ቻይና አጋርነቷን ከመርህ አንጻር በገሃድ አስታወቀች፤ በመቐለ ያሉ ጤና ተቋማት በሙሉ ሥራ መጀመራቸው ተገለጸ

ቻይና በኢትዮጵያ ጉዳዮች የውጭ ጣልቃ ገብነትን ትቃወማለች ብለዋል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ፡፡የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ፤ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳዮች የሚደረግ ጣልቃ ገብነትን አገራቸው እንደምትቃወም መናገራቸው ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ይን ጠቅሶ ሲጂቲኤን እንደዘገበው፤ ቻይና በኢትዮጵያ ጉዳዮች የውጭ ጣልቃ ገብነትን ትቃወማለች።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ከኢትዮጵያው አቻቸው ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ከተወያዩ በኋላ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ዋንግ ይ “ሁለቱ አገራት የሚተባበሩ አጋሮች ናቸው” ብለዋል፡፡ሲጂቲኤን በድረ ገጹ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር “ኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነትና መረጋጋቷን የመጠበቅ መብት አላት” ማለታቸውን አስነብቧል።

“ኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳዮቿን በዋነኛነት በራሷ ጥረት መፍታት አለባት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን ፍቃድ አክብሮ ድጋፍ መስጠት ነው ያለበት ማዕቀብ መጣልም የለበትም” ማለታቸውም ተዘግቧል።የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያው አቻቸው ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት፤

“ቻይና በትግራይ ክልል ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለማርገብ እርዳታ ለመስጠት ፍቃደኛ ናት የመጀመሪያው ዙር የምግብ እርዳታም ተልኳል” መባሉን ዢንዋ ዘግቧል።ቻይና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት ፖሊሲን በማራመዷ አቶ ደመቀ፤ ማመስገናቸውንም ዘገባው አስነብቧል።

ከወራት በፊት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ቀውስ በተመለከተ ውይይት በተደረገበት ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥትን ደግፈው ከቆሙ አገራት መካከል በምክር ቤቱ ድምጽን በድምጽ የመሻር ሥልጣን ያላት ቻይና አንዷ ነበረች።

በሌላ ዜና

በመቐለ ከተማ የሚገኙ የጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወደስራ መግባታቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡ የጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ የወደሙባቸው እና ራቅ ብለው ባሉ አከባቢዎች የጤና አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻልም በ60 ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮች አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በቢሮው የድንገተኛ ህክምና እንዲሁም የፈውስና ተሃድሶ የሥራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር አቤኔዘር ዕጸድንግል እንደገለጹት፤ በጥቃቱ በክልሉ በርካታ የጤና ተቋማት በከፊል እና ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡ እነዚህን ጤና ተቋማት ወሰድራ ለማስገባት በተከናወኑ ተግባራት ግን በርካቶችን ጠግኖና ግብዓት አሟልቶ ወደስራ ማስገባት የተቻለ ሲሆን፤ በመቐለ ያሌ ጤና ተቋማት ግን ሙሉ በሙሉ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

እንደ ዶክተር አቤኔዘር ገለጻ፤ በጤና ዘርፉ እንደ አገር ምሳሌ የሚሆን እንቅስቃሴ የነበረበት የትግራይ ክልል በጥቃቱ በርካታ የጤና ተቋማት ወድመዋል፡፡ በዚህም የህግ ማስከበር እርምጃው እንደተጠናቀቀ በተወሰነም ቢሆን አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የጤና ተቋማት ቁጥር ከ50 ያልበለጡ ነበሩ፡፡ይህ ደግሞ በክልሉ የጠየና አገልግሎት ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት አዳጋች አድርጎት የነበረ ሲሆን፤ ከፌዴራል መንግስትና አጋሮች ጋር በተደረገ ርብርን በርካታ የጤና ተቋማትን ጠግኖና ግብዓት አሟልቶ ወደስራ ማስገባት ተችሏል፡፡

በዚህም በመቐለ ከተማ ያሉ የጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ሥራ የጀመሩ ሲሆን፤ ጤና ተቋማት ተጠግነው ወደስራ ባልገቡባቸው አከባቢዎች ለመድረስም በ60 ያህል ተንቀሳቃሽ ጀክሊኒኮች በመታገዝ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡በመቐለ ከተማ ከሚገኙ የጤና ተቋማት መካከል በዓዲ ሹምዱሑን ጤና ጣቢያ እና በየካቲት 11 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎቱ እየተሰጠ መሆኑን ዝግጅት ክፍላችን የተመለከተ ሲሆን፤ የየጤና ተቋማቱ ኃላፊዎች እንደገለጹትም የጤና ተቋማቱ በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል፡፡ ኢፕድ በወንድወሰን ሽመልስ (መቐለ)


 • ትህነግ- በኤርትራ ስደተኞች ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት እንዲቆም አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ተነፈሰች
  የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች በትግራይ በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያቆሙ አሜሪካ አሳሰበች በትግራይ ክልል በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ በህወሃት ታጣቂዎች እየደረሰባቸው ያለው ጥቃት እና ማስፈራራት እንዲቆም የአሜሪካ መንግሥት አሳሰበ። በትግራይ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ስደተኞች በአሸባሪው የህወሓት ቡድን እየተገደሉ፣ እየተደፈሩና ንብረታቸው እየተዘረፈ መሆኑን የማይፀምሪ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ አስተባባሪ አቶContinue Reading
 • በታደሰ ወረደ ፃድቃን ገ/ትንሳኤን ጨምሮ በ74 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱን ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ
  ዐቃቤ ሕግ በእነ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ጀነራል ገብረፃድቃን ገ/ትንሣኤን ጨምሮ በ74 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱን በይፋ ማህበአዊ ገጹ ይፋ አድርጓል። ሰነዶችንም አያይዟል። የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ክስ የመሰረተዉ ተከሳሾች የፌዴራል መንግስትን በሀይል ለመለወጥ በማሰብ በሽብርተኝነት ከተፈረጀዉ ከህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራሮች ተልእኮ በመቀበል ጥቃት ለማድረስ የሚችልContinue Reading
 • U.S. calls for halt to violence against Eritreans in Tigray
  The United States is deeply concerned about reported attacks against Eritrean refugees in Ethiopia’s Tigray region, a U.S. State Department spokeswoman said on Tuesday, calling for the intimidation and attacks to stop. “We are deeply concerned about credible reports of attacks by military forces affiliated with the Tigray People’s LiberationContinue Reading
 • ትህነግ ቅድመ ሁኔታ አንስቶ ድርድር ጠየቀ፤ “ክተቱ ለትህነግና ለኢትዮጵያ ጠላቶች እንጂ ለትግራይ ሕዝብ አይደለም”
  አዲስ አበባ በሁለት ሳምንት ለመግባት የሚያግደው አንዳችም ሃይል እንደሌለ በይፋ ያስታወቀውና በቃል አቀባዩ ጌታቸው አማካይነት ትናንት ጎንደርና ወልቃይት በአሸባሪው ትህነግ እጅ መውደቁን ያወጀው ቡድን ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ትቶ ድርድር እንደሚፈልግ ማስታወቁ ተሰማ። ለዚሁ ተግባር አዲስ አበባ የገቡ አሜሪካዊ አማላጆች መኖራቸውን ታውቋል። ቀደም ሲል ስምንት ቅደመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ የነበረው የትግራይ ሕዝብContinue Reading
 • The Rise, Rule & Fall of TPLF in Ethiopia
  By – Birhanu M Lenjiso 1) Executive Summary It took TPLF 16 years to rise to power in Ethiopia. For nearly twice as long, they used extraordinary cruelty (iron fist strategy) to maintain dominance in Ethiopian political and economic life. The fall of TPLF however was dramatic and shocking thatContinue Reading

Leave a Reply