ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አደም ፋራህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል እና ለአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዩርሱላ ቮን ደር ላየን አድርሰዋል፡፡
አፈጉባኤው ከአውሮፓ ህብረት አመራሮች ጋር ኢትዮጵያ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ እና ፍትሓዊ ምርጫ ለማድረግ እያደረገች ያለው ጥረት፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር፣ በትግራይ እየተደረገ ያለው የሰብአዊ ድጋፎችና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በዚህ ወቅትም የአውሮፓ ህብረት የስራ ሃላፊዎች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ በአግባቡ እንዲደርሳቸው የሚደረገው ጥረት ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
የስራ ሃላፊዎች በትግራይ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በጋራ የጀመረው የምርመራ ሂደት የሚበረታታ ነው ማለታቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡
የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ የተላከ ደብዳቤን አደረሱ፡፡
ደብዳቤውን ለሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና የውጭ ንግድ እና ልማት ትብብር ሚኒስትር ሲግሪድ ካግ አስረክበዋል፡፡
በዚህ ወቅትም ከሚኒስትሯ ጋር በተለያዩ ጉደዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡
በውይይታቸው ወቅትም በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ በመጪው ሃገራዊ ምርጫ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር እና በኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ ዙሪያ መምከራቸውንም ገልጸዋል፡፡ via . FBC
- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”“የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም!” በሚል ርዕስ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ባሰራጨው መግለጫ… Read more: የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”
- በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!More stories አዲሱ ሚኒስትር “የሰላም እጦት”February 23, 2024 ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ህዝብ ተወካዮች ጋርApril 1, 2024 ካለፈ… Read more: በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late on Thursday, citing… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report