MIMI
MIMI
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሚሚ አለማየሁ የትዊተር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆና መመረጧን ድርጀቱ አስታውቋል፡፡
እያደገ በመጣው ገበያ ከ20 ዓመታት በላይ የኢንቨስትመንት እና የገበያ ባለሞያነት ልምድ ያላት ሚሚ ለቦርድ አባልነት አብቅቷታል ተብሏል፡፡
ሚሚን ለቦርድ አባልነት ያበቃት በተለያዩ አዳጊ ገበያዎች በመንግሥት እና የግል የኢንቬስትመንት እና የፋይናንስ ዘርፎች ከ20 ዓመታት በላይ በመስራት ያካበተችው ልምድ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
ሚሚ ያላት ይህ ሰፊ ተሳትፎ እና ልምድ ትዊተር በዓለም ዙሪያ የህዝብ ውይይትን ለማዳበር የያዘውን ተልዕኮ ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የትዊተር ገለልተኛ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ ፒቼት ገልፀዋል፡፡
ሚሚ የትዊተርን ማህበራዊ ኃላፊነት እና ዓለምአቀፋዊ ማህበረሰብን የመፍጠር ተልዕኮ ትጋራለች ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው ትዊተር በተለይ በአፍሪካ ያለውን ተልዕኮ ለማስፋፋት በጋና ቢሮ በመክፈቱ የሚሚን ስራ እንፈልገዋለን ብለዋል፡፡
በዓለም ላይ ህዝባዊ ውይይቶች እንዲዳብሩ ዓልሞ እየሰራ ያለውን ትዊተር አደንቃለሁ ያለችው ሚሚ በበኩሏ የትዊተር ገለልተኛ ቦርድ አባል በመሆኔ ኩራት ተሰምቶኛል ስትል ደስታዋን ገልፃለች፡፡
ሚሚ አለማየሁ በማስተርካርድ የመንግስት እና የግል ጥምረት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያለገለች ትገኛለች፡፡ ENA
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡ More stories… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ እውቀቶች… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions about the… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች ለዓመታት የቆየ ውዝግብ… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ