ዜጎች አጠራጣሪ ነገር ሲመለከቱ በ910 የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጥሪ አቀረበ

ዜጎች ማንኛውም ለሀገርና ለህዝቦች ሰላምና መረጋጋት እንቅፋት የሚሆኑ እንዲሁም ከሀገራዊ ምርጫው ጋር በተያያዘ የደህንነት ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ አጠራጣሪ ሁኔታዎችን በአቅራቢያችሁ ስትመለከቱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አጭር የጥቆማ መስጪያ ቁጥር 910ን በመጠቀምና ጥቆማ በመስጠት ለጋራ ደህንነታችን መረጋገጥ የበኩላችሁን እንድትወጡ ሲል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጥሪ አቅርቧል።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሀገሪቱን ደህንነትና ብሔራዊ ጥቅም የመጠበቅ ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም ሲሆን፤ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ተልዕኮውን ለመወጣት የሚያግዙ መረጃዎችን፣ ይሰበስባል፣ይተነትናል ለሚመለከተውም አካል ይሰጣል። የመረጃና ደህንነት ተቋም ሥራ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን የህብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ሲል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለኢቲቪ በላከው መረጃ ገልጿል፡፡


Leave a Reply

%d bloggers like this: