህዝብ ለማስደሰት እስከመጨረሻው ተስፋ አልቆረጥኩም” ጉዳፍ ፀጋይAugust 20, 2023 “በአማራ ክልል ግድያና… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ እውቀቶች ፈሰውበታል፤ አዳዲስ ነገሮች ተዋውቀውበታል፡፡ ዓለምን እጅ በአፍ አስጭኗል…. “ኒዮም ሲቲ” (Neom City) በሳውዲው ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ይፋ የሆነው ይህ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ በ2017 የተጀመረ ሲሆን በውስጡ አራት ሥራዎች ይገኙበታል፡፡ እነሱም ዘ ላየን፣ ኦክሳገን፣ ትሮጄና እና ሲንዳላህ… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions about the stability of the Horn of Africa and resulted in a similar deal struck between Somalia and Türkiye recently. However, arguments that the region might fall into turmoil due to Ethiopia’s move are overstated. Addis Ababa, with the deal,… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa