የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናዋ 100 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ከጎጆ ብሪጅ ማህበር ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል። የከተማ አስተዳደሩ የመኖሪያ ቤት ችግርን ከማቅለል አንፃር የተያዘውን እቅድ ለመተግበር ሲባል አብሮ ለመስራት መስማማቱ ተገልጿል።
ይህ ማህበር በቅርቡ ከ1000 የሚልቁና ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን ለመገንባት የዲዛይን ስራ እያከናወነ መሆኑ ተጠቅሷል። በቀጣይም በዋነኛነት መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ግለሰቦች የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ማድረግ ላይ በማተኮር ቤት ተመዝግበው ለሚጠባበቁ እንዲሁም በማህበር ተደራጅተው እየተጠባበቁ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን ለመደገፍ ማለሙ ተገልጿል።
የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ አልማው ጋሪ ማህበሩ ቤቶችን በእቅዱ መሰረት ሰርቶ ለማስረከብ እና ሀላፊነቱን ለመወጣት እንደሚንቀሳቀስ ገልጸዋል።
የከተማው ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር መስከረም ዘውዴ በበኩላቸው በከተማው ያለውን የጋራ መኖሪያ ቤት ችግር ለማቅለል ይዞ የመጣውን አማራጭ ሃሳብ በመቀበል አስተዳደሩ ከማህገሩ ጋር በጋራ እንደሚሰራም በማስታወቅ የጋራ የመግባቢያ ፊርማ ተከናውኗል።
ጎጆ ብሪጅ የግል ይዞታ ኖሯቸው መገንባት ያልቻሉ ግለሰቦችን በማህበር በማደራጀት ከቦታቸው ሳይነሱ ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት በማለም ከ3 ዓመታት በፊት የተደራጀ ማህበር ነው።
በጥላሁን ካሳ EBC
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ በሀገራችንም የሽግግር… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው” የሚለው የዋዜማ ዜና ፖለቲካውን… Read more: “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In its statement, the… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council