የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናዋ 100 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ከጎጆ ብሪጅ ማህበር ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል። የከተማ አስተዳደሩ የመኖሪያ ቤት ችግርን ከማቅለል አንፃር የተያዘውን እቅድ ለመተግበር ሲባል አብሮ ለመስራት መስማማቱ ተገልጿል።
ይህ ማህበር በቅርቡ ከ1000 የሚልቁና ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን ለመገንባት የዲዛይን ስራ እያከናወነ መሆኑ ተጠቅሷል። በቀጣይም በዋነኛነት መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ግለሰቦች የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ማድረግ ላይ በማተኮር ቤት ተመዝግበው ለሚጠባበቁ እንዲሁም በማህበር ተደራጅተው እየተጠባበቁ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን ለመደገፍ ማለሙ ተገልጿል።
የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ አልማው ጋሪ ማህበሩ ቤቶችን በእቅዱ መሰረት ሰርቶ ለማስረከብ እና ሀላፊነቱን ለመወጣት እንደሚንቀሳቀስ ገልጸዋል።
የከተማው ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር መስከረም ዘውዴ በበኩላቸው በከተማው ያለውን የጋራ መኖሪያ ቤት ችግር ለማቅለል ይዞ የመጣውን አማራጭ ሃሳብ በመቀበል አስተዳደሩ ከማህገሩ ጋር በጋራ እንደሚሰራም በማስታወቅ የጋራ የመግባቢያ ፊርማ ተከናውኗል።
ጎጆ ብሪጅ የግል ይዞታ ኖሯቸው መገንባት ያልቻሉ ግለሰቦችን በማህበር በማደራጀት ከቦታቸው ሳይነሱ ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት በማለም ከ3 ዓመታት በፊት የተደራጀ ማህበር ነው።
በጥላሁን ካሳ EBC
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by the people of… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በበጎ ጎኑንና በስጋት ከፍለው መግለቻቸው… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to local companies, would bring… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism
- መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀMore stories መከላከያ የሙትና የቁስለኛና ምርኮኛ ቁጥር ይፋ አደረገ ” ይቀፋል፣ መነገር ስላለበት እንናገራለን”September 4, 2021 “ከሚሰጣቸው ዳረጎት ውጪ… Read more: መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀ