ኢ/ር ይልቃል መንግስት ከትህነግ ጋር ይደራደር አሉ፤ “ወያኔው ይልቃል የወልቃይትና የራያ ህዝብ ላይ ክህደት በመፈጸም ሊጠየቅ ይገባል”

ብሄር ብሄረሰቦች ሉዓላዊ መሆናቸውን ጠቁመው፣ትግራይ የራስዋ ባንዲራ ያላት ሉዓላዊ ክልል መሆኗን ይገልጻሉ። አያይዘውም በዓለም ላይ እንደታየው ትልልቅ አገሮች ትንንሽ አገሮች ውስጥ ገብተው እንደተዋረዱት እንዳይሆን ያሳስባሉ። ይህን ማብራሪያ ያስደገፉት መንግስት “አሸባሪ” ከተባለው ትህነግ ጋር መደራደር እንዳለበት ሲናገሩ ነው። ተናጋሪው ፓርቲ በመቀያየር የሚታወቁት ኢ/ር ይልቃል ናቸው።

ይህ የተባለው በአርት ቲቪ ላይ በተደረገ ውይይት ነው። የኢዜማው አቶ ግርማ ሰይፉና የህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ወኪል ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሲከራከሩ የሚከተለውን ተባባሉ

” … ድርድር መደረግ አለበት ”

ግርማ ሰይፉ ” ከማን ጋር?”

“ከማናቸውም ….”

ግርማ ሰይፉ ” ግልጽ አድርገው። ከማን ጋር? ከትህነግ?”

” … ከትህነግ ጋር ድርድር መደረግ አለበት ”

ግርማ ሰይፉ ቀበል አድርገው ትህነግ የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ያረደ፣ የጨፈጨፈ ከሃዲ ሃይል በመሆኑ ከእንዲህ ያለ አሸባሪ ሃይል ጋር ድርድር ሊታሰብ እንደማይገባ፣ ከሆነም በታረዱት ወገኖች ደም ላይ ክህደት መፈጸም እንደሆነና ሰራዊቱም ሆነ ህዝብ ተደራዳሪውን ሃይል እንደማይለቀው አስጠነቀቁ። እንደውም ትህነግ ላይመለስ መሸኘት ያለበት ክፉ ድርጅት መሆኑንን አመላከቱ።

ከለውጡ በሁዋላ የህዝብ የለውጥ ፍላጎት በመጋሉ አዲስ ፓርቲ እንዳቋቋሙ ለቢቢሲ ገልጸው የነበሩት ይልቃል፣ ” መርህ ይከበር” በሚል ወ/ት ብርቱካን ይመሩት የነበረውን አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲን ተለይተው ሰማያዊ ፓርቲ መስርተዋል። እዛም ብዙ ሳይቆዩ በተነሳባቸው የሌብነት ክስ ጉብኤ ፊት ቀርበው መሞገት ባለመቻላቸው ተሰናብተዋል። ከዛም “ኢሃን” የሚባል ፓርቲ አቋቋሙ። በቂ የፊርማ ዘመቻ ማሰባሰብ ያልቻሉት ይልቃል ከአቶ ልደቱ ጋር ተጣምረው የሽግግር መንግስትና የብሄራዊ መግባባት ሃሳብ አቀንቃኝ ሆኑ። መቸረሻ ላይ ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ላይ አረፉ። ዛሬ የምርጫ ተወዳዳሪ ናቸው።

ከፓርቲዎች ደጅ የማይከርሙት ይልቃል ” ከትህነግ ጋር ድርድር ማድረግ ብቸኛ አማራጭ ነው” ሲሉ በርካታ መከራከሪያ ቢያቀርቡም አማራነታቸው በሃይል እንደተጨፈለቀባቸው ለዓመታት በሚናገሩት በወልቃይትና በራያ ህዝብ ጥያቄ ላይ ምን ምላሽ እንዳላቸው አላብራሩም። በደፈናው ኢትዮጵያን አሁን ለደረሰችበት አስከፊ ደረጃ የዳረጋት ትህነግን እንደሚጠሉ አስታውቀው፣ በነካ ምላሳቸው ደግሞ ” ለትግራይ ህዝብ መፍትሄው ትህነግ ብቻ ነው። ሌላ አላማራጭ የለም” ሲሉ ይከራከራሉ።

አሜሪካ በተደጋጋሚና በግልጽ የአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ከትግራይ ክልል እንዲወጣ መጠየቋን፣ በውሳኔ R-97 መሰረት የጉዞ እገዳ ከተጣለባቸው መካከል የአማራ ክልል መሪዎችና የክልሉ የጸጥታ ሃላፊዎች መሆናቸው በገሃድ በስቴት ዲፓርትመንት በግልጽ ተጠቅሶ እያለ፣ አማራ ከትግራይ ክልል እንዲወጣ የሚጠየቅበት ምክንያት በግልጽ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ፣ ” አማራ ከትግራይ እንዲወጣ በሴኔት የውሳኔ ሃሳብ ላይ የለም” በሚል መከራከሪያ አስገዳጁንና “የአገር ሉዓላዊነት ይዳፈራል” የተባለውን ውሳኔ እንደሚደግፉ ይልቃል ደጋግመው አውስተዋል።

ግርማ ሰይፉ በተጠና ደረጃ ሚዲያዎች፣ የአውሮፓ አገራትና ተቋማት በተለይም አሜሪካ ምን እያራመደች አነደሆነ ለማንም ግልጽ እንደሆነ ሲያስረዱ፣ ለይልቃል ማብራሪያ ” ግራ የሚያጋባ” የሚል አስተያየት ነው የሰጡት። ደጋግመው እንዳሉትና ፓርቲያቸው እንደሚያምነው በሉዓላዊነት መቀለድ አይፈቀድም። የይልቃል ንግግርና ድጋፍም ” እኛ አስቀድመን የጠየቅነውን ሁሉን ያካተተ ድርድርና የሽግግር መንግስት ጥያቄ ያጠናክራል” ከሚል እሳቤ እንደሆነ ነግረዋቸዋል።

አቶ ግርማ ኢዜማ በሁሉን አቀፍ ንግግር፣ በብሄራዊ መግባባት፣ በሰከነ አገር ግንባታ እንደሚያምን አውስተዋል። ” ግን” አሉ አቶ ግርማ ” ግን ይህ ሂደት የሰከነ ጊዜ ያስፈልጋል። በችኮላ መንግስት ንዶ የሚከናወን አይሆንም” ሲሉ ለተቋማት ምስረታ ቅድሚያ እንደሚሰጡ ያብራራሉ። እንደ ምስሌ ምርጫ ቦርድን ያነሳሉ።

ይልቃል ምርጫ ቦርድን እንደማያምኑ፣ እንደውም ምርጫው አስፈላጊ ነው ብለው እንደማያምኑና ዋጋ ቢስ እንደሆነ ሲገልጹ፤ አቶ ግርማ ” ይህ ምርጫ ቦርድ የሚታመን፣ ከደህንነት ተቋሙ ጋር ያልተገናኘ፣ ማንም የማያዘው ነው” ሲሉ ክብር እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

ይልቃልና አቶ ልደቱ ግንባር ፈጥረው የምርጫ ቦርድን ሰብሰቢ ወ/ት ብርቱካንን ሲያወግዙና ” ተላላኪ” ባሏቸው ወቅት ክፉኛ ተቃውሞ ተሰንዝሮባቸው ነበር። ከትህነግ ጋር ቅርብ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሁለቱ ፖለቲከኞች ” አማራ ነን” በሚል ራሳቸውን ከአማራ ተቆርቋሪነት አንሳር የሚመድቡበት ጊዜ መኖሩን የሚያስታውሱ በውቅቱ ” የበግ ለምድ ለባሽ…” ሲሉ ወቅሰዋቸውም ነበር። ብርቱካን በሁሉም ነገር የተፈተኑ፣ የአጎብዳጅነት ታሪክ የሌላቸው እንደሆኑ ጠቅሰው የተከራከሩ እንዳሉት ልደቱም ሆነ ይልቃል ብዙ የሚያወራርዱት ጉዳይ እንዳለ ጠቅሰው ነበር። በተቃራኒ ” አብጃችሁ” ሲሉ እንደ 360 ዓይነት ገጾች አወድሰዋቸው ነበር።

ይልቃል ምርጫወን ” ዋጋ ቢስ” ምርጫ ቦርድን ” የማይታመን” ባሉበት የአርት ቲቪ ዲስኩራቸው ምን መልዕክት ለማስተላለፍ በምርጫው ዋዜማ ይህን ሊሉ እንደቻሉ ግልጽ እንዳልሆነላቸው ግርማ ሰይፉ አስታውቀዋል። ለመወዳደር እጩ ሆነው ሳለ ይህን ማለታቸው አግባብ እንዳልሆነ ያስረዱት ግርማ ሰይፉ ” እኔ ተወዳድሪ ነኝ ምረጡኝ” ሲሉ ማስታወቂያ ሰርተዋል።

ኢትዮ12 ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ተባባሪያዋን ጠቅሳ ባለቀ ሰዓት እንደማይመረጡ ሲያረጋግጡ ከምርጫ ለመውጣት እየተወሰወሱ ያሉ ድርጅቶች መኖራቸውን መግልጹ ይታወሳል። የአቶ ይልቃል ጥሪ ከዚሁ ውጥን ጋር ስለመያያዙ መረጃ የለም።

አቶ ይልቃል ከትህነግ ጋር ድርድር መደረግ እንዳለበት በማናገራቸውን ተከትሎ ከጎንደር ህብረት አንዱ ነኝ ያሉ ” በወልቃይትና በራያ ሕዝብ ላይ ክህደት በመፈጸም ሊጠየቅ ይገባል” ሲሉ በጽሁፍ አስተያየት ልከዋል። “ዛሬ በትግራይ የተከሰተው ቀውስ አሳዛኝ ነው። መላ ያስፈልጋል። በሌላ በኩል ግን ላለፉት ሰላሳ ዓመታት የራያና የወልቃይት ሕዝብ እንዴት ሲኖር እንደነበር ተዘንግቷል። ይህ በአማራ ላይ ክህደት መፈጸም ነው። ይልቃል ከዚህ የከሃዲዎች ፋይል ውስጥ አለ” ብለዋል። በዝርዝር መረጃ አጣቅሰው ለአንባቢ እንደሚያበቁም አመልክተዋል።


Leave a Reply

%d bloggers like this: