የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 36 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባለፉት 10 ወራት ብቻ 36 ቢሊዮን 315 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።

በቢሮው የሕግ ተገዥነት ሥራዎች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮማንደር አህመድ መሐመድ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ ቢሮው በበጀት ዓመቱ 10 ወራት 36 ቢሊዮን 838 ሚሊዮን 844 መሰብሰብ አቅዶ፤ 36 ቢሊዮን 315 ሚሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ የእቅዱን 98 ነጥብ ስድስት በመቶ አሳክቷል።

የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸሙ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በሰባት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር ወይም 24 ነጥብ ሰባት በመቶ ብልጫ እንዳለው አስታውቀዋል።

እንደምክትል ቢሮ ኃላፊው ገለጻ፤ ዘንድሮ ለመሰብሰብ ከታቀደው ከ42 ቢሊዮን 479 ሚሊዮን ብር 92 በመቶ አሳክቷል። የ10 ወራትን አፈጻጸም እንኳን ሲታይ በእቅድ ከተያዘው የእቅዱን 98 ነጥብ ስድስት በመቶ ማሳካት ችሏል ብለዋል።

አብዛኛው ሥራ ዛሬም በእጅ (ማኑዋሊ) የሚሰሩ መሆናቸውና ማህበረሰቡ ለግብር ያለው አተያይ ዛሬም አለመስተካከሉ በግብር አሰባሰብ ሂደት ፈታኝ ችግሮች እንደነበሩ አመልክተው፣ በአመራሩና በሠራተኛው መካከል የተቀናጀ አሠራር መኖር ችግሩን አሸንፎ ለመውጣት አቅም መፍጠሩን አስታውቀዋል።
(ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply

%d bloggers like this: