የህዳሴ- ደዴሳ ባለ500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርን የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሥራ ለሚጀምረው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዝግጁ የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የምዕራብ ሪጅን ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ቶማስ መለሰ ገለጹ፡፡
በተለያየ ምክንያት የተሰበሩትን ኢንሱሌተሮችን በአዲስ የመተካት ስራም ተጀመረል። እንደ ዳይሬክተሩ ገላጻ ኢንሱሌተሮቹን የመተካት ሥራው የተጀመረው በቅርቡ የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሥራ ለሚጀምረው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መስመሩን ዝግጁ ለማድረግ ነው፡፡
ኢንሱሌተር የመቀየር ሥራው ከህዳሴ- ደዴሳ – ሆለታ ድረስ ከተዘረጋው መስመር መካከል እስከ ደዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ድረስ ባለው በሁለቱም የማስተላለፊያ መስመሮች በተተከሉ ምሶሶዎች ላይ እንደሚከናወን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
በመስመሩ ላይ በተካሄደለት የፍተሻ ስራ መሠረት ከአንድ ሺህ 535 ምሶሶዎች በ312 ምሶሶዎች ላይ የሚገኙ ኢንሱሌተሮችን በሌላ የመቀየር ስራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል።በቀጣይ ከደዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያ እስከ ሆለታ ማከፋፈያ ጣቢያ በተዘረጋው ባለ500 ኪሎ ቮልት ማስተላለፊያ መስመር ላይ የተሰበሩ ኢንሱሌተሮችን በተመሳሳይ የመቀየር ሥራ እንደሚከናወን ተጠቁማል።
የደዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ስምንት ባለ33 እና ሁለት ባለ132 እንዲሁም አንድ ባለ500 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ያሉት ሲሆን በአሁኑ ሠዓት ሁለት ባለ33 እና አንድ ባለ132 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች ለነቀምቴ ከተማ እና አካባቢው ኃይል በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመለክታል፡፡
የህዳሴ ደዴሳ ሆለታ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ቻይና ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጅ በተሰኘ ኩባንያ መገንባቱ ይታወሳል ሲል ኢፕድ ነው የዘገበው።
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William Ruto… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting a… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late on Thursday, citing a… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report
- ዓለም ባንክና መንግስት በአሜሪካ እየመከሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ” የብርን የምንዛሬ አቅም ቀንሱ” ጥያቄ አልተቀበለችምዓለም ባንክና የዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም ኢትዮጵያ የጠቀችውን ብድር ለመፍቀድ ያቀረቡት ዋና ቅድመ ሁኔታ የብርን የመግዛት አቅም ዝቅ… Read more: ዓለም ባንክና መንግስት በአሜሪካ እየመከሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ” የብርን የምንዛሬ አቅም ቀንሱ” ጥያቄ አልተቀበለችም
- ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡMore stories “የትናንት ዘር፣ የዛሬ ፍሬ፣ የነገ ስንቅ!” ዐቢይ አሕመድFebruary 2, 2023 አማራ ክልል አሸባሪው ሃይል ላይ አርምጃው… Read more: ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ