በኢትዮ-አውሮፓ ህብረት የጋራ ምክክር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ጆሃን ቦርግስታም በጋራ መሪነት ተካሂዷል።

ምክክሩ በኢትዮ-አውሮፓ ህብረት የትብብር ጉዳዮች፣ የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ፣ የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ እንዲሁም በቀጣይ በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ላይ በማተኮር የተካሄደ መሆኑ ተነግሯል።

በወቅቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት መካከል የሚደረገው ቋሚ ምክክር በኮቶኖ ስምምነት እንዲሁም በኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት መካከል እ.ኤአ በ2016 የተፈረመውን የስትራቴጂያዊ የትብብር ሰነድ መሰረት ያደረገ ሰለመሆኑ ገልጸዋል።

በወቅቱም ተሳታፊ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት አምባሳደሮች በሰጡት አስተያየት የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵየ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት በተያዩ መልኩ ድጋፍ ማደረጉን አስታውሰው፣ ወረርሽኙ በኢኮኖሚው ላይ የሚደርስባትን ተጽዕኖ ለመከላከል የተከተለችውን መንገድ እንደሚያደንቁ ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚውን ለመክፈት በተሌኮም ሴክተር የታየው ተግባራዊ እርምጃ የሚበረታታ መሆኑንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ሆኖ እንዲቋቋም መደረጉን እንደሚያደንቁ ገልጸው፤ ቀጣዩን አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ከሎጀስቲክ ስርጭት አንጻር የሚያጋጥሙ ችግሮች ትኩረት መሰጠት ያለበት መሆኑን አምባሳደሮች አንስተዋል።

የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እየወጡ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሂደቱን ለማፋጠን የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

በትግራይም የተፈናቀሉ ዜጎች ከዝናብ ወቅት በፊት ለመመለስ እንዲቻል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተቋቋመው ኮሚቴ አማካይነት ስራዎች እየተከናወኑ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

የሕወሓት ቅሪቶች በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር አባላት እና ሌሎች ንጹሃን ዜጎችን ዒላማ ማድረግ መቀጠላቸውን ጠቅሰው፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁኔታውን በሚዛን በማየት መሰል ተግባራትን በይፋ መኮንን እንደሚገባው አቶ ደመቀ ጠቅሰዋል።

የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተም የጠቅላይ አቃቢ ህግ፣ የፌደራል ፖሊስ ከሚሽን ከትግራይ ክልል ጊዚዊ አስተዳደር ጋር በመተባበር አስፈላጊው ምርመራ በማድረግ አጥፊዎችን ተጠያቂ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።

ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጠቀሙ https://www.ena.et/?p=130954

Leave a Reply

Previous post የትግራይ ክልልን መልሶ ለማቋቋምና እየተሰሩ ያሉትን አበረታች ስራዎች መካድ ተቀባይነት እንደሌለዉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ
Next post የኬንያው ፕሬዝዳንት ቆይታ ውጤታማ ነበር – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
%d bloggers like this: