ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሚሚ አለማየሁ የትዊተር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሚሚ አለማየሁ የትዊተር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆና መመረጧን ድርጀቱ አስታውቋል፡፡

ሚሚ

እያደገ በመጣው ገበያ ከ20 ዓመታት በላይ የኢንቨስትመንት እና የገበያ ባለሞያነት ልምድ ያላት ሚሚ ለቦርድ አባልነት አብቅቷታል ተብሏል፡፡

ሚሚን ለቦርድ አባልነት ያበቃት በተለያዩ አዳጊ ገበያዎች በመንግሥት እና የግል የኢንቬስትመንት እና የፋይናንስ ዘርፎች ከ20 ዓመታት በላይ በመስራት ያካበተችው ልምድ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ሚሚ ያላት ይህ ሰፊ ተሳትፎ እና ልምድ ትዊተር በዓለም ዙሪያ የህዝብ ውይይትን ለማዳበር የያዘውን ተልዕኮ ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የትዊተር ገለልተኛ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ ፒቼት ገልፀዋል፡፡

ሚሚ የትዊተርን ማህበራዊ ኃላፊነት እና ዓለምአቀፋዊ ማህበረሰብን የመፍጠር ተልዕኮ ትጋራለች ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው ትዊተር በተለይ በአፍሪካ ያለውን ተልዕኮ ለማስፋፋት በጋና ቢሮ በመክፈቱ የሚሚን ስራ እንፈልገዋለን ብለዋል፡፡

በዓለም ላይ ህዝባዊ ውይይቶች እንዲዳብሩ ዓልሞ እየሰራ ያለውን ትዊተር አደንቃለሁ ያለችው ሚሚ በበኩሏ የትዊተር ገለልተኛ ቦርድ አባል በመሆኔ ኩራት ተሰምቶኛል ስትል ደስታዋን ገልፃለች፡፡ ሚሚ አለማየሁ በማስተርካርድ የመንግስት እና የግል ጥምረት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያለገለች ትገኛለች፡፡


Leave a Reply

%d bloggers like this: