NEWS

ባልደራስ ዳግም የመረጮች ምዝገባ እንዲካሄድ ጠየቀ፤ የአዲስ አበባ የመርጫ ጣቢያ ወደ 300 ማነስ እንዳለበት በ”ጥናት” አረጋገጠ

ባልደራስ አዲስ አበባን ከብሄር እሳቤ ውጭ ለማድረግ ማሰቡን ገልጾ ሲነሳ ” በተረኘት ስሜት” የተደናገጡ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተቀብለውት እንደነበር፣ ከዛ በሁዋላ ብዙም ሳይቆይ ከአብን ጋር መጋባቱ ሙሉ ድጋፍ እንዳሳጣው፣ ከዚያም በላይ የትህነግ አፍ የነበረው ኤርሚያስን ለገሰን ምክትል ሊቀመንበር ማድረጉ ራሱን በራሱ ያከሰመ ያህል እንደጎዳው በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር።

ኢትዮ12 ከአራት ቀን በፊት ” በሂልተን ሎቢ ባልደራስ ምርጫ ቦርድ ለእስክንድር ደጋፊዎች ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ እንዲሰጠው የመጠይቀ ሃሳብ እንዳለው ማናገሩ ተሰማ” በሚል ርዕስ በጉዳዩ ዙሪያ ዝግጅት ሲደረግ እንደነበርና አስታውቃ ነበር።


ቀደም ሲል ከሂልተን በደረሰ ሪፖርት መሰረት ይህን ጽፈን ነበር


በዘገባው ” ለኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ተባባሪ ትዝብቱን የሚያካፍለው የውጭ አገር ጋዜጠኛ እንዳለው ባልደራስ እነ እስክንድር ምርጫ የሚወዳደሩ ያልመሰላቸው ደጋፊዎቻችን ስላልተመዘገቡ ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ የመመዝገቢያ ቀን እዲሰጣቸው ለመጠይቅ ማቀዳቸውን ትልቅ ለምትባለዋ አገር ዲፕሎማት ነግረዋል” ነበር ስትል ነበር አምዳችን የአዲስ አበባ ተባባሪዋን ጠቅሳ የጻፈችው።

ዛሬ ኢትዮ ኢንሳይደር የሚባለው የድረ ገጽ ሚዲያ ባልደራስ ዛሬ በራስ አምባ ሆቴል ባካሄደው መግለጫ በርካታ ክሶችን ካቀረበ በሁዋላ፣ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱ በበርካታ ችግሮች የተተበተበ መሆኑንን የበጥናቱ አስታውቆ ፓርቲው፤ የምርጫ ካርድ ማውጫ ጊዜ እንዲራዘም በድጋሚ ጠይቋል።

ባልደራስ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱ በተጠናቀቀበት ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይም ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርቦ ነበር። የመጪው ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ሁለት ሳምንት በቀረው በዚህ ጊዜም፤ ባልደራስ አሁንም ይህን አቋሙን አለመተውን አስታውቋል። የፓርቲው የሰብዓዊ መብት እና የህግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሔኖክ አክሊሉ፤ “የመራጮች ምዝገባ እንደገና እንዲደረግ ባልደራስ ይጠይቃል” ሲሉ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በሰነድ ጥያቄውን ስለማቅረባቸውና አዎንታዊ ምላሽ ካላገኙ ምን እርምጃ እንደሚወስዱ ይፋ አላደረጉም።

ስለ አዲስ አበባ ያነሳው የባልደራስ መግለጫ ቅድመ ምርጫ ሂደቱ ከእጩዎች እና መራጮች ደህንነት አኳያ ምርጫው “የደህንነት ስጋት” እንዳለበት አመልክቷል። ፓርቲው ለዚህ በማሳያነት የጠቀሳቸው በቢሾፍቱ፣ በመተከልና በጎንደር መተማ ዩሃንስ የተገደሉ የኢዜማ እና የአብን አባላትን ነው። “እነዚህ ግድያዎች የቅድመ ምርጫውን ሂደት ነጻነት እና ፍትሃዊነት አጠያያቂ ያደርገዋል” ሲል ባልደራስ አዲስ አበባ ላይ ላነሳው ጥያቄ ማሳያ አድርጓል።

ኢትዮ 12 ሜይ 23 ቅድመ ዳሰሳ ለሚካሂዱ አባሎቻቸውና የውጭ ሚዲያዎች ኦፊሳል ባልሆነ ስብሰባ  US AID፣ አሜሪካን ኤምባሲ፣አሊያንስ ፍራንስ በህብረት ባዘጋጁት የመሰረታዊ መረጃ ማስጨበጫ ውይይት ላይ በስም ጠቅሰው አብንና ባልደራስ ምርጫው ሲቃረብ መመረጣቸውን ሲጠራጠሩ ባለቀ ሰዓት ሊያፈነግጡ እንደሚችሉ መረጃ ጠቅስው መናገራቸውን አስታውቀን ነበር። ከስር ያለውን ያንንቡበምዘገባ፣ በቅሰቀሳ፣ በመዘግብ ማጣራት፣ የራት አባላቱ እስር፣ መገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም፣ አዲስ አበባ እንግልትና ግርግር እንዳይኖር በሚል ታስቦ 1727 የምርጫ ድምጽ መስጪያ ጣቢያ መኖሩን እንደ ችግር አንስቶ ቸግሩ በ300 የምርጫ ጣቢያ ብቻ ለሰጥ እንደሚገባ በጥናት ማረጋገጡን አውስቷል። በመጨረሻም ምንም እንኳ ምርጫው እንጀን የሞላበት ቢሆንም ሁሉም ወገን ትብብር እንዲያደርግ ጠይቋል። የፓርቲው የውጭ ክንፍ መሪ የሆኑትና የ360 ተንታኝ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ማምሻውን ምን እንደሚሉ አልታወቀም።

ሙሉ መረጃው እንዲኖራችሁ ኢትዮ ኢንሳይደርን እዚህ ላይ በመክፈት ቪዲዮውን ያድምጡ


Categories: NEWS

Tagged as:

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s